🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ገራዶ ሚዲያ

Logo of telegram channel geradomedia — ገራዶ ሚዲያ
Logo of telegram channel geradomedia — ገራዶ ሚዲያ
Channel address: @geradomedia
Categories: News
Language: English
Subscribers: 679
Description from channel

🔸ሁሉን አቀፍ የመረጃ ምንጭ!🔸
✍ ፃፉልን @geradomediabot
fb.com/geradomedia
twitter.com/geradomedia

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages 52

2021-02-12 18:36:23
ግብፅ

አልጠግብ ባይ

PIC Credit: Journalist Silabat Manaye

t.me/geradomedia
6.0K viewsKedir Ahmed, 15:36
Open / Comment
2021-02-12 16:06:18 አሜሪካ እና ተመድ በትግራይ ጉዳይ የኢትዮጵያን ጥረት መደገፍ እንደሚቀጥሉ ገለጹ!

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ትናንት በስልክ ባደረጉት የትውውቅ ቆይታ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ መክረዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረገጹ እንዳስታወቀው፣ ሁለቱ ግለሰቦች ከተወያዩባቸው ጉዳዮች መካከል በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ያለው ወቅታዊ ጉዳይ ይገኝበታል፡፡

ኢትዮጵያን በተመለከተው ውይይታቸው፣ ሁለቱም በትግራይ ለተፈጠረው ቀውስ ምላሽ ለመስጠት የኢትዮጵያን ጥረት ለመደገፍ ያላቸውን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጠዋል፡፡

ሚስተር ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በቅርቡ በነበራቸው የስልክ ውይይት ወቅትም በትግራይ ክልል መንግስት የሚሰራውን ስራ አሜሪካ እንደምትደግፍ ገልጸው ሰብዓዊ ድርጅቶች በክልሉ እንዲንቀሳቀሱ መንግስት ሙሉ ፈቃድ እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡

በመከላከያ ሰራዊት እና በሕወሓት ኃይል መካከል በትግራይ ክልል የተካሔደው ውጊያ በርካታ ቀውሶችን ማስከተሉ ይታወቃል፡፡ ከነዚህም መካከል የንጹኃን መፈናቀል እና የሰብአዊ ቀውስ ይገኙበታል፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችም በክልሉ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እና መደረግ ያለባቸውን ተግባራት በተመለከተ ሪፖርቶችን አውጥተዋል፡፡

የሰብዓዊ ድጋፍ ድርጅቶች ያለምንም ገደብ ወደ ክልሉ እንዲገቡ እና ድጋፍ እንዲያደርሱ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ የተለያዩ መንግስታት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጫና ሲያሳድሩ ቆይተዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ከሰብዓዊ ድርጅቶች ጋር በደረሰው ስምምነት መሰረት የተለያዩ ድርጅቶች ወደ ክልሉ ገብተው በመስራት ላይ መሆናቸው በተለያዩ ጊዜያት ይፋ ሆኗል፡፡ የሰላም ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ በትግራይ ክልል የሰላም ማስከበር ሂደቱን ተከትሎ ላለፋት 3 ወራት የተባበሩት መንግስታት ልዩ ልዩ ድርጅቶችን ጨምሮ ከ26 በላይ አለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በጥምረት የሰብዓዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ተግባራን ለማገዝ ሰፊ እንቅስቃሴ ሲደረግ እንደቆየ አስታውቋል፡፡

ባለፉት 3 ወራት በቦታው ተገኝተው ድጋፍ ለማድረግ ላመለከቱ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና ዓለም አቀፍ መመዘኛን አሟልተው ለተገኙ 75 አባላት ወደ ትግራይ ክልል በመግባት የሰብዓዊ ድጋፍ ሂደቱን እንዲያግዙ ፈቃድ መስጠቱንም ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው፡፡

የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ድጋፍ አስተባባሪ የኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት (UN-OCHA) የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፉንና የመልሶ ማቋቋም ሂደቱን በማስተባበር ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በቅንጅት እያሰራ ይገኛልም ብሏል መግለጫው።

ከኢትዮጵያ ጉዳይ በተጨማሪ በሌሎች ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይም የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የተመደወ ዋና ፀሐፊ ተወያይተዋል፡፡ አሜሪካ ወደ ዓለም ጤና ድርጅት መመለሷን እንዲሁም በኮሮና ቫይረስ ፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና መሰል ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ከተባበሩት መንግስታት እና በስሩ ከሚገኙ ድርጅቶች ጋር በትብብር እንደምትሰራ ብሊንከን ለጉተሬዝ አረጋግጠዋል፡፡

(Via AlAin Amharic)

t.me/geradomedia
5.7K viewsGashu, 13:06
Open / Comment
2021-02-12 16:05:31
5.2K viewsGashu, 13:05
Open / Comment
2021-02-11 20:13:53
"በትግራይ ክልል የኤርትራ ወታደሮች እንደፈለጉ እየገቡና እየወጡ ነው" - ኢዜማ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፓርቲ ኢዜማ በክልሉ የተፈጠረውን ጦርነት ተከትሎ ወደ ስፍራው ባቀናበት ወቅት የኤርትራ ወታደሮች ሲንቀሳቀሱ ተመልክቻለሁ ብሏል፡፡ ፓርቲው የአካባቢው ነዋሪዎች ነገሩኝ ብሎ እንደተናገረው ባሁኑ ሰአት የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ክልል እንደፈለጉ ይንቀሳቀሳሉ ሲል አስታውቋል፡፡

እንደዚሁም የሁመራ አካባቢ ነዋሪዎች ለፓርቲው እንደተናገሩትም የኤርትራ ወታደሮች ባካባቢው ባይገኙ ኖሮ በነዋሪው ዘንድ ከፍተኛ እልቂት ይፈጠር ነበር ሲሉ ነግረውናል ሲል ነው ፓርቲው ያስታወቀው፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፓርቲ ኢዜማ ወደ ኮንሶ፣ መተከል፣ ማይካድራ እና መቐለ ልዑክ ቡድን በመላክ በስፍራዎቹ የተፈጠረውን ሁኔታ ለማጣራት ሙከራ አድርጎ በዛሬው እለት ምልከታውን ይፋ አድርጓል፡፡

የማካይዳራ ነዋሪዎችም አሁንም ሳምሪ በተሰኘው ቡድን፣ ተቆርጠው በቀሩ የህዋሃት ቡድን ታጣቂዎች እና በሱዳን ጦር ጥቃት ሊደርስብን ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው ገልፀዋል።

ወደ መቐለ የተጓዘው የኢዜማ ከፍተኛ ቡድን በመጠለያ ያሉ ወገኖች ተዟዙሮ ከማየት ጎን ለጎን በቦታው ከነበሩ የፌደራል መንግሥት ባለሥልጣናት፣ ከትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር እንዲሁም ከተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ጋር አሁን ስላለው ነባራዊ ሁኔታ እና መፍትሔዎች ላይ ውይይት ማድረጉን ገልጿል፡፡ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከዶ/ር ሙሉ ነጋ ጋር በመገናኘት ‹‹በክልሉ አመራር የነበሩ ታዋቂ ፖለቲከኞችን ፤ ታዋቂ ግለሰቦችን እና የሌሎች ፓርቲዎች አባላት በመዋቅሩ ውስጥ አካተው ቢጠቀሙባቸው ጥሩ እንደሚሆን ፓርቲው ጠቁሟል፡፡

(ኢትዮ ኤፍ ኤም)

t.me/geradomedia
6.9K viewsGashu, 17:13
Open / Comment
2021-02-11 20:13:44 በአጭር ጊዜ ውስጥ የሴት ጓደኛ እንድትኖርክ ትፈልጋለህ

በአጭር ጊዜ ውስጥ የወንድ ጓደኛ እንዲኖርሽ ትፈልጊያለሽ

ስለፍቅር ጥልቅ እውቀት እንዲኖራችሁ
OPEN የሚለውን ብቻ ይጫኑ!

OPEN
1.7K viewsGashu, 17:13
Open / Comment
2021-02-11 17:29:03
የአፋር ክልል በትግራይ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ አደረገ!

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳዳር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ የአፋር ክልል ሕዝቦች በትግራይ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ያበረከቱትን ድጋፍ ተቀብለዋል። የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና ሕዝብ ከዘጠኝ ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ድጋፉን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኤለማ አቡበከርና የአፋርን ሕዝብ የወከሉ የሃገር ሽማግሌዎች መቐለ ተገኝተው አስረክበዋል፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳዳር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ የአፋርና የትግራይ ሕዝቦች በደምና በታሪክም የተሳሰሩ፣ መቼም መለያየት የማይችሉ ናቸው ብለዋል፡፡

የትግራይ ሕዝብ ከገጠመው ችግር እንዲወጣ ሁልጊዜም ከጎናቸው ያልተለዩ መሆናቸውንም ገልፀዋል። የዛሬው ድጋፍም የአፋር ሕዝብ ለትግራይ ሕዝብ ያለውን አለኝታነት የገለጸበት መሆኑን ነው የተናገሩት።

የሁለቱ ሕዝቦች ወንድማማችነትና ትስስር ከመቼውም ጊዜ በላይ የሚጎለብት መሆኑንም ዋና ስራ አስፈፃሚው ገልፀዋል፡፡ ድጋፉ የመልካም ጉርብትና መገለጫ መሆኑን በመጥቀስ የአፋርን ሕዝብና መንግስትንም አመስግነዋል፡፡

የአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኤለማ አቡበከር ሁለቱ ሕዝቦች ችግሮችና መልካም አጋጣሚዎችን በጋራ ያሳለፉ መሆናቸውን በማውሳት የትግራይ ሕዝብ ለደረሰበት ጉዳት ከ2 ሺህ 700 ኩንታል በላይ የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸውን ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ ቀደም የኦሮሚያና የደቡብ ክልሎች እንዲሁም የአዲስ አበባ አስተዳደር በትግራይ ለተጎዱ ወገኞች ድጋፍ አድርገዋል። #ENA

t.me/geradomedia
5.9K viewsGashu, edited  14:29
Open / Comment
2021-02-11 16:45:43
በትግራይ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኞች ፈተናውን በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ይወስዳሉ ተባለ!

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒኤችዲ) በትግራይ ክልል የሚገኙ ከ12ሺ ህ በላይ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች በአካባቢው የትምህርት መሰረተ-ልማቶች ሙሉ ለሙሉ በመውደማቸው ፈተናቸውን በአካባቢያቸው በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት (ዩኒቨርስቲዎች) ውስጥ እንደሚወስዱ ገልፀዋል፡፡

በዚህም መሰረት ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ተፈታኞች በአካባቢያቸው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እና ትምህርት ቢሮዎች ሪፖርት እንዲያደርጉ ተጠይቋል፡፡ በሚቀጥሉት ሳምንታትም ተፈታኞችን በክልሉ ወደሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የማጓጓዝ ስራዎች እንደሚሰሩ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

ተፈታኞቹ ፈተናቸውን የሚወስዱባቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም መቐለ፣ አክሱም፣ አዲግራት እንዲሁም ራያ የኒቨርስቲዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ፈተናው ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 2 ቀን 2013 ድረስ እንደሚሰጥ ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

Via MoE

t.me/geradomedia
5.7K viewsGashu, 13:45
Open / Comment
2021-02-11 10:48:20
የ12ኛ ክፍል ፈተና የካቲት 29 ይሰጣል ተባለ!

የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና የካቲት 29 ቀን እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። ከየካቲት 22 እስከ 24 ቀን 2013 የዲጂታል መታወቂያ ይሰራጫልም ብሏል።

የፈተናው ገለጻ የካቲት 26 ቀን ተካሂዶ ፈተናው ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥም ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡ በቀጥታ (ኦንላይን) ይሰጣል ተብሎ የነበረው ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥም የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ገልጸዋል፡፡ ሚኒስቴሩ በፈተና አሰጣጡ ላይ ለተፈጠረው መዘግየትም በይፋ ይቅርታ ጠይቋል። #FBC

t.me/geradomedia
5.9K viewsGashu, edited  07:48
Open / Comment
2021-02-10 20:53:18
የምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር ይፋ ተደረገ!

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው 6ኛው አገር አቀፍ የምርጫ ሰሌዳ ላይ በተገለጸው መሰረት ዛሬ የካቲት 3 ቀን የምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር ይፋ ማድረጊያ ቀን ነው። በዚህም መሰረት በዛሬው እለት ቦርዱ የምርጫ ምልክት በመውሰድ ለምርጫ ለመወዳደር ዝግጅት እያደረጉ ያሉ ሁሉም ፓርቲዎች የምርጫ ጣቢያዎቹን ዝርዝር በፍላሽ እንዲደርሳቸው ማድረጕን አስታወቋል።

የምርጫ ጣቢያዎቹን ዝርዝር በምርጫ ቦርዱ ድረ-ገፅ ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል። በዚህ መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ (1,848)፣ በሲዳማ ክልል (2,247)፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል (699)፣ አፋር ክልል (1,432)፣ አማራ ክልል (12,199)፣ ድሬዳዋ (305)፣ ጋምቤላ ክልል (431)፣ ሃረሪ ክልል (285)፣ ኦሮሚያ ክልል (17,623)፣ ደ/ብ/ብ/ህ ክልል (8,281)፣ ሶማሌ ክልል (4,057) ምርጫ ጣቢያዎች አሉ።

በአጠቃላይ 49 ሺህ 407 የምርጫ ጣቢያዎች ለ6ተኛው ጠቅላላ ምርጫ አገልግሎት የሚሰጡ ሲሆን የምርጫ ጣቢያዎቹን ዝርዝር ከስር ከሚገኘው ሊንክ ላይ ማግኘት ይቻላል። #AMN

https://nebe.org.et/am/polling-stations

t.me/geradomedia
5.7K viewsGashu, edited  17:53
Open / Comment
2021-02-10 20:53:08 በአጭር ጊዜ ውስጥ የሴት ጓደኛ እንድትኖርክ ትፈልጋለህ

በአጭር ጊዜ ውስጥ የወንድ ጓደኛ እንዲኖርሽ ትፈልጊያለሽ

ስለፍቅር ጥልቅ እውቀት እንዲኖራችሁ
OPEN የሚለውን ብቻ ይጫኑ!

OPEN
886 viewsGashu, 17:53
Open / Comment