Get Mystery Box with random crypto!

❿ⓉⒽ 🅕🅤🅝 ™

Logo of telegram channel tenthfun — ❿ⓉⒽ 🅕🅤🅝 ™
Logo of telegram channel tenthfun — ❿ⓉⒽ 🅕🅤🅝 ™
Channel address: @tenthfun
Categories: Education
Language: English
Subscribers: 554
Description from channel

➥➥➥➥1.6 k Thanks
➥➥🎀Welcome🎀◀◀◀◀◀◀◀◀◀
Stay positive ➕
Bot comment @TenthfungtBot
⛔️ @thekey4242 CEO OF 10TH FUN CHANNEL

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


The latest Messages 29

2021-04-28 17:53:26 Quiz ' ➥➥ʟᴇᴛ ᴋɴᴏᴡ ᴏᴜʀ sᴇʟғ '
መነሻ ጥቅስ የስሜት ብልህነት ከአእምሮ ብቃት ይበልጣል። የትኑም ያህል እውቀትህ ቢበዛ፣ አእምሮህ ቢፈጥን የስሜት ብልህነት ከለለህ ምንም የለህም። "የሰውን ችግር እንደራስ ማየት" አንዱ የስሜት ብልህነት መገለጫ ነው።
6 questions · 10 sec
186 viewspeace, 14:53
Open / Comment
2021-04-28 11:21:54 ሰዎች እኮ በችግር ውስጥ ሆነህ መፍትሔ ይሰጡኛል ብለህ ስትጠብቅ እነሱ ግን ስለ ውስጥ ሀዘንህ ሳይሆን ደረትህ ላይ ሳላለው ንቅሳት ያወራሉ ስለ ልብህ ህመም ሳይሆነ ስለ ውጫዊ ሰውነትህ ይጨነቃሉ ስለ እንባህ ሳይሆን ስለ አይንህ ማማር ያወራሉ ስለ ለቅሶህ ሳይሆን የሳቅህ ውበትና ፣ የጥርስህ ንጣት ያስጨንቃቸዋል። በቃ አንዳንድ ሰዎች እንዲ ናቸው። ዘንጠህና ፈገግ ብለህ ሲያዩህ ምንም ችግር የሌለብል ይመስላቸዋል። ከንቅሳትህ ጀርባ ያለውን ቁስል ፣ ከሳቅህ ጀርባ ያለውን እንባ፣ ከፈገግታህ ጀርባ ያለውን ሀዘን ከራስህ በቀር ማንም ሰው አይረዳልህም።
⓾𝕥𝕙 𝕗𝕦𝕟 𝕥𝕙𝕖 𝕣𝕚𝕘𝕥𝕙 𝕨𝕒𝕪 𝕗𝕦𝕟
Amazingtruth
1.2K viewsᴢᴇᴋɪ 10ᴇ, 08:21
Open / Comment
2021-04-27 18:21:14 የልጅነት ትዝታዎቼ



አያቴ ሰላም ያዋልከን ሰላም አሳድረን ብላ መብራት ስታጠፍ የምድራችንን መብራት ሁሉ የምታጠፍው ይመስለኝ ነበር

ከአጎቴ በላይ እውቀት ያለውና የሚፈራ ሰው ያለ አይመስለኝም ነበር።

ሰፈራችን ያለው ልጅ ያበደው በትምህርት ነው ሲባል እኔም ተምሬ ስጨርስ የማብድ ነበር የሚመስለኝ

የመንግስት ሰራተኛ ሲባል የመንግስቱን ቤት ማፅዳት ምግብ መስራትና ልብስ ማጠብ ይመስለኝ ነበር

አቢዮት ጠበቂ ሲባል ቀበሌ ውስጥ አቢዮት የሚባል ሰውዬ እንዳይጠፍ የሚጠበቅ ይመስለኝ ነበር

አያቴ መፃፍና ማንበብ ያልቻለችው እንደኔ አጥኚ ብሎ የሚቆጧት አጎትና አክስት ስለሌላት ይመስለኝ ነበር

ኤሌክትሪክ ደም መጦ ይገድላል ሲባል ደሙን ከመጠጠ በኅላ የት እንደሚያደርገው ግራ ይገባኝ ነበር።

ፊታውራሪ ሲባል የሆነ አስፈሪ ተናካሽ አውሬ ነበር.....

አያቴ ጠዋት በቀኝ አውለኝ ብላ ስትፀልይ በግራ በኩል ያሉትን ጎረቤቶቻችንን የማትውዳችው ይመስለኝ ነበር።
⓾𝕥𝕙 𝕗𝕦𝕟 𝕥𝕙𝕖 𝕣𝕚𝕘𝕙𝕥 𝕨𝕒𝕪 𝕠𝕗 𝕗𝕦𝕟!!
amezingtruth
𝑙𝑒𝑡𝑠 𝑔𝑒𝑡 2𝑘 𝑣𝑖𝑒𝑤𝑠 .............𝑠ℎ𝑎𝑟𝑒 .
982 viewsᴢᴇᴋɪ 10ᴇ, edited  15:21
Open / Comment
2021-04-27 05:21:49 10 ስለ ወንዶች በሳይንስ የተረጋገጡ ነገሮች


, ወንዶች ከሴቶች የበለጠ ጥያቄ ለመጠየቅ ይፈራሉ።

አንድ በተደረገ ጥናት ወንዶች መኪና ሲነዱ አቅጣጫ ሲጠፋባቸው ሰው አቅጣጫ ከመጠየቅ ይልቅ ወዲያ ወዲህ እያሉ መንዳት ወንዶች በየአመቱ በሺዎች የሚቆጠር ሌትር ነዳጅ ያባክናሉ ፡፡

ወንዶች ከሴቶች የበለጠ በቀላሉ ስሜታቸው ይጎዳል። ለማዘንም በጣም ቅርብ ናቸው።

2000 ከፍቅረኛቸው ጋር የተጣሉ ወንዶች ላይ በተደረገ ጥናት መሠረት 93% ወንዶች ከፍቅረኛቸው ጋር ሲለያዩ በመጀመርያ ሳምንት ላይ ይሄን ያህል የጉዳት ምልክት ያላሳዩ ሲሆን; ከተወሰነ ግዜ ቡኃላ ግን ዘላቂ የሆነ ከፍተኛ የስሜት መረበሽ; የሞራል ጉዳት; የመጠጥ ሱሰኝነት እና ሴት አለማመን የመሰሉ ችግሮች አጋጥሟቸዋል ። ሴቶች ደሞ ከዚ ተቃራኒ በሆነ መልኩ ከፍቅረኛቸው ጋር ሲለያዩ የመጀመሪያ ወራት በጣም ሲጎዱ ቀጣይ ግን ይሄን ያህል ዘላቂ ችግሮች አያጋጥማቸውም።

ወንዶች እራሳቸውን የማጥፋ እድል ከሴቶች በ 3 እጥፍ ይበልጣል

አምና ከተለያዩ ሀገራት በተሰበሰበ መረጃ መሠረት በ 2020 እራሳቸውን ከጠፉ ሰዎች መካከል በሚገርም ሁኔታ 78 ፐርሰንቱ ወንዶች ናቸው።

ወንዶች ከሴቶች የበለጠ ይዋሻሉ።

ወንዶች ሴቶች ከሚዋሹት እስከ ሁለት እጥፍ ድረስ ይዋሻሉ። ሴቶች በአማካኝ በቀን 3 ግዜ ሲዋሹ: ወንዶች ግን በቀን እስከ 6 ግዜ ይዋሻሉ።

ወንዶች ከህይወት ዘመናቸው ውስጥ በአማካኝ 1 አመት ሚሆነውን ሴቶች ላይ በማፍጠጥ ነው የሚያጠፉት

አንድ ወንድ በአማካኝ በቀን 10 የተለያዩ ሴቶችን በመመልከት በቀን 43 ደቂቃ ያጠፋል ፡፡ ይህ በየአመቱ ወደ 259 ሰዓታት (ወይም ወደ 11 ቀናት ያህል) ይደርሳል ፡፡ በዚህ ምክንያት ( አንድ ወንድ 50 አመት ኖረ ብንል) ከ 18 እስከ 50 ዓመቱ ባለው ጊዜ ውስጥ ወንዶች የሴቶችን አቅዋም በማድነቅ 11 ወር ከ 11 ቀናት ያጠፋሉ ፡፡

ወንዶች ከሴቶች ጋር ሲሆኑ ለብቻቸው ከሚበሉት ሁለት እጥፍ ምግብ ይበላሉ።

ይሄ ነገር ውሸት ሊመስል ይችላል ግን እውነት ነው። ወንዶች ከሴት ጋር ምሳ ወይም እራት ሲበሉ ከሌላው ግዜ የበለጠ ምግብ ይመገባሉ ፡፡ ለምሳሌ ወንዶች ከወንዶች ጋር ከሲመገቡ የመድገም እድላቸው 14 ከ መቶ ብቻ ነው; ከሴቶች ጋር ሲበሉ ደሞ የመድገም እድላቸው 93% ነው። ይሄን ያልኩት እኔ ሳልሆን በታዋቂው ኮርኔል ዩኒቨርስቲ የተደረገ ጥናት ነው ፡፡ ጥናቱ እንዳለው ከሆነ ወንዶች እንደዛ የሚያረጉት ሴቶችን ለማስደመም ነው የሚያረጉት።

የወንዶች የኑሮ ሁኔታ በ አስተሳሰብ ጥራታቸው ( IQ ) ነው ሚወሰነው።

አንድ በሚጠጡ ሰዎች ሰዎች ላይ የተደረገ ጥናት ከፍተኛ IQ ያላቸው ወንዶች አብዛኞቹ አልኮል የማይጠጡ ሲሆኑ ; ዝቅ ያለ IQ ያላቸው ወንዶች አዘውትረው ጠጪ ( ሰካራም) ናቸው።

በመብረቅ የመመታት እድል

ወንዶች ከሴቶች የበለጠ በመብረቅ የመመታት እና የመሞት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው ፣ 2006 እስከ 2016 ባለው ግዜ ውስጥ በአለም ላይ ከተመዘገቡት የመብረቅ አደጋ ሞት ውስጥ 79% የሚሆኑት ወንዶች ናቸው ፡፡

የአለም የወንዶች ቀን በየአመቱ November 19 ይከበራል።

ምርጥ ጉዋደኛ

ወንዶች በህይወት ዘመናቸው በአማካይ 3 ብቻ ምርጥ ጉዋደኛ ( Best Friend ) ሲኖራቸው:: ሴቶች ግን እስከ 7 ይሆራችዋል። የ ወንዶች ጉዋደኝነት ከሴቶች ጉዋደኝነት የበለጠ እንደሚረዝም ተረጋግጧል።

#amezingtruths
⓾𝕥𝕙 𝕗𝕦𝕟 𝕥𝕙𝕖 𝕣𝕚𝕘𝕙𝕥 𝕨𝕒𝕪 𝕠𝕗 𝕗𝕦𝕟!!!
1.2K viewspeace, 02:21
Open / Comment
2021-04-26 12:25:16 https://t.me/kogoese
149 viewsᴢᴇᴋɪ 10ᴇ, 09:25
Open / Comment
2021-04-26 07:58:26 ጠላታችን ያለው አይምሯችን ውስጥ ነው፤ እስክንሞት የሚያስጨንቀን...የሚያንገበግበን... ሊሰብረን ሊያቆመን የሚታገለን...ህልማችንን ሊያዳፍን የሚዋጋን...በቃ ፍልሚያው ጭንቅላት ውስጥ ነው! ባንክ የቆጠብናት አካውንት ውስጥ አይደለም! ስራችን ውስጥ አይደለም! ግንኙነት ትዳራችን ውስጥ አይደለም! ወዳጄ በሰዎች አዝነህ ልብህ እንዳይሰበር ውጊያው አይምሯችን ውስጥ ነው!


ግሩም ቀን ተመኘንላችሁ!!!!!
Kogoese
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
982 viewsᴢᴇᴋɪ 10ᴇ, 04:58
Open / Comment
2021-04-25 19:04:47 ካነበብኩት ላካፍላችሁ

ይህ ያስተምራችኋል ብዬ ስላሰብኩ እንዲህ አሰናድቼ አቀረብኩላችሁ.... ..............!!!


አንድ በስቃይ የተሞላ ህይወትን የሚመራ ሰው ነበር። ሰውየው ወደ አምላኩ በሚፀልይበት ወቅት "ሁሉም ሰው ደስተኛ ሆኖ ለምን እኔ ብቻ እሰቃያለሁ? ለምን እኔ ብቻ?" ይል ነበር።

አንድ ቀን ጥልቅ በሆነ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ሆኖ ለአምላኩ ጸለየ። "አምላኬ የማንኛውም ሰው ስቃይ ብትሰጠኝ ልቀበልህ ዝግጁ ነኝ። እባክህ! እባክህ ጌታዬ የእኔን ግን ውሰድልኝ። ከዚህ በላይ ልሸከመው አልችልም" ሲል ተማጸነ።

ጸሎቱን ጨርሶ እንደተኛ ውብ የሆነ ህልም አየ። በህልሙ አምላክ ሰማይ ላይ ተከሰተና እንዲህ ሲል ተናገረ። "ስቃያችሁን ሁሉ ወደ ቤተ መቅደስ አምጡ።"

እያንዳንዱ ሰው የየራሱ ስቃይ የታከተው ስለነበር በተለያዩ ወቅቶች "የማንኛውም ሰው ስቃይ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ። የእኔን ግን ውሰድልኝ። ከዚህ በላይ መሸከም አልችልም " ብሎ ይጸልይ ነበር።

እንደተባለው ሁሉም ሰው ስቃዩን በቦርሳው አጭቆ ወደ ቤተ መቅደሱ አመራ። ባለታሪኩን ጨምሮ ሁሉም ሰው ጸሎቱ አምላኩ ዘንድ ተቀባይነት ስላገኘ በስፍራው ላይ ከፍተኛ የደስታ ስሜት ነገሰ።

ሁሉም ሰው ከቤተ መቅደሱ ሲደርስ አምላክ እንዲህ ሲል አወጀ። "ቦርሳችሁን ከግድግዳው ስር አስቀምጡ"

ሁሉም ሰው ቦርሳውን አስቀምጦ ከጨረሰ በኋላ አምላክ እንዲህ ሲል በድጋሚ አወጀ። "አሁን መምረጥ ትችላላችሁ ማንም ሰው የፈለገውን ቦርሳ መውሰድ ይችላል።"

በጣም አስገራሚው ነገር ቀን ከሌት ሲጸልይ የነበረው ሰውዬ ሌላ ሰው ቦርሳውን እንዳያነሳበት እየተጣደፈ ወደ ቦርሳው ሮጠ ሁሉም ሰው አንደ ሰውየው የነራሱን ስቃይ ያጨቀበትን ቦርሳ ፍለጋ ተራወጠ። እያንዳንዱ ሰው የየራሱን ስቃይ ለመሸከም ዝግጁ ነበር።

ምንድን ነበር የተከሰተው?

በህይወታቸው ለመጀመሪያ ጊዜ አንዳቸው የሌላቸውን ችግር ስቃይና መከራ ተመለከቱ። እንደውም እራሳቸው ከያዙት ቦርሳዎች የሚበላልጡ የሌሎች ሰዎች በስቃይ የታጨቁ ትልልቅ ቦርሳዎች እንዳሉ ተገነዘቡ በተጨማሪ ሁሉም ሰው ከራሱ ስቃይና መከራ ጋር ተላምዷል። የራሱን ስቃይ ማባበል እና መቻል ይችላል። የሌላውን የመከራ ቦርሳ ቢወስድ ግን ከቦርሳው ውስጥ ያለው አዲስ አይነት መከራ ምን አይነት እንደሆነ አያውቅም። ምናልባት የባሰም ሊሆን ይችላል።

አላሚው ሰው ከእንቅልፉ ሲነቃ በድጋሚ ጸለየ። "አምላኬ ስላሳየኸኝ ህልም አመሰግናለሁ። ከዚህ በኋላ እንዲህ አይነቱን ጥያቄ ደግሜ አልጠይቅም። የሰጠኸኝን ነገር ሁሉ የሰጠኸኝ ለበጎ ነው። ለዛም ነው የሰጠኸኝ።"
1.2K viewsᴢᴇᴋɪ 10ᴇ, 16:04
Open / Comment