2021-05-03 19:40:24
ካነበብኩት ላካፍላችሁ
ይህ ያስተምራችኋል ብዬ ስላሰብኩ እንዲህ አሰናድቼ አቀረብኩላችሁ.... ..............!!!
አንድ በስቃይ የተሞላ ህይወትን የሚመራ ሰው ነበር። ሰውየው ወደ አምላኩ በሚፀልይበት ወቅት "ሁሉም ሰው ደስተኛ ሆኖ ለምን እኔ ብቻ እሰቃያለሁ? ለምን እኔ ብቻ?" ይል ነበር።
አንድ ቀን ጥልቅ በሆነ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ሆኖ ለአምላኩ ጸለየ። "አምላኬ የማንኛውም ሰው ስቃይ ብትሰጠኝ ልቀበልህ ዝግጁ ነኝ። እባክህ! እባክህ ጌታዬ የእኔን ግን ውሰድልኝ። ከዚህ በላይ ልሸከመው አልችልም" ሲል ተማጸነ።
ጸሎቱን ጨርሶ እንደተኛ ውብ የሆነ ህልም አየ። በህልሙ አምላክ ሰማይ ላይ ተከሰተና እንዲህ ሲል ተናገረ። "ስቃያችሁን ሁሉ ወደ ቤተ መቅደስ አምጡ።"
እያንዳንዱ ሰው የየራሱ ስቃይ የታከተው ስለነበር በተለያዩ ወቅቶች "የማንኛውም ሰው ስቃይ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ። የእኔን ግን ውሰድልኝ። ከዚህ በላይ መሸከም አልችልም " ብሎ ይጸልይ ነበር።
እንደተባለው ሁሉም ሰው ስቃዩን በቦርሳው አጭቆ ወደ ቤተ መቅደሱ አመራ። ባለታሪኩን ጨምሮ ሁሉም ሰው ጸሎቱ አምላኩ ዘንድ ተቀባይነት ስላገኘ በስፍራው ላይ ከፍተኛ የደስታ ስሜት ነገሰ።
ሁሉም ሰው ከቤተ መቅደሱ ሲደርስ አምላክ እንዲህ ሲል አወጀ። "ቦርሳችሁን ከግድግዳው ስር አስቀምጡ"
ሁሉም ሰው ቦርሳውን አስቀምጦ ከጨረሰ በኋላ አምላክ እንዲህ ሲል በድጋሚ አወጀ። "አሁን መምረጥ ትችላላችሁ ማንም ሰው የፈለገውን ቦርሳ መውሰድ ይችላል።"
በጣም አስገራሚው ነገር ቀን ከሌት ሲጸልይ የነበረው ሰውዬ ሌላ ሰው ቦርሳውን እንዳያነሳበት እየተጣደፈ ወደ ቦርሳው ሮጠ ሁሉም ሰው አንደ ሰውየው የነራሱን ስቃይ ያጨቀበትን ቦርሳ ፍለጋ ተራወጠ። እያንዳንዱ ሰው የየራሱን ስቃይ ለመሸከም ዝግጁ ነበር።
ምንድን ነበር የተከሰተው?
በህይወታቸው ለመጀመሪያ ጊዜ አንዳቸው የሌላቸውን ችግር ስቃይና መከራ ተመለከቱ። እንደውም እራሳቸው ከያዙት ቦርሳዎች የሚበላልጡ የሌሎች ሰዎች በስቃይ የታጨቁ ትልልቅ ቦርሳዎች እንዳሉ ተገነዘቡ በተጨማሪ ሁሉም ሰው ከራሱ ስቃይና መከራ ጋር ተላምዷል። የራሱን ስቃይ ማባበል እና መቻል ይችላል። የሌላውን የመከራ ቦርሳ ቢወስድ ግን ከቦርሳው ውስጥ ያለው አዲስ አይነት መከራ ምን አይነት እንደሆነ አያውቅም። ምናልባት የባሰም ሊሆን ይችላል።
አላሚው ሰው ከእንቅልፉ ሲነቃ በድጋሚ ጸለየ። "አምላኬ ስላሳየኸኝ ህልም አመሰግናለሁ። ከዚህ በኋላ እንዲህ አይነቱን ጥያቄ ደግሜ አልጠይቅም። የሰጠኸኝን ነገር ሁሉ የሰጠኸኝ ለበጎ ነው። ለዛም ነው የሰጠኸኝ።"
Re.. 🄿🄾🅂🅃... 🅸🆃!
1.5K viewsᴢᴇᴋɪ 10ᴇ, 16:40