Get Mystery Box with random crypto!

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 129.63K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
Buy ads: https://telega.io/c/bewketuseyoum19
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 182

2021-12-14 10:25:49 በክፉ ቀን

ለእውነት ለሀቅ አይደለም
ቤቴ ብርሃን ሲሆን የማይወደኝ የለም
ወዳጄ ይበዛል በዝቶ እንኳ ይተርፋል
ጨለማ ሲሆን ግን...
የመጣው ሰው ሁሉ ተያይዞ ያልፋል
ቀን ለኔ ሲወጣ
ከጎንህ ነን ባዩ ሞልቶ ሞልቶ ይበዛል
በቅቤ ምላስ ሽንገላ አባባል ይገዛል

ዛሬ ድንገት ቢያመኝ
ጨለማ ቢወርሰኝ
ቸነፈር ሲገርፈኝ
ችጋር ሲሳለመኝ
እኔን ማን ጠየቀኝ???

ዮኒ
ኣታን @yonatoz

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.7K views07:25
Open / Comment
2021-12-13 20:17:49 ከሌላ እንዳትቆጥር

ይሀዉልህ ዉዴ
ትላንትና ማታ

እንባዬን አፍስሼ
አፈር ትቢያ ልሼ
ከእግርህ ወድቄ ማረኝ ተዉ ማለቴ
ታቦት እየጠራዉ መማል መገዘቴ

ከሌላ እንዳትቆጥር

ደግሞም ታቦታቱን ጠርቼ ጠርቼ
አንተም ዝም ብትል
የሞተች እናትህን መቃብር አዉጥቼ
በሷ ሞት እያልኩኝ ያኔ መለመኔን
አንተንም እያስማልኩ.......
ቅዱሱን መፅሐፍ በእጆችህ አስይዤ
አልተውሽም ስትል በደስታ ፈንጥዤ

ያኔ መጨፈሬን

ከሌላ እንዳትቆጥር

ከወትሮዉ በሌላ
ካልለመድከዉ ገላ
እራሴን ሰጥቼ ደባብሰኝ ማለቴን
ሳመኝ እቅፍ አርገኝ ብዬ መማፀኔን
ላለፈ ስህተቴ
ከእቅፍህ ገብቼ ንስሀ መግባቴን

ከሌላ እንዳትቆጥር

አንተን ከረሳሁኝ
ባንተ ከማገጥኩኝ
ሳት ብላኝ ነብሴ
ሌላዉን ከሻተች ሞት ይሁነኝ ዋሴ።

ስቅበዘበዝ ልሙት ልክ እንደ ይሁዳ
የሄድኩበት እግሬ ይቅር ምድረ በዳ።

ነፍሴንም አይማረዉ
እግዜሩም ይጣላኝ
እኔ አንተን ከረሳዉ
ያቀፍኩበት እጄን ለምጥ እከክ ይዉረሰዉ
ብዬ መገዘቴን
በራሴ ጨክኜ ርግማን ማዝነቤን

አደራ እንዳትቆጥረዉ
እባክህ በሌላ
ሰክሬ ነዉ እንጂ
ባሌ ትዝ ብሎኝ
ለደቂቃም እንኳን እንዲያዉ ለቅፅበቱ
አንተ የኔ እንድትሆን አልሻም በእዉነቱ።
..........................
..........................
..........................
..........................
አንተን እንደ ንፁህ ወንድሜ ነዉ የማይህ አላለችም

በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ

@Tizita_wolde

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.9K views17:17
Open / Comment
2021-12-13 11:28:45 #ላንጠቅማት ነገር
ከቦታዉ ካልሆነ ሁሉም
#በራሱ
ሆኗል ሳቅም ለቅሶ ላይ
#ማልቀሱ
ሲያመን ህመመቻን በጋራ
#ታማሚ
ራዕያችን ካልሆነ ሩቅ
#አላሚ
በራችን ክፍት ነዉ ብለን
#ለፍቅር
ክፉ ጠባቂ በሩን ዘግቶት
#ቢቀር
ደፍረሶ እስኪጠራ ላለመጠበቅ
#ብሎ
ደፍቶት ሲሄድ ኩባያዉንም
#ጥሎ
ተኖ አየጠፋ ፍቅር
#ከልባችን
ጠፍቶ እያያን አንቆም
#ከደጃችን
የሰቃይ ቤት በደም
#የሰከረዉ
ፍቅር ሰለጠፋ ወገኑን
#ሲከዳዉ
ቃል ጠፋ ሚወጣ
#ከአንደበቴ
ወገኔ እየሞተ ፍቅር
#በማጣቴ
ጥቅሜ ለምኗ ነዉ ለዚች ብሩክ
#ምድር
ሰኖር ከነስተት ካለቦታዬ
#ብፈጠር
#ከዳዊት#


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
3.4K views08:28
Open / Comment
2021-12-13 10:03:39
2.9K views07:03
Open / Comment
2021-12-13 08:07:28 ድልዙ ደብዳቤ!
'''''''፠'''''''፠'''''''
የፃፍኩልሽ ቅኔ አልኮል ሲሎኝ በርታ
ረጅሙ ጽሁፍ ብዕር ጠፍቶ ማታ
ሰርዤ ደልዤ በዱልዱሙ እርሳሴ
አይገርምም መማሌ ቆሜ "በስላሴ"?

ጠፍቶብኝ ጸጸቱ ጭፈራ ሳልወጣ
"ወለል" ብዬ ጠራው አስተናጋጅ ሳጣ!
መልዕክት እስቲ አድርስ እዛጋ ላለችው
መጠጡን ስትቀዳ ዐይን ዐይኔን እያየችው'

በፍቅሯ ጣለችኝ ወይ ወገብ መቅጠኑ
ጨፈር ልል ስነሳ ቢዘጋ ዘፈኑ!

እሷም ትወጣለች~
እሷም ትሔዳለች~
እሷ የምታውቀው ማየት ሆኖ 'ታማኝ'?
ያስተናጋጅ ፍቅር መች ይዞ ገደለኝ!


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
3.1K views05:07
Open / Comment
2021-12-12 21:54:13 ለፈገግታ ያህል

ሙላ ናስሩዲን ሃጅ ወደሳውዲ ሄዶ ነው። ሰው ከመብዛቱ የተነሣ ናስሩዲን
ማደሪያ ማግኘት አልቻለም። በመጨረሻ አንድ ሆቴል ውስጥ ጥንድ አልጋ ያለው
እንድ ክፍል አግኝቶ ገባ። ብዙ ሳይቆይ ሁለተኛው አልጋ ተከራይቶ ሰውዬው
መጣ። ናስሩዱን ሰውየውን ሲያየው ልክ እንደሱ ነበር የለበሰው። ቁርጥ
እራሱን። መተኛት አልቻለም። ሰውየው ነቅቶ
“ወንድሜ፣ ለምን አትተኛም?” አለው።
“አንድ ችግር ገጥሞኝ ነው።”
“ምን?”
“እኔና አንተ ተመሳሳይ ነን። ተኝተን ስንነቃ እራሳችንን መለየት ቢያቅተንስ?” አለ
ናስሩዲን።
ሰውየው ለካ ተንኮልኛ ኖሯል። ዞር ዞር ሲል አንዲት አሻንጉሊት ጥግ ላይ
ተቀምጣ ይመለከታል። ያነሳና እግሩ ላይ አስሮ...
“አሁን ተኛ፣ አሻንጉሊት እግሬ ላይ የታሰረው እኔ ነኝ ።” ይለዋል።
ናስሩዲን ችግሩ ስለተፈታለት አመስግኖ ይተኛል። ሰውዬው በጠዋት ሲወጣ
አሻንጉሊቱን ከእግሩ ላይ ፈቶ ናስሩዲን ላይ አስሮት ይሄዳል። ናስሩዲን ሲነቃ
ደነገጠ። እየሮጠ ወደ አደባባይ በመውጣት እንዲህ አለ።
“አንድ ሰው ተሳስቶ እኔነቴን ይዞ ሄዷል። እሱ እኔ ነውና የት ነው
የማገኘው?”........አለ ይባላል

አለማየሁ ገላጋይ ከታል መፅሃፍ የተወሰደ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.6K views18:54
Open / Comment
2021-12-12 20:25:39 ዘመኔ ቀለም



ገላን ማብከት
ሆነኝ ተብሎ ልብስን መቅደድ
የሚያስደንቅ
ኖሩ ሚያስብል የዘመኑ ድንቅ መውደድ፡፡
ካ'ለም ጋርዶ
ከሟች አስበልጦ
በቋሚ አስጨፍልቆ ሰወንና ቀልቡን ማውረድ
እያዩ ማያዩት
ሰምተው ማይሰሙት
የሰው ጥላ መፍጠር የጊዜያችን ታላቅ ማበድ፡፡
ልብሱን መቅደድ
ድንቅ መውደድ፡፡
ቀልቡን ማውረድ
ታላቅ ማበድ፡፡
አይደል ማበድ
በውሃ የሚያልቅ ጨርቅን መቅደድ፡፡
አይደል መውረድ
ኗሪን መምራት በሟች መንገድ፡፡
ሰምተን ባንሰማ'ንጂ
መለኮት ነግሮናል
ፍቅር እንደሚያወርድ ከሰማይ ዙፋኑ፡፡
ልብ ባንል'ንጂ
በፍቅር ያበዱ
ለጽድቅ የተጠሩ በሰው አቅም ያመኑ
ስናየው ኖረናል
ጨርቅ ማቄን ሳይሉ
በዕድሜ ልካችን ልክ ካ'ለም ሲመንኑ፡፡
ሰማይ ቄስ አይነት ነው
ክብር አጎናጽፉኝ
ይላል አወድሱኝ ይወዳል ቡራኬ
አመሉን ስለማውቅ
በታጠፈ አንጀቴ
ዝናቡን ለመንኩት ቆሜ ተንበርክኬ፡፡
አረ እኔን ጨነቀኝ
ከሰማዩ ይብስ
ፍቅሬ ያወረደው ከፋብኝ አምላኬ፡፡
ሰማይ በቄስ አምሳል
አምላክ በኩሩ አካል
ሆነው ቆመው ፊቴ የዝንት ሆነ ብርኬ፡፡
< ሰማይ መቀመጫህ
ምድር መረገጫህ.....>
ብለው ያገነኑት ቄሱ የሰበኩት
ፈጣሪ ዘንግቷል
መሆኑ ጠፍቶታል
አካሌ ምድርነት ነፍሴ ሰማይነት፡፡
እኔን ተረግጦ
እኔ ላይ ተቀምጦ
ገድሉን ያገዝፋል በቄስ ገዛችነት፡፡
ግዝት እፈራለሁ፡፡
እንጰረጰራለሁ!!!
ያ'ምላክ አጋፋሪ ገበዝ እሸሻለሁ፡፡
ስሞት እንደሚኖር
ሳልኖር ዲዳ እንደሆን
ሁሉን እያወኩ ለቃሉ እሰግዳለሁ፡፡
ግዝት እየፈራሁ
ገበዝ እየሸሸሁ
አንዳንዴ ስጀግን
ከሰው አውድ ርቄ
አምላክ ተብዬውን እንዲ እጠይቃለሁ፡፡
ለምን!?
ለምን!?
ለምን!?
ለምን....
ለምን እንዲህ ሆነ
ብዬ እወጥራለሁ አስጨንቀዋለሁ!!!!
እሱም ተረጋግቶ
እንዲህ መለሰልኝ በሽንፈቴ ተነቃቅቶ
ቅፅበት ንቃቴ ሳይረብሸው
ቀጭን ፍርሃቴን አሳይቶ
ድንድን ድፍረቴን
በምጣድ ሳይሆን በክብ ዓለሜ አነጉቶ፡፡
ከአቻዬ ሳይሆን
ከቄሰ ገበዙ ከሰይጣኔ ከፍቶ፡፡
አለኝ....
" ምድር አረገዘ
ዘር እሸት ወለደ ሰማይ በወሰበ
ሊሰፋ የፈጠርኩት
መብል ያጠበበው የሰው ሆድ ጠገበ..."
አለና መለሶ
መለኮት ታላቁ አንገቱን ዘለሰ፡፡
የቄሱን አክብሮ
የምስኪን ታካቹን የኔን አንኳሰሰ፡፡
እኔም.....
< ካምላኩ ያወቀ...>
ፍጡር አልኩኝና መቅሰፍቱን ፈርቼ
መጻ'ፍ እንዳላጥብ
ለሰው ተራቅቄ በራሴ ከፍቼ
ይኸው እኖራለሁ
ለጥበብ ጠባቡን
ለምግብ ኅልቁውን ሆዴን ብቻ አስፍቼ፡፡
ፍቅር ጠራኝ ባለ
በኔ ላይ ተራምዶ
በኔው ላይ ተቀማጭ አምላክ ተጣልቼ
ሰማይ የሚመስልን
ክብር ያደለበውን
የገበዙን ዱላ ግዝቱን ፈርቼ፡፡
ሳላብደው አብጄ
ሳልወደው ወድጄ
ሞቴን ረስቼ
ሕይወት ነው እላለሁ
አዲስ ረስቼ ልማድን ለምጄ፡፡
እኔኑ አርሳለሁ
መውደድ ነው ያሉኝን መንፈዜን ጠምጄ፡፡
መሆኔን አርክሼ
ድንቅ ላሉት እብደት ጨርቄን ቀዳድጄ፡፡

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.3K views17:25
Open / Comment
2021-12-12 15:49:31 መርዶ አታርዱኝ

ሰዎቹ አምነዋል
ቤታችን ስገባ ጉዝጓዝ ተጎዝጉዛል
ፍራሾቹ ወርደው መሬት ተነጥፈዋል
ፍሪጁ ቲቪያችን አቡጀዲ ለብሷል
አንዷ ደሞ መጣች ነጠላ ዘቅዝቃ
የት ሄደ ደግ ሰው ጠየቀችኝ አንቃ
ምንም መልስ ሳልሰጣት
ዞሬ እነኳን ሳላያት
ፎቶህን እያየው አንድ ቃል ነገርኳት
የኔ ባል አልሞተም አታልቅሺ አልኳት
እዛ የነበረ ሁሉም ደነገጠ
እንባ እያወረደ ከንፈሩን መጠጠ
ምን ያደርግልኛል....
ከንፈር መመጠጡ
ምን ያደርግልኛል....
እንባቸው መፍሰሱ
አንተን አይመልሱ
ጎጆዬን አይቀልሱ
የእነሱ ዋይ ዋይታ
የእነሱ ዋይ ዋይታ
በአንድ ቀን ታይታ
ከሰልስት
ከአርባው
ደሞም ከ ሰማንያው
የማትዘልቅ ናት
ግና ግን
ግና ግን የኔ ባል
ስምህ ለዘላለም ሲወሳ ይኖራል
በከንቱ አለም ላይ ደግነትህ ገኗል

ሐና ይመር

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
3.2K views12:49
Open / Comment
2021-12-12 10:31:55 ፍቅር ጮኸ
======
ድምፅ በሌለዉ እምቢልታ
ቃላት ባጣ ኡኡታ
ተከዳሁኝ እያለ ብሶቱን እያረዳ
የፍጥኝ ተያይዞ ለሞት እየተሰናዳ
ከንቱ ነሽ እምነት በሚል ምሬት
ፍቅር ጮኸ ያለ አንደበት።


በሰላም ተፃፈ
for any comment @selamnen

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
3.6K views07:31
Open / Comment
2021-12-12 09:44:10 ርእስ :-7 ቁጥር
ደራሲ :-መስፍን ሰለሞን ሙሀባ
ዓመት :-2012
የይለፍ ቁጥር :-7

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
3.4K viewsedited  06:44
Open / Comment