Get Mystery Box with random crypto!

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 128.65K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
Buy ads: https://telega.io/c/bewketuseyoum19
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 206

2021-10-24 23:03:15
"…. ዝም ስትል የማታውቅ የሚመስላቸው ብዙዎች ናቸው ምክንያቱም እነሱ በማውራት ያምናሉና ፡፡ ነገር ግን ያወሩትን አይኖሩትም :: አንተ ግን በማውራት አትመን ዝም ብለህ ልታወራው የፈለከውን ኑረው ። ከዛም በአንተ ዝምታ ውስጥ የኖርከው ህይወት ጥሶ ይወጣና አንተ ዝም እንዳልክ ሳታወራ ሰዎች ያወሩልሀል ።....."

አና ፍራንክ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
874 viewsAbela, 20:03
Open / Comment
2021-10-24 21:49:10
መውውደድ ይመለሳል ወደዱ
(እንፍራንዝ ካፍካ እና ትንሿ ልጅ)

እንፍራንዝ ካፍካ(1875-1916) በአርባ ዐመቱ ሚስትም ሆነ ልጅ አልነበረውም ። አንድ ቀን በርሊን ውስጥ በመናፈሻ ውስጥ በመንሸራሸር ላይ ሳለ በጣም የምትወደው አሻንጉልት በመጥፋቷ የምታዝን ቲንሽዬ ልጅ ያገኛል ። ልጅቷና እንፍራንዝ ካፍካ አሻንጉሊቱን ቢፈልጉት ሊያገኙት አልቻሉም ።

ካፍካ ልጅቷን ለበነጋታው ይቀጥራታል ፤ ተገናኝተውም አሻንጉልቷን እንደሚፈልጉ ይነግራትና ይለያያሉ። በማግስቱም አሻንጉልቷን ማግኘት ባይችሉም ። ካፍካ ለልጅቷ ደብዳቤ ይሰጣታል ። ደብዳቤውም እባክሽ አታልቅሺ ። ዓለምን ለመጎብኘት ጉዞ ላይ ስለሆንኩ ነው ። ስለ ጉዞ ገጠመኜ እጽፍልሻለሁ " ይል ነበር በዚህ ደብዳቤ ሰበብ እስከ ካፍካ የሕይወት ፍጻሜ የዘለቀ ታሪክ ይጀምራል ።

በተገናኙበት ጊዜ ካፍካ የአሻንጉሊቷን የጉዞ ገጠመኞችና የቃላት ልውውጦች በደንብ ጽፎ ለልጅቷ ያነብላታል ።ልጅቷም ደብዳቤውን በጣም ወደደቻቸው ። በመጨረሻም ካፍካ ወደ በርሊን ተመልሶ ለልጅቷ ሌላ አሻንጉሊት አመጣላት(ልጅቷ ሌላ አሻንጉሊት ገዝታ ነበር)
"ምኗም የኔን አሻንጉሊት አይመስል" አለችው
ካፍካ ሌላ ደብዳቤ ለልጅቷ ሰጣት:-
"ትንስዬዋ ልጅ አዲስ አሿንጉሊት አቅፋ ወደ ደስተኛው ቤቷ መጣች ይል ነበር

ከአንድ ዐመት ቡኋላ ካፍካ ሞተ።
ከብዙ ዐመታት ቡኋላ አሁን ጎልማሳ የሆነችው ልጅ አንድ ደብዳቤ አሻንጉሊቷ ውስጥ አገኘች
ደብዳቤው እንዲህ ይላል ። "የምትወጂው ነገር ሁሉ ሊጠፋ ይችል ይሆናል ። በመጨረሻም የምትወጂው በሌላ መልኩ ተመልሶ ይመጣል ። "

ተ-ፈ-ጸ-መ
419 viewsAbela, 18:49
Open / Comment
2021-10-24 15:55:23 ለምትናፍቂኝ

ዉድሽ ባንቺ ምክንያት ይጠጣል ይላሉ
አስረዳኝ እባክህ ጉዳዩን በሙሉ

ብለሽ ስትጠይቂኝ...........

ከአመታት ጅረት
ከሰአታት ንጉደት
ከወራት መቃዠት
ከለታት መዋተት
ከልቤ ቆጣሪዉ
ከነፍሴ ዠዋሪዉ
ከሴኮንዶች እርቃን
ከፍቅርሽ ምርቃን
ላታነቂኝ ደርሰሽ
እባክህ ንገረኝ አልሺኝ አለሳልሰሽ።

የትኛዉን ልንገር...............

አጓደኞችሽ ጋር መጥተሽ ለጫወታ
ኑ ተቀላቀሉ ስትይ በፈገግታ
ከራስሽ ቀላቅለሽ ልቤ ገራገሩን
እዉን እሱን መስማት ትሻለሽ አሁኑን?

ወይስ...........

ለሁሉም ለምኑም የመጀመሪያዬ
ወዳንቺ ሳቀና የገነት መግቢያዬ
ካንቺ ጋር ስቀመጥ ከመላዕክት ዜማ ያማረ ቃልሽን
ስሰማ መኖሬን መስማት ትሻለሽን።

የተቀመጥሽበት የተቀመጥኩበት የፍቅራችን ወንበር
ማርያምን እላለሁ ይህን እዉነት ያዉቅ ነበር።

ዉድሽ ባንቺ ምክንያት ይጠጣል ይላሉ
አስረዳኝ እባክህ ጉዳዩን በሙሉ
ብለሽ ስትጠይቂኝ..............

በነዛ ለሊቶች ያወራናቸዉን
መለያየት ተስኖን ያወጋናቸዉን
መልሼ እያሰብኩ ከዶርሜ ገብቼ
ስኖር እንደነበር ልንገርሽ አዉጥቼ።

ከመዉደድሽ ጥላ
ከኩርፊያና ሳቅሽ ተቀምጬ ኋላ
ካንቺ ተሳስሬ
መስካሪ ባላየዉ በፍቅርሽ ታስሬ።

ዉል ባልታሰረለት መፍቻ በሌለዉ ጉድ
ገርጃፋ አድርገሽዉ ልቤ አንቺን በመዉደድ።

እሱን ብነግር ይሁን ላንቺ የተሻለ
በፍቅርሽ ቀይደሽ ነፍሴ እንደዋለለ።

አረ........እዲያ መዉደዴ
ይልቅ ይቅር በይኝ
ዛሬም እኮራለሁ አንቺን በመዉደዴ።

ዉድሽ ባንቺ ምክንያት ይጠጣል ይላሉ
አስረዳኝ እባክህ ጉዳዩን በሙሉ
ብለሽ ስትጠይቂኝ..............

አፍቃሪዉ እዉሩ አይኔ ተሸፍኖ
ማጣት አይኑ ይጥፋ ብሎ አመሳክሮልኝ

ሞኙ ጅሉ ልቤ ካንቺ ሲዉል ጊዜ
ካንቺ ሲያድር ጊዜ
ልክ እንደ አሁኑ ካንቺ ሲኖር ጊዜ
ሚያጣሽ አልመሰለዉ መዉደዱን መናገር
ማፍቀሩን መመስከር ከቶ መች መጣለት
አንቺ ደረሽና እንለያይ ብለሽ መርዶ አረዳሽለት።

ፅልመቱን ህይወቴን ያኔ እንደጠራሽዉ
መኖሬን ከመሞት እንዳወዛገብሽዉ
ባወራ ይሻል ሆይ ዉዴ እንደሰማሽዉ
አስቀይመሀኛል በቃ እንለያይ ብለሽኝ እንዳልሽዉ


ብዬ ብልሽ ይሁን የጥያቄሽ መልሱ
6 አመት በፊት ካሳየሽ በስሱ

እንጃልኝ መዉደዴ
ዛሬም እኮራለሁ አንቺን በመዉደዴ።

ይልቅ ይቅር በይኝ ፍቅርሽን በደልኩ
አንቺን ልርሳ ብዬ ሌላ ሴት አቀፍኩ
ያቺኛዋን ሳምኩ
ከዛች ተጋደምኩ
ዉዴ...ዉዴ አንቺን ለመርሳት ያልሆንኩትን ሆንኩ።

ዉድሽ ባንቺ ምክንያት ይጠጣል ይላሉ
አስረዳኝ እባክህ ጉዳዩን በሙሉ
ብለሽ ስትጠይቂኝ..............

መጠጣቴ እኮ ነዉ ደፍሬ እንድደዉል ካንቺ የሚያረገኝ
ከአመታት ኋላ ድምፅሽን ሚያሰማኝ

ይገርምሻል ፂዬ ከድምፅሽ ሚወጡት የቃላትሽ ዜማ
ያስደነግጡኛል እዉነት ስልሽማ።

እንጃልኝ መዉደዴ
ዛሬም እኮራለሁ አንቺን በመዉደዴ

ዉድሽ ባንቺ ምክንያት ይጠጣል ይላሉ
አስረዳኝ እባክህ ጉዳዩን በሙሉ
ብለሽ ስትጠይቂኝ..............

ከጊዜያት ቀመር
ከሂወቴ ቁማር
አኬሩ ቢወጣ
የኛ መለያየት ሚስጢሩ ሲወጣ
ስትነግሪኝ ጊዜ
ካለፈ በዋላ የፍቅር ደሞዜ

ለካ ሀይማኖት ነዉ
ይገርምሻል ፂዬ
ከንለያይ ይልቅ ያመመኝ ይሄ ነዉ

አይኔ አነባልሽ
ዉስጤ አለቀሰልሽ
ምነዉ በነገርሺኝ
ያኔ እንዲ ነዉ ብለሽ ፂዬ ባረዳሽኝ

አሁን ይበልጡኑ እጅጉን ጎዳሽኝ
ገላዬ ቢቆሽሽ
ዉስጤ ቢቃጠልም በመጠጥ ሰክሬ

ተማሪዉ ልቤ ነዉ ዛሬም የሚወድሽ
ከሀዋሳ ካምፓስ ይድረስልኝ ፍቅሬ።


የስንታየሁ100% እዉነተኛ ታሪክ

በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ

@TIZITA21

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
768 viewsAbela, edited  12:55
Open / Comment
2021-10-24 15:23:28 Adobe after effect በመጠቀም Video edit በማረግ ከኛ Youtube ቻናል ጋር መስራት የሚፈልግ ካለ አሁኑኑ በውስጥ መስመር ያናግረኝ።
@Yile_Ortodox
1.2K views| ፼ ωΑνЄ |, 12:23
Open / Comment
2021-10-24 11:26:19 ገላዬ....
ከመስኩ ላይ ቆሜ ፥ እምባን ባረገዘ
በናፍቆት ወይቦ ፥ በተድበዘበዘ
በዚያ መንታ አይኔ...
የመራቤን ጅራፍ ፥ የምኞቴን ጩኸት
ላንቀላፋው ጤዛ ፥ ለወፍ ጎጆው ምልዓት
ዘምሬ
ዘምሬ
ደስኩሬ
ደስኩሬ
ህቅ ባለው መንፈስ ፥ ምሬት ባየው ልሳን
ብናገር ለእነሱ ፥ የኔን እንዲህ መሆን
የአንቺ ወዲያ መቅረት ፥ የንጋት ሰቀቀን
በጉድ ወጣ እያሉ ፥ ለሰማይ ለምድሩ
ለሰው ላራዊቱ ፥ ለቀየው መንደሩ
መስቀሉ ናት ብለው ፥ ናፍቆት ወለፈንዴ
ተሸነፈ ብለው ፥ ያሙኝ ይሆን እንዴ?
.................. / / .....................
ሲራክ ወንድሙ
387 viewsAbela, 08:26
Open / Comment
2021-10-23 23:56:32
የማንቂያ ደውል በመምህር ምህረታብ አሰፋ የሚቀርብላችሁ የቴሌግራም ቻናል ነው ቻናሉን በዚ ያገኙታል።
60 views| ፼ ωΑνЄ |, 20:56
Open / Comment
2021-10-23 23:56:06 የማሰብ ብቃቶን ማበልፀግ ይፈልጋሉ?
ትኩረትና አስተዋይነቶን መጨመር ያስባሉ?
የአእምሮ ሰላምና መረጋጋት ለማግኘትይናፍቃሉ?

እነዚህን ሁሉ የያዘዉን ቻናል ይቀላቀሉ
55 views| ፼ ωΑνЄ |, 20:56
Open / Comment
2021-10-23 20:03:41 ትልቁን የኦርቶዶክስ የስልክ ጥሪዎች ቻናል ለመቀላቀል ከታች ያለው ሊንክ ይጫኑት
155 views| ፼ ωΑνЄ |, 17:03
Open / Comment
2021-10-23 10:55:06 የዘላለም እናት
በእናትነት አንጀት በአባታዊ ወኔ፣
አቅፋ አሳድጋኝ እኔን በወገኔ፣
የወላድ ማህጸን እንስፍስፍ ሲያደርጋት፣
ፍቅሯ ከልክ ሲያልፍ እናት ነሽ ስላልናት፣
የደጉ ቀን እናት የከፋ ለት አባት፣
ሀገሬ እንዲህ ናት፣

በስም አባት ብቻ ልጇን ያልተጋራች፣
እኔ ላሳድገው ሲሏት ያልተስማማች፣
አሁን ላይ ጐርምሶ ከቤት ልውጣ እንዳለው፣
ሰፈር ሲበጠብጥ ያላሰደገ አባት ከየት ነው ሚመጣው፣
ባላዋቂ ብዕር ማገር ሲነቀንቅ፣
የት ያለው አባት ነው ምሰሶ እሚያጠብቅ፣
ጠግቦ ልውጣ ብሎን ለያዥ ካስቸገርን፣
በምን ቀሚሷ ነው እሷ ምሸሽገን፣
ቀሚሷን ለመያዝ የተሽቀዳደመው፣
ሸማዋን ቀዳዶ ሌጣዋን ካስቀረው፣
እናቴ ምን ታድርግ በምኗ ትያዘው፣

ፍሬዎቿ እሾህ ሆነን ከበቀልን፣
እሽ በምን እዳ መጣ ትሰብስበን፣
እንደው በየት ቦታ እረ በየት ሀገር፣
ልጅ እናትን እንጂ እናት ልጅን አጦር፣
በማረፊያዋ ወቅት ባክኚልን ካልናት፣
ውለታዋን ሽረን ካልን አባት አባት፣
ጀግና እናት መሆኗን የረሳነው መስሏት፣
እንደ ዘመዶቿ እሷም አንሳ ጎብጣ፣
ለማደጎ እንዳይሆን ነገም የእኛ እጣ።

ትዕይንት አባተ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.6K viewsAbela, 07:55
Open / Comment
2021-10-23 08:50:25 እንደ ሙዱ

ይሔ መዉደድ ማለት ፣ለካስ አለዉ አይነት፤
አንደኛዉ እሰኪያገኝ፣ሌላዉ #ደግሞ እስኪሞት፤
አንዱ እስከሚጠላ፣አንዱ እሰከሚወደድ፤
አንዱ #ዉድ እስኪያገኝ፣ደግሞ ሌላዉ እሰኪያብድ፤
#እንደ ሰዉ ተፈጥሮ፣ቢለያይ መንገዱ፤
#ወዶ ነዉ የሚኖር ፣ሁሉም እንደሙዱ፤
ሰዉ ወዶ ነዉ እንጂ፣ #ባይወድ'ማ ኑሮ፤
ማን ይዘልቅ ነበር፣ ከዉሸታም #አብሮ፤

@KeyD219 (kidus)

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
330 viewsAbela, edited  05:50
Open / Comment