Get Mystery Box with random crypto!

❿ⓉⒽ 🅕🅤🅝 ™

Logo of telegram channel tenthfun — ❿ⓉⒽ 🅕🅤🅝 ™
Logo of telegram channel tenthfun — ❿ⓉⒽ 🅕🅤🅝 ™
Channel address: @tenthfun
Categories: Education
Language: English
Subscribers: 554
Description from channel

➥➥➥➥1.6 k Thanks
➥➥🎀Welcome🎀◀◀◀◀◀◀◀◀◀
Stay positive ➕
Bot comment @TenthfungtBot
⛔️ @thekey4242 CEO OF 10TH FUN CHANNEL

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


The latest Messages 21

2021-06-21 09:40:40 የ 70 አመት እድሜ ያላቸው ሽማግሌ መንገድ በማቋረጥ ላይ ሳሉ አንዲት መኪና እያበረረች መጥታ አጠገባቸው "ሲጢጢጢጢ" ብላ ቆማች. ሽማግሌውም በመኪናዋ ከመገጨት ለጥቂት ተረፉ መኪናዋን
እየነዳች የነበረችዋ ሹፌርም በጣም ተናዳ ከመኪናዋ በመውረድ
"ለምንድነው እያዩ የምይሄዱት?" አለቻቸው
.
ሽማግሌውም "ኸረ ልጄ ስህተቱ እኮ ያንቺው ነው። .
ሴትየዋም፦ስሙ አባቴ እኔ መኪና በማሽከርከር የ 15 አመት ልምድ ያለኝ ሰው ነኝ"
.

ሽማግሌውም.....
.
.
.
.
..
.
"ኸረ ልጄ እኔም በእግሬ በመጓዝ የ 70 አመት ልምድ ያለኝ ሰው ነኝ።

ቅድሚያ ለእግረኛ እንስጥ ረጋ አድርጋችሁ ንዱ።
እስኪ እግረኞች
ባለጎማዎች

~~~~☞ zeganeenazege ~~~~
98 viewsᴢᴇᴋɪ 10ᴇ, 06:40
Open / Comment
2021-06-19 09:10:10 ሰላም ለእናንተ ይሁን

• ሰዉ በነገሮች መሳካትና አለመሳካት ላይ በሚያደርጋቸዉ መስተጋብሮች ሃሳቡ፣ ህልሙ ወይ ይሳካለታል አለበለዚያ ይከሽፍበታል፡፡ በህይወትህ ዉስጥ በምትኖረዉ የተገደበ ጉዞ እያንዳንዷን ዉሳኔህን እንደ ብስለትህ መጠን ትተገብራቸዋለህ፡፡

• አእምሮህ ከምንም በላይ የተሳለና 'ግራና ቀኝ' አስተሳሰብን ያዳበረ እንዲሆን ሁልጊዜ ኮትኩተዉ፣ መግበዉ፣ አሳድገዉ፡፡

• በእድሜ ብዛት ወይም በሃብት ከፍታ አእምሮህ ሊያድግ አይችልም፡፡ ይልቁንስ በየቀኑ የምትሰማዉ፣ የምታዳምጠዉና የምታሰላስለዉ ነገር ዛሬህን እየቀረፀ የነገዉን አንተነትህን ያሳይሃል፡፡

• ብስለት መፅሃፎችን በማንበብ፣ ከሰዎች ጋር አብረህ በማሳለፍ፣ በህይወትህ ከሚገጥሙህ ችግሮች፣ ከህብረተሰቡ ደስታና ሃዘን ወዘተ.ልትቀስማቸዉ የምትችላቸዉ ናቸዉ፡፡

• ብስለት ባገኙት አጋጣሚና ቦታ ሁሉ ማዉራት ሳይሆን፣ ጆሮን ከፍቶ የሰዎችን ሃሳብ በመገንዘብና ጠቃሚ የሆኑትን በመለየት የሚዳብር ነዉ፡፡

• ሰዎችን በአለባበሳቸዉና በዘመናዊ ስታይላቸዉ 'የበሰሉ' እንደሆኑ ልትገምት አይገባም፡፡ እኔም ሆንኩ አንተ የተለያየ ባህሪ፣ እምነት፣ ቋንቋ ወዘተ...ሊኖረን ይችላል ግን ሃሳብህ በኣካባቢህ ላሉት ወሳኝ ነዉ ብዬ ካመንኩ በትዉልድ መካከል አስፈላጊዉ ጉዳይ ሃሳብህ ነዉ፡፡

• ትዉልዶች በአንድ ላይ በሚኖሩባት በኛ ሀገር ፣ሰዎች ከተለያዩ የህይወት መስመሮቻቸዉ ተነስተዉ የበሰሉ እንደሆኑ ከነሱ ትዉልድ በኋላ የመጣዉ ግን ነገሮችን እንዳበለሻሸ ሲናገሩ ትሰማለህ፡፡ ይሄ የኛ የሃበሾች ትልቁ ችግራችን ነዉ ብዬ አስባለሁ፡፡

• የበሰለ ሰዉ በበዛ ቁጥር የበሰለ ትዉልድን ያፈራል፤ያ የበሰለ ትዉልድ ደግሞ ከጊዜያዊ ጥቅምና ጉራ ባለፈ ነገን የሚናፍቅ አዲስና ብርቱን ትዉልድ ይፈጥራል፡፡

• እራስህን ከትንሹ እስከትልቁ ዉሳኔ እንዴት መብሰል እንዳለብህና ጠቃሚዉ ጎን የቱ እንደሆነ እየለየህ አስተምረዉ፣ ገስፀዉ፣ መንገድ ምራዉ፣ አሳርፈዉ፣ አስኪደዉ፡፡ በል ይመችህ! ይመችሽ!

ቸር ያሰማን

kogoese
241 viewsᴢᴇᴋɪ 10ᴇ, 06:10
Open / Comment
2021-06-17 08:28:13 እናትነት ².⁸k

እናትነት የሚጀመረው ነፍስ በሆዷ ውስጥ ካበቀለችበት ቀን ጀምሮ አይደለም......እናት መሆን የሚጀመረው ልክ 9ወር ሙሉ በሆዷ ተሸክማ ወደዚህ አለም ልታመጣው እእ.........ብላ ከምታምጥበ exት ቀን ጀምሮ ነው። 9ወር ሙሉ በሆዷ ስታስቀምጠው እያንዷንዷን ቀን ልጇን በእጇ ምትታቀፍበትን ቀን በጉጉት ትጠብቀዋለች። በእያንዳንዱ ደቂቃ ስለልጇ ጤንነት....ስለ ልጇ ትንንሽዬ እጆች....ስለ ልጇ አስተዳደግ ታስባለች...ትልቅ የስቃይ ሰዓታትን አሳልፋ.....ደሟን አፍስሳ......''እናት'' ለሚባለው ክብር ትበቃለች።
እናትነት እንዲህ ነው:-

....ልክ በእጆቿ አቅፋ እነዛን ትንንሽዬ እጆች እየነካቻቸው ጡት ስታጠባው
....ከዛም እነዛ የሚያማምሩ ትንንሽዬ ጣቶቹ ደረቷን ሲነካት
....በራሷ ጉያ ውስጥ ታቅፋ እሹሩሩ ብላ ስታስተኛው
....ከዛም ከፍ ሲል በእጁም በእግሩም ዳዴ ማለት እየጀመረ ሲጫወት
....እየጠነከረ ሲመጣ መራመድን በነዛ በትንንሽዬ እግሮቹ መንገድ እየሳተ ትንሽ እየተወላገደ በኋላም ላይ መራመድን ሲችል
....ትንሽ ከፍ ብሎም በዛ ማር በሆነ አንደበቱ እማዬ እማ እያለ ሲጠራት
....ት/ቤት ገብቶም እኔ መሆን ምፈልገው ብሎ የመጀመሪያ ምኞቱን ሲነግራ
....ከዛም ከፍ ብሎ ምኞቱን ሊያሳካ ሲጥር እናትም ስታግዘው
....ከዛም ከፍ ብሎላት የልጅነት ምኞቱን አሳክቶ ተመሮቆ ስራ ይዞ እናትም በልጇ ስትደሰት
....ከዛም ከፍ ብሎ ለወግ ለማዕረግ በቅቶላት የሚፈልገው ስኬት ላይ ደርሶ የራሱን ቤተሰብ መስርቶ አያት የሚባለውን ማዕረግ ሲሰጣት
.......አነዚህ ሁሉ ሂደቶች ውስጥ <<እናትነት>> አለ ትልቅ ልጅ ሆኖላት እንኳን እንቅፋት ቢመታው ''እኔን ልጄ'' ትለዋለች።

እናትነት ልጅ ከወለደችበት ቀን ነው የሚጀመረው....አው....ሴት ልጅ በነዛ 7 ወይም 8 ቀናት ውስጥ ደም እየፈሰሳት እያመማት ''እናት'' የምትሆንበትን ቀን ትጠብቃች እነዛ የህመሟ ቀናቶች አልፈው ወደፊት ''እናት'' እንደምትሆን ይነግራታል......ሴት ልጅ 9 ወር በሆዷ ልጇን ስትሸከም ደከመኝ፣ ከበደኝ፣ አሳመመኝ ሳትል ታግሳ ያቺን ቀን ናፍቃ ልጇን በስቃይ ትወልደዋለች....... 6ወር ኧረ ከዛም በላይ ጡቴ ደረቀብኝ፣ ነከሰኝ ሳትል ሳትሰስት በጡቷ ትመግበዋለች.... ልጇን እንዲመቸው በጀርባዋ አዝላ እሹሩሩ እያለች ታስተኛዋለች.....ሳዝለው ወገቤን አመመኝ፣ እሹሩሩ ስለው ጉሮሮዬ ደረቀ ሳትል ህመም ቢሰማት እንኳን ችላ አልፋ የራሷን ኑሮ ትታ ለልጇ ትኖራለች.... በሱ ሳቅ የምትስቀው....በሱ ለቅሶ የምታለቅሰው....ልጇ ሰው ስለሆነ ብቻ አይደለም ''እናት'' ስለሆነች ነው.... አው እናት እንዲህ ናት....ታድያ እናት መሆን መታደል አይደል?

StEpHeN17
98 viewsᴢᴇᴋɪ 10ᴇ, 05:28
Open / Comment
2021-06-17 08:26:51 ካነበብኩት ትንሽ ላጋራቹ ¹.⁸k

ንስር ቁራ

ታላቁን ንሥር አሞራ (Eagle) የሚደፍረው ቁራ ብቻ ነው። ቁራ በንሥሩ ጀርባ ላይ ይቀመጥና ማጅራቱን ደጋግሞ በሹል መንቁሮቹ ይነክሰዋል።

ንሥሩ የቁራው ንክሻ ቢያሳምመውም ከቁራው ጋር በመታገል ጊዜውንና ጉልበቱን አያባክንም። ንሥሩ ክንፎቹን ዘርግቶ ወደ ላይ ከፍ ከፍ ከፍ እያለ ይበራል። በቃ ከፍታውን እየጨመረ ወደ ሰማይ ያሻቅባል። ንሥሩ ከፍታውን በጨመረ ቁጥር ቁራው የመተንፈስ ችግር ያጋጥመዋል።

በመጨረሻም ቁራው በሚያጋጥመው #የኦክስጅን_እጥረት ይሞትና ሬሳ ሆኖ ወደ መሬት ይወድቃል።

ዝም ብለህ ወደ ላይ ወደ ከፍታህ ውጣ። ቁራዎቹ ከአቅማቸው በላይ መሄድ ስለማይችሉ ተመልሰው ይወድቃሉ።

በተስፋዬ ሃ/ማርያም
170 viewsᴢᴇᴋɪ 10ᴇ, 05:26
Open / Comment
2021-06-15 09:41:18 ሰላም ለእናንተ ይሁን

አንድ ሀብታም ሰው ዘመናዊ መኪናውን አቁሞ ለጉዳዩ ገባ ይላል ጉዳዩን ጨርሶ ወደ መኪናው ሲመለስ የአንዱ ጎማው 4 ብሎኖች ተፈተው ተወስዶበት ያያል፡፡ ይህኔ ይበሳጭ እና አከባቢው ላይ ዞር ዞር ብሎ ብሎን ፈልጎ ያጣል፡፡

ያኔ መኪናውን ተደግፎ በጭንቀት ቆዝሞ ሳለ አከባቢው ላይ ያለ አንድ እብድ ነገሩን ተከታትሎ ኖራልና "ምን ሆነህ ነው?" ይለዋል፡፡ ሰውየውም በንቀት አይን አየት እያደረገው "የጎማዬ ብሎኖች ተፈተው ተወስዶብኝ ነው እንዳልገዛ አከባቢው ላይ የለም" ይለዋል በብስጭት ስሜት ውስጥ ሆኖ፡፡

ይህኔ እብዱ "ነው እንዴ? ታዲያ ለምን ከ3 ጎማዎች አንድ አንድ ብሎን ፈተህ አራተኛውን ጎማ አታስርም" አለው፡፡

ሰውየውም በመገረም ሀሳቡ በጣም አስደሰተውና አንዳለውም አደረገ፡፡

"ቆይ አንተ እብድ አይደለህ እንዴ! አንዴት ይህ ሀሳብ ሊመጣልህ ቻለ?" ብሎ ጠየቀው፡፡

እብዱም ቀበል አድርጎ "ታዲያ እኔ እብድ ነኝ እንጂ ደደብ አይደለሁም" ብሎ ይመልስለታል፡፡

ዝቅ በል፤ ዝቅ ስትል ከፍ ትላለህ፤ ተናነስ፤ ራስህን አትቆልል፤ ሁሌም እኔ አዋቂነኝ አትበል።
,10th fun ✓

kogoese
368 viewsᴢᴇᴋɪ 10ᴇ, 06:41
Open / Comment
2021-06-15 09:20:32 #fun4
ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነህ የድሮ ፊዚክስ አስተማሪህ ተከሳሽ ሆኖ ሲመጣ...

እስኪ Newton's first law ከኔ Law
በልጦ ካዳነህ እናያለን

zeganeenazege
10th fun ✓
286 viewsᴢᴇᴋɪ 10ᴇ, 06:20
Open / Comment
2021-06-14 14:52:25
የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን የስራ ጉብኝት ላይ እያሉ በጥፊ ተመቱ።

ፕሬዚደንቱ በደቡብ ምስራቅ ፈረንሳይ #ደሮም_ከተማ ጉብኝት በማድረግ ላይ እያሉ ነው በጥፊ የተመቱት። gossip

ማክሮን በተከለለ አጥር ውስጥ የነበሩ ሰዎችን ሰላም ለማለት ጠጋ ሲሉ ነው ክስተቱ የተፈፀመው።

ፕሬዚዳንቱ በጥፊ ሲመቱ “ Down with Macron-ism ” የሚሉ ቃላት ይሰሙ ነበር።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ሁለት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፈረንሳይ ዜና አውታሮች ዘግበዋል።
662 viewsᴢᴇᴋɪ 10ᴇ, edited  11:52
Open / Comment
2021-06-14 06:23:19 #fun3
ልጅ ተምሮ ት/ቤት እንደተመዘገበ ክላስ የጀመረ ሳምንት

ልጆ ፡- አባ ማትስ ቲቸራችን አልተመቸኝም
አባት፡-ለምን?
ልጅ ፡-በቃ የሆነ ግራ የገባው ነገር ነው
አባት፡-እንዴት?
ልጅ፡-ከትላንትና ወድያ 1+8=9 ነው አለን፡፡ ትላንትና ደሞ 2+7=9 ነው አለን፡፡
ዛሬ ደሞ 3+6=9 ነው። አይለንም መሰለህ, አስበው እስቲ?
አባት፡ ድሮውንም እኮ እዛ ትምህርት ቤት ስትገባ ደስ አላለኝም ነበር::
እነሱ ገንዘባቸውን ካገኙ ለ ትምህርቱ መች ይጨነቃሉ! ሌቦች
zeganeenazege
792 viewsᴢᴇᴋɪ 10ᴇ, edited  03:23
Open / Comment
2021-06-14 06:21:18 ሰላም ለእናንተ ይሁን

"• አንዳንድ ቀን የምንፈልገዉን እናገኛለን ወይም አናገኝም ወይም ደግሞ ከዛ በላይ የሚበልጥ ነገር እናገኛለን፡፡

• ያለህ ብቸኛ ነገር እራስህ ብቻ ብትሆንስ? ያ ብቸኛ ነገር ላንተ በቂ ቢሆንስ?

• እራስህን በአዲስ መልክ ለመስራት አትፍራ!

• ድንገት ተነስተህ ቢራቢሮ አልሆንክም፤እድገት ሂደት ነዉና!

• ይገለኛል ያልሽዉን ነገር አሸንፈሽ በህይወት አለሽ፡፡ስለዚህ ዘዉድሽን አስተካክለሽ ልክ እንደንግስት ወደፊት ተራመጂ!

• ህይወት አጭር ናት፤ ጉዞ አድርግ ፣ ጫማ ግዛ ፣ በወጣትነት ሚስትህ ደስ ይበልህ፣ ኬክ ብላ ጣፋጭ ነገር ካልተስማማህ ወደ ሸንኮራ ቀይረው !

• አንቺ ማለት ብዙዎቹ ሴቶች በህልማቸዉ እንኳን ቢደርስባቸዉ የማይችሉትን ፈተና ያለፍሽ ጠንካራ ሴት ነሽ፡፡ መቼም ቢሆን ይህንን እንዳትረሺ!

• ሰዎች ፅጌረዳን እሾሃም ወይም ዉብ ቢሏት አይበርዳት አይሞቃት!

• የሆነ ሰዉ አበባ እንዲያመጣልሽ አትጠብቂ፡፡የራስሽን አትክልት ተክለሽ ነፍስሽን አስዉቢያት!

• ህልምህ ኤክስፓየር ቀን የለዉም ስለዚህ ትንፋሽህን ስበህ እንደገና ሞክር!

•ከሁሉም በፊት ግን ብዙዎች ሊደርሱበት አቅደው ፣ ሊያዩት ተመኝተው ፣ ሊያጣጥሙት ጓጉተው ነገር ግን ሳይደርሱበት ከቀሩት ዛሬ ላይ አንተ እንድትገኝ ስለተፈቀደልክ ፈጣሪክን አመስግነው

ቸር ያሰማን

kogoese
1.2K viewsᴢᴇᴋɪ 10ᴇ, 03:21
Open / Comment
2021-06-13 01:13:54
Thanks for supporting ,:-):-):-):-):-):-)

1K......
58 viewsᴢᴇᴋɪ 10ᴇ, 22:13
Open / Comment