Get Mystery Box with random crypto!

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 129.18K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
Buy ads: https://telega.io/c/bewketuseyoum19
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 179

2021-12-21 20:10:43
አዲስ አልበም በዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን ቀን አውጣላት ተለቀቀ።ከታች ባለው ሊንክ ገብታቹ ማውረድ ትችላላቹ።
1.7K views17:10
Open / Comment
2021-12-21 17:50:42 እንቆማለን
∞∞∞∞∞
አክሱምን ተደግፈን
ስር በሰደደ በጸና ማንነት
ታቦተ ጽዮንን ይዘን ያ'ባቶቻችንን እምነት
ምንም ሳይበግረን እንደ ላሊበላ ውቅር
.
.
.
ዘመናትን ልንሽር ፣
አድዋን ልንደግም ፣
ትውልድ ልናስቀጥል ፣
ያለምንም ማፈግፈግ
ታሪክን እንፅፋለን
ዛሬም እንደገና ለድል እንቆማለን!!!

የማይረሳ ነገር ሼር ማድረግ

በለዓለም መሰረት እንደተጻፈ
@Leo_poet
2.5K views14:50
Open / Comment
2021-12-21 13:44:37
Ultrasound Atomization Cool Humidifier
በኤሌክትሪክ የሚሰራ
ለቤት መልካም መዓዛን የሚሰጥ

Capacity: 250ml
Purify the air & Beautify the Environment
Reducing soot soothe fatigue
Moisturizing the skin beauty beauty

Your Home , Your Smile


ዋጋ፦ 1200 ብር



አድራሻችን
አዲስ አበባ


ስልክ:
0911468394
@abela1987

Join
https://t.me/habeshamarket2
478 views10:44
Open / Comment
2021-12-21 12:56:28 ፨፨፨ ሰንደቅ~ዓላማ ።።።

ከአገራቶች አርማ የቀለማት ውህድ፤
ከትርጉም ቃላቸው የሚስጥራት ሰደድ ፤
የጦቢያ ልዩ ነው ቀይ ቢጫ አረንጓዴው ፤
በምድር ከፍታ ላይ ሰማይን ያቆመው፤
የማርያም መቀነት የኖህ ደማቅ ቀለም፤
የአለም አርማ ጦቢያ በሰማይ ማሕተም፤
ወንዙ ቀለም ሳለ ፤እፅዋት ብዕሩ
መጣፊያውም የገፍ ሰማይና ምድሩ
ቀስቱ እየከረረ ፤ደመናን እየሰነጠቀ
በህብር ታጅቦ ፤ቀለም ተሰበቀ
ምነው ለሰውኛ? ያውም ለሃበሻ !
ፀሃይ ያከሰለ አካሉን
የፍጥረት አሃድ አፈሩን
በሰንደቅ ጠቅልሎ
አላማን ሰንቆ አደረገው ጉርሻ ፤
ዝማሬ ተሰቅሎ ጉልበት ሆነ ልምሻ ፤
ምነው? ምነው አንተ-ችየ ?
ሰማችን ቀለለ ክፍተታችን ታየ
ፍቅር ተነቅሶ ፤ልብ ባንድራ አትሮ
ዘላለም ነው አርማ ሰው እስካለ ኑሮ ።

Rebih...


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
821 views09:56
Open / Comment
2021-12-20 21:01:40 ༄ፍቅሬ༆
𓂀ድብቅ ግጥሞች༒︎

ብርዱ:ቅዝቃዜው
ሙቀት፡ነበልባሉ፤
እኔን፡ለማበስበስ፡የሚዘንበው:ሁሉ፤
ተስፋ:አይስቆርጠኝ:መንገዴን:አይገታው፤
መጓዜን:አላቆም:ከቶ:ለምመጣው፤
አይሻለው:ብዬ:ሁሌም:የምጓዘው፤
ባላወራሽ:እንኳን:ባልተነፍስ:እንኳ
አንቺኑ:ካየሁሽ:ደስ:ስለሚለኝ:ነው።

ሚኪያስ እንዳለው
@mikiendialem



ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.0K views18:01
Open / Comment
2021-12-20 13:22:18 .

በሁሉ የደመቀው : ደብዝዟል ያ መልኳ
ቀሚሷ ይመስክር : ነውር ሆኗል ልኳ
ማንም የሚስመው : ቀልቷል
አብጧል ፊቷ
የተመካችበት : ፈርሳለች ጣኦቷ
ኪዳን የማታውቀው : ጣቷ ኮስምናለች
ቀድማ የወጣችላት : ፀሀዩኣ ጠልቃለች
ሲነኳት ተሰብራ : ሲገፏት ወድቃለች
ሳታቃስት ሙታ : በቁም ተቀብራለች
.
.
.
አልቃሽ አጣችና
ሙሾ አውራጅ ጠፋና
በራሷ ቀብር ላይ : ራሷ አለቀሰች
ራሷ ለስሟ : ሙሾን አወረደች
(ለኔ ያርግ እያለች)
ገላዋን ጨክና : አፈር አለበሰች
....ሩጫ ጨረሰች?

ከዛ ቀን በኋላ
ያማት አልተገኘም : የሚያነሳ ስሟን
ነውሯን የሚያነውር : የሚሰብር ቅስሟን
የት ጠፍታ ነው? የሚል : አስታዋሽ አልመጣም
ደበዘዘች የሚል : ከአፍ ውስጥ ቃል አልወጣም

በአንድ እብድ ገመድ
ያላበደ ንፋስ : የሚወዘውዘው
ቀሚስ ይዘምራል
መዝሙሩን ሲሰማ
ከደመና በላይ
የመነነ ውብ ጥርስ : ደርሶ ፈገግ ይላል

ቀሚሱ ሲዘምር.....
ጨዋ እንደነበረች : ጨዋነት ነፈጓት
ቆንጅየ ነበረች : ውብ መልኳን ገፈፏት
ለባሽ አድማቂየን : እንቡጤን ቀጠፏት
(ቀጥፈውስ መች ተዋት)
ለእድፍ ለነውራቸው : አረጓት ተከሳሽ
ለመርገፋቸው ልክ : አረጓት ስም ወራሽ

በስንት ልመና
በፀበል በፀሎት : ብታገኝ እብደቷን
ይተራመሳሉ
ሊሰጧት በሽታ : ያንን ደህንነቷን
የቀራትን ሀብቷን : እብደቷን ሊሰርቁ
መላእክት ሰልፍ ያዙ : ጤንነት ሊያጠምቁ
ምናለ ብትተዋት : እንዲህ ባትሻሙ
"አዲሱ በሽታ : ጤንነት ነው ስሙ"
(ብሏል ያ ገጣሚ
ቢኖር ኖሮ ሰሚ).

አለሁላት እኔ : መስካሪ ንፅህቷን
እሷን ሲያጨልሙ : ሌሎቹን ማብራቷን
ከራሷ እንኳ ሸሽታ : ብቻዋን ማንባቷን
ነፍሷን አሳብዳ : ስጋዋን መክዳቷን
ሞታም ኗሪነቷን

ይዘምራል ቀሚስ
ባበደ ገመድ ላይ ያላበደ ንፋስ የሚወዘውዘው
ጥላሸት ያጠላት...
አንዲት የጠቆረች...
እብድ የተሰኘች... እስከምታነሳው።።።።


በአቤኒ የተፃፈ


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.4K views10:22
Open / Comment
2021-12-20 10:08:43 አሜን በይ አደራ

ያየሽ አይኑ ይጥፋ
እግርና እግሩን ያርግበት ወልካፋ።

ቡዳ እንደበላዉ ልጅ አይኑ ፈጦ ይቅር አንቺኑ ያየበት
አናቱ ቅል ይሁን አንቺን ያሰበበት
ልቡ ስራ ታቁም ካንቺ የከጀለበት።

ፍቅርሽ እስክመጣ
ፍቅር የተባለ ከወንድ መኖ ይዉጣ
ጠንጋራ ያድርገዉ አንቺን ሊያይ የመጣ።

በፈገግታ ማርኮ ቀልብሽን ለሻተ
ጥርሶቹን አግጥጦ ለተንከራተተ
መጋኛ አግኝቶልኝ ከንፈሩን ያጣመዉ
ጥርሶቹን አርግፎ በድዱ ያስቀረዉ።

እኔ ያንቺዉ መዉደድ ስቃይ እንዳይገባኝ
ቅናት እንዳይገባኝ
ፍርሀት እንዳይገባኝ
ችግር እንዳይገባኝ

የሀገሬዉ ተባዕት በርሀብ ይቀጣ
ሆዱን እያሰበ ወዳንቺ እንዳይመጣ።

የሚበላዉ ይጣ
የሚጠጣዉ ይጣ።
በቃላት ሊያጠምድሽ አንደበቱ ናፍቆ ስምሽን የጠራ
ያሰበዉም ቢሆን ከኔ ፍቅር ጋራ።

ሀረግ ሊደረድር ተፈጥሮ የሰራዉ
ጉሮሮ፣ትናጋ፣ምላስ ከከንፈሩ
ላንቃዉም ሳይቀሩ
የጨዉ ሀዉልት ሆነዉ እዛዉ ደርቀዉ ይቅሩ።

ብቻ ግን አደራ ይሄ ሁሉ ሲሆን
አንዱን አያሳይሽ እንዳይገባሽ ሀዘን
ሲከፋሽ አልወድም።

በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ

@Tizita_wolde

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.0K views07:08
Open / Comment
2021-12-19 16:07:01 ከግጥሞቼ

ነፍስ ይማር ይበልህ የገደልከዉ ልቤ
በቁም ተስካር ላዉጣ መሞቴን ተርቤ።

ተፃፈ በሰላም
For any comment @selamnen

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.4K views13:07
Open / Comment
2021-12-19 11:50:51 @Tizita_wolde

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.4K viewsedited  08:50
Open / Comment
2021-12-19 09:11:40 ለምን ልኑር እኔ ማንን ይድላው ብዬ
ልሙት ልውደም እንጂ ይኸው ነው አጣዬ
ጤና ይንሳኝ አምላክ በህመም ልማቅቅ
ከፍታ እያማረኝ ስንኩል ሆኜ ልውደቅ
ጥጋብ ከቶ አይጎብኘኝ
ጠኔ ፀንቶ ያድቅቀኝ
መውደቅ ነው ሚያምርብኝ ለምን ቆሜ ልገኝ
ልጥፋ ከምድረ ገፅ መኖር ምን ሊጠቅመኝ
ኑሮ ብሎ መጥራት 'ላፍ እያሳቀቀኝ
መሞትም መኖርም መብላትም መራብም
መልበስ መታረዝም ማግኘትም ማጣትም
ሁሉ አንድ ከሆነ መለየት ካቃተው
ኑሮ ካሉት አይቀር መቃብር አለም ነው፡፡

Nuniyat
@yetyelele1


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
797 views06:11
Open / Comment