Get Mystery Box with random crypto!

❿ⓉⒽ 🅕🅤🅝 ™

Logo of telegram channel tenthfun — ❿ⓉⒽ 🅕🅤🅝 ™
Logo of telegram channel tenthfun — ❿ⓉⒽ 🅕🅤🅝 ™
Channel address: @tenthfun
Categories: Education
Language: English
Subscribers: 554
Description from channel

➥➥➥➥1.6 k Thanks
➥➥🎀Welcome🎀◀◀◀◀◀◀◀◀◀
Stay positive ➕
Bot comment @TenthfungtBot
⛔️ @thekey4242 CEO OF 10TH FUN CHANNEL

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


The latest Messages 11

2021-07-24 18:32:23 ሰላም ለእናንተ ይሁን

• በተለያዩ ጊዜያት ሃላፊነት ይሰጠናል፡፡ በእዉነቱ ከሆነ 'የማደጎ ራእይ' በራሱ መጥፎ ባይሆንም ከሰዉ ተቀብሎ ለማሳደግ ግን በሳል መሆንን የሚጠይቅ ይመስለኛል፡፡ የሰዉ ልጅ ለሌላ ሰዉ በማደጎነት ይሰጣል...'ይህንን ልጅ አሳድገዉ' ተብሎ

• ሃሳብና ራእይም እንዲሁ ነዉ፤ አባቶቻችን በትንሹም ቢሆን ሲመግቡት የነበረዉን 'የሃሳብ ማደጎ' ለኛ አስረክበዋል፡፡ ጥሩም መጥፎም ሊሆን ይችላል...ቁም ነገሩ የተቀበልነዉ ሃሳብ ጥሩ ከነበረ የበለጠ እንዴት እናፋፋዋለን? እናሳድገዋለን? መጥፎ ከነበረ ደግሞ እንዴት ወደትክክለኛዉ መንገድ ሊመጣ ይችላል ብለን ማሰቡ አይከፋም፡፡

• የሃሳብ ማደጎ ከትዉልድ ትዉልድ ይተላለፋል፡፡ ካለበት ቦታ ሆኜ የተሻለ አሻራ አኑሮ ማለፍ የሚፈልግን ሃሳብ የበለጠ መለወጥ፣ ማስፋት ያስፈልጋል፡፡ በኛ ሀገር የህይወት ሩጫ ዉስጥ ግን ለምን እንደሆነ ባላዉቅም ይህንን ነገር አናገኘዉም፡፡

የሆነ ሃሳብ ወይም ራእይ ከሰዎች በሚሰነዘርብን ሰአት ቶሎ ብለን መጥፎዉን ጎን ማጉላት ይቀለናል፡፡'ይሄማ ፈፅሞ የማይሆን ቅዠት ነዉ...የማይመስል ሃሳብ' ምናምን እያልን እናጣጥላለን፡፡

• ሁላችንም በጊዜና በቦታ ዉስንነት የተገደብን ነን፡፡ ዛሬ ወጣት 'የነብር ጣት' የተባልነዉ ነገ ጉልበታችን ዝሎ ለሚቀጥለዉ ትዉልድ ምንም ነገር ሳናስተላልፍ 'የሃሳብ ቃሪያ የተጠቀጠቀበትን ጉርሻ' አጉርሰን ከምንሄድ ዛሬን ማስተዋሉ መፍትሄ ነዉ፡፡

አለበለዚያ 'እንቆቅልሹን ያልፈታ የትናንሽ ራእዬች ባሪያ' የሆነን ትዉልድ ደጓሚ ሆነን እንቀራለን፡፡

፤ ቸር ያሰማን

Kogoese
588 viewsedited  15:32
Open / Comment
2021-07-22 14:43:19 አንበሳ ቢያጋጥመን ምን እናድርግ?

በጉብኝት ወይም በሌላ አጋጣሚ ከአንበሳ ጋራ የመገናኘት ሁኔታ ሊያጋጥመን ይችላል፤ ምንም እንኳን አናብስት ከሰዎች ራቅ ብሎ የማሳለፍ ሁኔታ ቢኖራቸውም፤ አንዳንዴ ግን ጥቃት ሊሰነዝሩብን ችላላሉ፤ በመሆኑም ቢያንስ ምን ማድረግ እንዳለብን ማወቅ አለብን፡፡ ከዚህ በታች የተጠቀሱት በባለሙያተኞች የሚገለፁ የጥንቃቄ እርምጃዎች ናቸው፡፡

አንበሳ ቢያጋጥመን በፍፁም መሮጥ የለብንም ፤ ማድረግ ያለብን እኛም ለሱ ስጋት ልንሆን እንደምንችል ማሳየትን ነው፡፡ ለምሳሌ በማጨብጨብ እና በመጮህ ሊሆን ይችላል እኛም ቁጡና አደገኛ እንደሆንን ማንፀባረቅ አለብን፤ ይህ ባሕሪ በአራዊቶች ውስጥ የተለመደ ራስን ማስጠበቂያ መንገድ ነው፡፡

ፊትን ወደ አንበሳው አዞሮ ቀስ እያሉ ወደ ኋላ በመራመድ ማፈግፈግ።
ጀርባችንን ለአንበሳው ማዞር የለብንም፤ ፊትለፊት ተጋፍጠነው ወደ ኋላ ማፈግፈግ የተሻለ ውጤት አለው፤ ልዩነታችን እየሰፋ ከሄደ ችላ ስለሚሉን ጥቃት ላይደርስብን ይችላል፡፡ ከአንበሳው እየሸሸን ስንራመድ አሁንም እያጉረመረመ ተንደርድርሮ መጥቶ ሊያጠቃን ይችላል፤ በመሆኑም በመጮህ የያዝነው እቃ ካለ በእጃችን ከፍ በማድረግ እኛም ልንጎዳው እንደምንችል ፍንጭ መስጠት አለብን፤ ስንጮህ ያለ አቅማችንን ተጠቅመን መሆን አለበት፡፡ ይህንን ስናደርግ ጥለውን ከሄዱ ወከባችንን በማቆም አፈግፍገን ማምለጥ አለብን፡፡

የምንሞክራቸውን ጥረቶች በሙሉ አልፎ ሊያጠቃን ከመጣ፣ ቀጥ ብለን እንደቆምን ልንጠብቀው ይገባል፤ አንበሳ ጥቃት ሊያደርስብን የሚሞክረው በፊታችን ወይም በጉሮሯችን ላይ ነው፤ ይህም ማለት ዘሎ የሚመጣው ወደ ፊታችን ነው፤ አንበሳው ዘሎ ሲመጣ በተቻለንን አቅም በ እጃችን አይኑን መጠንቆል ያስፈልጋል። የ አንበሳ አቅም ከሰው ጋር የሚመጣጠን ባይሆንም አይናቸውን ከተመቱ ይሸሻሉ
440 views11:43
Open / Comment
2021-07-21 05:18:53 የሁሉም ነገር መነሻ

ህይወትህን የሚቀይረው በየቀኑ የምታደርጋቸው ድርጊቶች ናቸው። ከሱ በፊት ግን....

ድርጊቶችህን የሚቆጣጠራቸው ደግሞ ስሜትህ ነው፤ ጥሩ ስሜት ላይ ስትሆን ጥሩ ትሰራለህ ካልሆንክ ደግሞ በተቃራኒው። ከሱ በፊት ግን....

ስሜትህን የሚቆጣጠረው ደግሞ ሀሳብህ ነው፤ ስለዚህ ወዳጄ ለምታስበው አስብ! ምክንያቱም የማንነትህ አለቃ እሱ ነው።
653 views02:18
Open / Comment
2021-07-20 11:55:10
ᴀɴɪᴍᴀʟ ᴛᴀʟᴋ ᴛɪᴍᴇ!!!!!!
#ሀምስተር

- ሀምስተሮች የሚመገቡት የለወዝ እና የተለያዩ ፍሬዎችን ነው

- እነዚህ ሀምስተር የተባሉ የአይጥ ዝርያዎች ለየት የሚያደርጋቸው ልክ ወደፊት በሚሮጡበት ፍጥነት ወደ ኋላ መሮጥ መቻላቸው ነው።

- ሀምስተሮች በ እባብ እና በ ጉጉቶች ይበላሉ

- ክብደታቸው እስከ 900 ግራም ይደርሳል

-የተለያየ ቀለም ያላቸው ሀምስተሮች አሉ

- ሀምስተሮች በጣም ሲደነግጡ ይናከሳሉ

- የጥርሳቸው እድገት አይቋረጥም ግን ሁሌም አጭር ነው ምክንያቱም የተለያዩ ነገሮችን ስለሚፈረፍሩበት ጥርሳቸው ይሸረሸራል።

- ፈረንጆች ይቺን ሀምስተር እንደ ቤት እንስሳ ያሳድጓታል።

- በ አንድ ሳጥን ውስጥ ከ 1 በላይ ሀምስተር ማስቀመጥ የተከለከለ ነው ምክንያቱም እርስ በእርስ ይነካከሳሉ

- በአለማችን ጫካዎች ውስጥ የሚገኙ ሀምስተሮች ብዛት 57 ሚሊዮን ሲሆን ሰው የሚያሳድጋቸው ደግሞ ወደ 11 ሚሊዮን ይጠጋሉ

- 1 ሀምስተር ከ 15 እስከ 20 ዶላር ይሸጣሉ

ᴛʜᴀɴᴋs ᴀɴɪᴍᴀʟᴡᴏʀʟᴅ
725 views08:55
Open / Comment
2021-07-20 11:46:22 ፡።፣፤፥፦፧፨፧፧፦፥፥፤፤፣፣።፡።፥፦፧፨፨፦፤፣።።።፣፥፦፧፧
"ሁሉም ሰው ጂኒየስ ነው፤ ግን አሳ ከዛፍ ዛፍ በመዝለል ችሎታው ከተመዘነ እድሜ ልኩን የማይረባ እንደሆነ ያምናል" ይለናል አልበርት አንስታይን።

ድክመታችንን ከሌሎች ጥንካሬ ጋር ካወዳደርነውማ ሁሌም የበታችነት ይሰማናል፤ ከሌሎች ዝቅ ያልን ይመስለናል። እኛን የሚዳኘን የራሳችን መስፈርት ነው፤ የሌሎች መንገድማ የሌሎች ነው!

በደስታ የተሞላ ማክሰኞ ተመኘንላችሁ
Kogoese
799 views08:46
Open / Comment
2021-07-19 19:30:06 ❿ⓉⒽ 🅕🅤🅝 pinned «sᴘᴇᴄɪᴀʟ ᴀɴɴᴏᴜᴄᴇᴍᴇɴᴛ ᴡᴇ ᴡɪʟʟ ᴏᴘᴇɴ ɴᴇᴡ ɢʀᴏᴜᴘ !! አዲስ ግሩፕ ከፍተናል ስለዚህ አሁን እየሄደችሁ ᴊᴏɪɴ ,ᴀᴅᴅ ብታደረጉ ደስ ይለናል !! ብዙ አስዝናኝ ብዙ ብዙ ይኖራሉ Join @tenthfungt»
16:30
Open / Comment
2021-07-19 19:15:41 sᴘᴇᴄɪᴀʟ ᴀɴɴᴏᴜᴄᴇᴍᴇɴᴛ ᴡᴇ ᴡɪʟʟ ᴏᴘᴇɴ ɴᴇᴡ ɢʀᴏᴜᴘ !!
አዲስ ግሩፕ ከፍተናል ስለዚህ አሁን እየሄደችሁ ᴊᴏɪɴ ,ᴀᴅᴅ ብታደረጉ ደስ ይለናል !!
ብዙ አስዝናኝ ብዙ ብዙ ይኖራሉ
Join
@tenthfungt
52 viewsedited  16:15
Open / Comment
2021-07-19 19:04:50 ❿ⓉⒽ 🅕🅤🅝 pinned a photo
16:04
Open / Comment
2021-07-19 19:04:38
እንኳን ለኢድ አል አደሀ አረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
58 views16:04
Open / Comment
2021-07-18 06:17:37 ህይወት ላንተ ምንድነች ምን ብለህ ታስባለህ/ታስቢያለሽ ?

ጦርነት ነች እንደዛ ከሆነ ሁሌ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነህ ሁሌ ማምለጥ ያምርሃል ትሸሸጋለህ።

መድረክ ነች ሁሌ ራስህን ለማሳየት ነው የምትፈልገው ጠንቃቃ ነህ ።

ውድድር ነች ሰላምህን ታጣለህ ሌሎችን ለመብለጥ ስታስብ አብሮህ ያለን ሰውም ታስከፋለህ የሚበቃህ አይመሥልህም ለሁሉም።

ስጦታ ነች ሁሌም ደስተኛ ነህ ያለህን ታመሠግናለህ።

አለም ትልቅ ቤተሰብ ናት በሌሎች ስኬት ትደሰታለህ ለሰውም ታስባለህ።

የትኛውን ነህ ? ላንተ ህይወት ምንድናት ?

kogoese
35 views03:17
Open / Comment