Get Mystery Box with random crypto!

ቅኔ ያለው ትውልድ

Logo of telegram channel keney_serezoch — ቅኔ ያለው ትውልድ
Logo of telegram channel keney_serezoch — ቅኔ ያለው ትውልድ
Channel address: @keney_serezoch
Categories: Literature
Language: English
Subscribers: 1.33K
Description from channel

ለነፋሳቹ ነፋስ የሚሆኑ ነገሮችን ዝሩለት . . !
ቤቴን ቤቶ ስላረጉ አመሰግናለው!
. .

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages 9

2021-05-28 07:35:47
” ማንም ሰው ሌላውን ሰው በዘሩ እና በቆዳው ቀለም ወይም በሃይማኖቱ እንዲጠላ ሆኖ አልተወለደም ሰዎች መጥላትን ተምረውት ነው ። የሰው ልጅ ጥላቻን ከተማረ ፍቅርንም መማር ይችላል ። እንደውም ፍቅር ለሰው ልጅ ተፈጥሮ ከጥላቻ ይልቅ ቅርብ ነው ። ” ኔልሰን ማንዴላ

╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
93 views04:35
Open / Comment
2021-05-27 13:24:59
የፈጣሪ ልሳን

እጆቼን ዘርግቼ .......
ልጸልይ ፣ ልማልድ ፣ ከደጅኽ ተገኘኹ ፤
አንጋጥጬ ሽቅብ በሐሳቤ ዋኘኹ ።
ተንበርክኬ ለምሕላ በግንባሬ ተደፍቼ
ቀና ማለት ተዘነጋኝ ፤ የቃል ጸሎት ረስቼ ።

ያ'ንደበትኽ ልሳን ከየት ተሰወረ ?
ቃል ከምላሴ ላይ እንደምን ታወረ ?
ዝም ........ !
ዝም ዝም ........... !
እንደው ዝም ! ዝምታዬ ቀረ ፤
ሰምተኸኛል አንተ ፤
በዝምታ ልሳን ጸሎቴም ሰመረ ።


የሞት ጥቁር ወተት ( ተስፋኹን ከበደ )

╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
145 viewsedited  10:24
Open / Comment
2021-05-27 06:48:25 አንድ ቀን አንድ የትምህርት ቤት መምህር በሰሌዳው ላይ የሚከተለውን ፃፈ ፡፡
* 9 × 1 = 7 *
* 9 × 2 = 18 *
* 9 × 3 = 27 *
* 9 × 4 = 36 *
* 9 × 5 = 45 *
* 9 × 6 = 54 *
* 9 × 7 = 63 *
* 9 × 8 = 72 *
* 9 × 9 = 81 *
* 9 × 10 = 90 *

ከጨረሰ በኋላ ወደ ተማሪዎቹ እና ወደኋላ መለስ ብሎ ተመለከተ………

የመጀመርያውን ስሌት አይተው ሁሉም ሳቁ
ስህተት ነበር ፡፡ *

ከዚያም አስተማሪውም
"የመጀመሪያውን ቀመር የተሳሳትኩት ሆነ ብዬ ነው ፣ ምክንያቱም አንድ አስፈላጊ ነገር እንድትማሩ ስለፈለኩ ……
ውጭ ያለው ዓለም እንዴት እደሚያስተናግዳቹ ለማወቅ ይህ ለናንተ ትልቅ ትምህርት ይሆናል

ዘጠኝ ትክክል መልሶች እደፃፍኩ አይታቹ አንዳቹም እንኳን ስለዚህ ትኩረት አልሰጣቹም
ግን በአንድ ስህተት ምክንያት ሁላችሁም ሳቃችሁ ተቻቹ…………

ትምህርቱ ምን መሰላቹ እናንተ ለምታደርጉት ሚሊዮን መልካም ነገር ውስጥ ዓለም አንዷ እናንተ የተሳሳታቹትን ነገር ይተችባችዋል ስለዚህ ተስፋ አትቁረጡ!ሁል ጊዜም ከሙገሳውም ፣ ከትችቱም በላይ ተነሱ…………
ወደ ላይ ቀና በሉ !!

╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
150 views03:48
Open / Comment
2021-05-27 06:48:16
133 views03:48
Open / Comment
2021-05-26 15:57:13
"ቀን ያበደ ለታ"

ተፈጥሮ በድንገት፣ዛብ በለቀቀበት፣
በዞረበት ጊዜ፣በዞረባት መሬት፣
ዶሮ ሲያንቀላፋ፣በጓጉንቸር ጩኸት፣
በዘጠኝ ይነጋል፣ቀኑ ያበደ ለት፡፡
ጊዜ ቀስቱ ሲዝል፣ሲረግብ ደጋኑ፣
ቋጠሮው ሲላላ፣የተፈጥሮ ውሉ፣
ሳያልቅ ሌሊቱ፣እንደጭንጋፍ ሁሉ፣
በዘጠኝ ይነጋል፣እብድ ቀን ላመሉ፡፡
ጠብ-በመተቃቀፍ፣
ቁጣ-በፈገግታ፣
ፍቅር-በንክሻ፣
ሰላምታ-በቴስታ፣
ሀዘን-በዳንኪራ፣
ጋብቻ-በዋይታ፣
የሚሆነው ቀርቶ፣
የማይሆን ይሆናል፣ቀን ያበደ ለታ፡፡

{ጌትነት እንየው}


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
174 views12:57
Open / Comment
2021-05-26 06:03:05 ………

"ዶክተር ሱዛን ማኪነን ቀዶ ጥገና ማድረግ ሲያሻት እጇን ወደ አንድ የቀደመ መፅሐፍ ትዘረጋለች፤ በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ የተፃፈ መፅሐፍ።". . .

መፅሐፉ የሰው ልጅ ሰውነትን ልክ እንደ አንድ የኤሌክትሮኒክስ እቃ ከፋፍሎ ያሳያል፤ ከቆዳ ጀምሮ እስከ አጥንት፤ ከጉበት እስከ አንጅት. . .መፅሐፉን ስስ ልብ ያላቸው እንዲያዩት አይመከረም።

መፅሐፉ 'Pernkopf Topographic Anatomy of Man' የተሰኘ ርዕስ አለው። የሰው ልጅ መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥ ተብሎ በግርድፉ ሊተረጎም ይችላል፤ ወይም መልክዓ-ሰዋዊ አቀማመጥ።

ይህን መፅሐፍ የቀዶ-ጥገና ሐኪሞች እንደ ቅዱስ መፅሐፍ ነው የሚያዩት ተብለው ይታማሉ። የሰው ልጅን ውስጣዊ አሠራር ብትንትን አድርጎ የሚያሳየው መፅሐፍ ኤድዋርድ ፐርንኮፕፍ በተሰኘ የኦስትሪያ ሰው የተፃፈ ነው።

መፅሐፉ አሁን ከህትመት ውጭ ቢሆንም ማግኘት ግን ብዙ ድካም አይጠይቅም። በይነ-መረብ ላይ የተለያዩ የመፅሐፉ ዕትሞች ይገኛሉ። ከእርስዎ የሚጠበቀው ትንሽ ሺህ ፓውንዶች (ረብጣ ብር)መያዝ ነው።

መፅሐፉ ያላቸው ሰዎች ግን በኩራት ሼልፋቸው ላይ ወይም ከመስታወት ሥር ሲያስቀምጡት አይታዩም፤ ምክንያቱ ወዲህ ነው። ይህን መፅሐፍ ለመፃፍ የሰው ሕይወት ተከፍሏል-የሺህዎች ሕይወት።

መፅሐፉ ላይ ደም-ሥራቸው፣ አጥንታቸው እና ቆዳቸው እንደ ምስር ተለቅሞ የሚታዩ ሰዎች በናዚ ግፍ የተጨፈጨፉ ናቸው። ሐኪሞች ይህን መፅሐፍ በፍፁም ሊጠቀሙበት አይገባም የሚሉ በርካቶች ናቸው። ምክንያታቸውም 'መፅሐፉ ጥቁር ታሪክ አዝሏልና' ይላሉ።

ዶክተር ሱዛን መፅሐፉን መጠቀሟ ሰላም እንደማይሰጣት ባትክድም ለሥራዋ እጅግ አጋዥ እንደሆነ ግን አትሸሽግም።

ከናዚ የጅምላ ጭፍጨፋ (ሆሎኮስት) የተረፉት የጤና ፕሮፌሰሩ ዮሴፍ ፖላክ 'መፅሐፉ የሞራል ጥያቄ ያለበት ነው' ይላሉ። «የመፅሐፉ ሥረው-ግንድ ሠይጣናዊ ተግባር ቢጠናወተውም አሁን ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው ለበጎ ነው።»

የመፅሐፉ ደራሲ ኤድዋርድ ፐርንኮፕፍ የናዚ ዶክተር ነበር፤ የአዶልፍ ሂትለር ቀንደኛ ደጋፊ። የሥራ ባልደረባዎቹ 'ሶሻሊስት' ሲሉ ይገልፁታል፤ ወደ ሥራ ሲመጣ የናዚ ምልክት ክንዱ ላይ የማይለየው ቀንደኛ ናዚ ነበር። ግለሰቡ በቪዬና ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ትምህርት ክፍል ኃላፊ ሆኖ ሲሾም የሎሪየትነት ሽልማት ያገኙትን ሳይቀር አይሁዶችን መርጦ ጠራርጎ ያባረረ ሰው።

በወቅቱ በናዚ የተገደሉ የአይሁዶች ሬሣ ለሕክምና ትምህርት ወደ ዶክተሩ ይመጡ ነበር። ሰውዬው በቀን 18 ሰዓት የሰውን ልጅ አካል ሲቀድ እና ሲሰፋ፤ ሲከፋፍል ይውላል።

አጋሮቹ ደግሞ ያዩትን በፎቶ እና በስዕል ያስቀራሉ። አንዳንድ ጊዜ ክፍሉ ሙሉ ከመሆኑ የተነሳ ሊገደሉ ተራ የተያዘላቸው አይሁዶች አንድ ቀን ይራዘምላቸው ነበር።

መፅሐፎች የመጀመሪያ ዕትሞች የናዚ ምልክት ያለባቸውና ፊርማ ያረፈባቸው ናቸው። 1964 (በግሪጎሪ አቆጣጠር)እንግሊዝ ውስጥ የታተመው ሁለተኛ ዕትምም ሲሆን የናዚ
ምልክት ፊርማ ሰፍሮበታል።

90ዎቹ ላይ የሕክምና ተማሪዎች መፅሐፉ ላይ ያሉ ሰዎች እነማ ይሆኑ የሚል ጥያቄ ይጫርባቸውና መመርመር ይጀምራሉ። በኋላ ላይ የመፅሐፉ ያለፈ ምስጢር ሲጣራና ሲታወቅ እንዳይታተም እግድ ተጣለበት።

መፅሐፉ በበርካታ ሃገራት ከጥቅም ውጭ እንዲሆን ተደርጓል። በታሪክነት እንዲቀመጥ እንጂ ሐኪሞች እንዲጠቀሙበት አይመከርም። ነገር ግን በቅርቡ የቀዶ ጥገና ሐኪሞች የተሳተፉበት ጥናት ተሠርቶ 59 በመቶ ያህሎቹ መፅሐፉን እንደሚያውቁት ሲናገሩ፤ 13 በመቶዎቹም እንደሚጠቀሙበት ይፋ አድርገዋል።

ዶ/ር ሱዛን የዚህን መዘዘኛ መፅሐፍን ያህል ቅንጣት ታክል እንኳ መረጃ የሚሰጥ ሌላ መፅሐፍ የለም ትላለች። በተለይ ደግሞ ከበድ ያሉ ቀዶ ህክምናዎችን ቀለል የሚያደርግ እንደሆነ ዶክተሯ ትመሰክራለች።

ዶ/ር ሱዛን በአንድ ሰው ላይ የቀዶ ህክምና እያካሄደች ነበረች። እግሩ አካባቢ ጉዳት የደረሰበት ይህ ሰው ትክክለኛው ነርቭ ተገኝቶ ጥገና ካልተደረገለት እግሩ ሊቆረጥ ግድ ነበር። ዶክተሯ ወዲህ ብትል ወዲያ ትክክለኛው ነርቭ ሊገኝ አልቻለም። በስተመጨረሻ ግን እጇን ዘረጋች. . .ወደ መፅሐፉ። የሰውየውም እግሩ ከመቆረጥ ዳነ።

ፐርንኮፕፍ ናዚ ከተሸነፈ በኋላ ለእሥር ቢበቃም ከሦስት ዓመታት በኋላ ተለቀቀ። ምንም ዓይነት ክስ አልተመሠረተበትም ነበር። ሰውዬው ከእሥር ከወጣ በኋላ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ዕትም በማውጣት ቸብችቧል። አራተኛውን ዕትም ሊያወጣ በመዘጋጀት ሳለ ነበር ሞት የቀደመው።

መፅሐፉ ከወጣ 60 ዓመታት ቢያልፉትም አሁንም የሰው ልጅ ሰውነትን ለማጥናት ወደር የማይገኝለት እየተባለ ነው። መፅሐፉን የመጠቀም ተገቢነት ግን አሁንም አከራካሪነቱ ቀጥሏል።

╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
196 views03:03
Open / Comment
2021-05-26 06:02:08
180 views03:02
Open / Comment
2021-05-24 20:28:54
"................ ፍቅር በዓይኑ ጥቅሻ በጠራችሁ ጊዜ መንገዶቹ ምን ያህል አስቸጋሪ እና አቀበት ቢሆኑም ተከተሉት...ክንፎቹ ሲያቅፏችሁም ተሸጎጡበት ። በላባዎቹ መሀል የተደበቁ ሰይፎች ቢያቆስሏችሁም ወደኋላ አታፈግፍጉ ..ሲያነጋግራችሁም እመኑት ። ድምፁ የሰሜን ኃይለኛ ንፋስ የአትክልትን ስፍራ እንደሚያወድም ሁሉ ህልሞቻችሁን ቢበታትንባችሁም እሱን ከማመን አታመንቱ........
ፍቅር ዘውድ የሚደፋላችሁን ያህል ይሰቅላችሁም ይሆናል ። የሚያሳድጋችሁንም ያህል ይከረክማችኋልም...እስከ ጫፍ ከፍ ብሎ በፀሃይ ውስጥ የሚወዛወዙትን እጅግ ለስላሳ ቅርንጫፎቻችሁን በፍቅር እንደሚደባብስ ሁሉ ፣ በመሬት ውስጥ ቁልቁል ወደ ስሮቻችሁ ወርዶም ተጠምጥሞ ከመሰረታቸው ይነቀንቃቸዋል
ፍቅር እነዚህን ሁሉ ነገሮች የሚያደርግባችሁ ፣ የልባችሁን ምስጢራት እንድታውቁ እና በዚያ ዕውቀትም የህይወት ልብ አንድ ግማድ እንድትሆኑ ነው.............
" የጥበብ መንገድ ፪ "
ካህሊል ጂብራን


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
31 views17:28
Open / Comment
2021-05-23 16:37:48 ብታውቋቸው ...........

* ማንም ሳይጠራችሁ ስማችሁ የተጠራ መስሏቹ ያውቃል ........ የህ የጤነኛ አይምሮ ማሳያ ነው ይለናል world fact

* የቻይና አርቴፊሻል ፀሃይ 150 ሚሊዮን ዲግሪ ሰልሸስ ይሞቃል ይሄም ከፀሃይ እንብርት 10 እጥፍ ይሞቃል ማለት ነው

* ውሾች ካንሰርን የማሽተት ችሎታ አላቸው ስለዚህ በዙሪያቹ ያሉ ውሾች አዲስ አመል ካሳዩ ሂዱና ምርመራ አድርጉ

* በ2007 ዓ.ም ጠፈር ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ማርገዝ የቻለችው ፍጥረት በረሮ ናት ስሟም ናድዝሄድ ትባላልች እናም 33 ልጆች ተወልደዋል ጥናቱ እንደሚለው ከተለመዱት በረሮዎች ፈጣን እና ጠንካራ ናቸው ።

* የፃሃይ መጥለቅን በአትላቲክ ውቅያኖስ በኩል አይተን በሌላኛው አቅጣጫ የፀሃይ መውጣትን በፓሲፊክ ውቅያኖስን ላይ ማየት የምችልበት ብቸኛው ቦታ ፓርማ ነው

* ለመጨረሻ ጊዜ ምድር ላይ ሰዎች ባንድ ላይ የኖሩት ሚያዚያ 2 /2000 ዓ.ም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ድረስ ነው ከዛን ጊዜ በኋላ ከምድር ውጪ በስፔስ እስቴሽን ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች አሉ

*የ ኢሎን ማስክ አዲስ ምርምር በራስ ቅል ውስጥ የሚቀበር ቺፕ ነው እሌክትሮይዶቹም አንጎል ውስጥ ይቀበራሉ የቺፑ አገልግሎት የአይን እይታ ችግር ይፈታል እንዲሁም ምንም አይነት የጭንቅላት ችግሮችን ይቀርፋል

* በጥንት ጊዜ የነበረ ልምምድ አለ ''eye gazing'' ተግባሩም ሁለት ሰዎች አይን ለአይን ይፋጠጣሉ ረዘም ላለ ጊዜ ይሆናል የአይን ለአይን መተያየት ከጀመሩ ቡኋላ አንድ የሆነ ልዩ የሆነ ሃይል ይሆናል ይሄም ሃይል በምናየው አይን ውስጥ የሰውየውን ደስታ ፣ ሃዘን ፣ ልማድ ፣ ህልሙን ፣ ያለፈ ህይወቱን ፣ በጣም እሩቅ የሆነውን ቦታ ሳትቀር መመልከት እንችላለን ወደ ጥልቅ ሆነው ምልከታ እንገባለን ''eye are the window to the soul'' የሚለው አባባል ከዚህ ነው የመጣው


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
161 views13:37
Open / Comment
2021-05-23 16:37:43
143 views13:37
Open / Comment