2021-05-17 14:03:38
ብሎብ ፊሽ(blob fish)
- ብሎብ የተባሉት የ አሳ ዝርያዎች በ አለማችን ካሉት የ አሳ ዝርያዎች መሀል ቁጥር 1 አስጠሊታ መልክ ያላቸው አሳዎች በመባል ይታወቃnሉ።
የሚኖሩትም በ አውስትራሊያ ውቂያኖስ ታችኛው ክፍል ላይ ነው
አሳዎች ሞተው የ ውቂያኖሱ መሬት ላይ ሲወድቁ ብሎቦች የወደቀውን ሬሳ ይመገባሉ።
- ብሎብ ፊሽ በህይወት ዘመናቸው ምንም የሚያስጨንቃቸው ነገር የለም ምክንያቱም እታች ድረስ ወርዶ የሚያጠቃቸው እንስሳ የለም እንዲሁም ምግብ ሳያድኑ አፋቸውን ብቻ ከፍተው ከላይ የሚወርድላቸውን ሬሳ እየተመገቡ ነው የሚኖሩት።
አሁን አሁን ግን የሰው ልጅ ውቂያኖስ ላይ የሚጥላቸው ቆሻሻዎች ወደውስጥ ሲሰምጡ ብሎብ ፊሾች የሞተ አሳ መስሏቸው በመመገብ ህይወታቸውን እያጡ እንደሆነ ተነግሯል።
ፎቶግራፈሮች እነዚህን አሳ ውሀ ውስጥ ለማንሳት ይቸገራሉ ምክንያቱም ጥልቅ ውቅያኖስ ውስጥ ብርሀን መደረስ አይችልም። ስለዚህ አሳዎቹን ከውሀ ውስጥ በማውጣት ነው ጥሩ ፎቶ የሚያነሱት።
ብሎቦች በ አንድ ጊዜ ከ 1 ሺህ በላይ እንቁላሎች ይጥላሉ።
from Colombia Daily Tribune
50 viewsRediet M 10A, 11:03