Get Mystery Box with random crypto!

ገራዶ ሚዲያ

Logo of telegram channel geradomedia — ገራዶ ሚዲያ
Logo of telegram channel geradomedia — ገራዶ ሚዲያ
Channel address: @geradomedia
Categories: News
Language: English
Subscribers: 679
Description from channel

🔸ሁሉን አቀፍ የመረጃ ምንጭ!🔸
✍ ፃፉልን @geradomediabot
fb.com/geradomedia
twitter.com/geradomedia

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages 55

2021-02-07 17:11:01 ዛሬ የተመረቀው ቡሬ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ....

የቡሬ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ በፌደራል ደረጃ ከተመረጡ አራት ሞዴል አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች አንዱ በመሆን ጥር 25/2009 የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል።

በ2010 ነበር ለመንግሥት የልማት ድርጅቶች የሥራ ውል ተሰጥቶ ወደ ግንባታ ተገብቷል።

የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኩ የመጀመሪያ የግንባታ ምዕራፍ በ260 ነጥብ 35 ሄክታር መሬት ላይ ነበር በ2010 የተጀመረው። በአጠቃላይ ፓርኩ በ1 ሽህ ሄክታር ላይ ይለማል።

ለቡሬ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ 7 መጋቢ የገጠር የሽግግር ማዕከላት አሉት። ማዕከላቱም ሞጣ፣ አማኑኤል፣ ፍኖተሰላም፣ ዳንግላ፣ መርዓዊ፣ እንጅባራ እና ቻግኒ ይገኛሉ።

የቡሬ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ትምህርት ቤትን፣ የህፃናት ማቆያን፣ ክሊኒክን፣ መኖሪያ ህንፃና ሌሎችም ማኅበራዊ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ይገኙበታል።

ፓርኩ በዋናነት የሚያካትታቸው ኢንዱስትሪ አይነቶች የግብርና ምርትን በግብዓትነት የሚጠቀሙና የሚያቀነባብሩ፣ ምርታቸውን በጋራ ወይም በተናጠል ወደ ውጭ የሚልኩ፣ ለግብርናው ምርት መዘመን መሰረት የሚሆኑ፣ የተሻሻለ ቴክኖሎጅ የሚያስተዋውቁ፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ አስተዋጽኦ ያላቸውና ሌሎችም ይገኙበታል።

የምግብ መጠጥና ፋርማሲቲዮካል፣ የጥራጥሬና ቅባት እህል ውጤቶች ማቀነባባሪያ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ማቀነባበሪያ፣ የእንስሳትና የእንስሳት ተዋጽኦ ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎችና ሌሎችም በፓርኩ እንዲለሙ የተፈቀዱ የኢንዱስትሪ ዓይነቶች ናቸው።

ፓርኩ ደረጃውን የጠበቀ 13 ኪ.ሜ ኮንክሪት አስፓልት መንገድ፣ የውሃ መስመር ዝርጋታ፣ ማከሚያና ማከማቻ፣ መካከለኛና አነስተኛ የመብራት መስመር ግንባታ፣ የቴሌ-ኮም መስመር፣ የመረጃ ማዕከል፣ የገበያ ማዕከል፣ የስልጠና ማዕከል፣ የእሳት አደጋ መከላከያ ማዕከል፣ የፖሊስ ጣቢያ፣ የጉምሩክና ጥበቃ ማዕከል፣ ሞዴል የኢንዱስትሪ ሸዶች፣ ሁለገብ የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከል እና ሌሎችም መሰረተ ልማቶች አካቷል።

ምንጭ፦ የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን

t.me/geradomedia
5.0K viewsGashu, 14:11
Open / Comment
2021-02-07 17:09:51
4.5K viewsGashu, 14:09
Open / Comment
2021-02-07 14:26:00
የሰብዓዊ እርዳታ በትግራይ ክልል.....

የኢትዮጵያ መንግሥት እና የዓለም ምግብ ፕሮግራም በትግራይ ክልል በጋራ ሰብአዊ እርዳታ ለማድረስ ስምምነት ላይ ደርሱ። ስምምነት ላይ የተደረሰው የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ከተመድ የዓለም ምግብ ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ዴቪስ ቤስሊ (ዶ/ር) ጋር በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለው የሰብአዊ ድጋፍ ሁኔታ በጋራ የመስክ ጉብኝት ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው።

በመስክ በተካሄደ ምልከታ መቐለ የሚገኘው የእህል ማከማቻ ለቀጣይ ሁለት ወራት 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎችን መመገብ የሚያስችል የምግብ ክምችት መኖሩን ባለሥልጣናቱ ማረጋገጣቸውን የሰላም ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።

በክልሉ የእርዳታ ስርጭት ተደራሽነትን ለማስፋት በ36 ወረዳዎች 92 የምግብ ማሰራጫ ማእከላት እንደተከፈቱ እና ከ92 ማእከላት አራቱ ስደተኞች ያሉባቸውን ቦታዎች የሚሸፍኑ እንደሆነም ታውቋል።

እስካሁን ባለው እንቅስቃሴ በክልሉ የሚገኙ ሰብአዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎችን ተደራሽ ማድረግ እንደተቻለ እና የመንግሥት ድርሻ 70 ከመቶ መሆኑን ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ገልጸዋል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቤስሊ በበኩላቸው የሰብአዊ ድጋፍ ለሚመለከታቸው ዜጎች እየደረሰ እንደሆነ መመልከታቸውን ገልፀው፣ በቀጣይ ለሚከናወኑ ድጋፎች ድርጅታቸው አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። #EBC

t.me/geradomedia
5.0K viewsGashu, edited  11:26
Open / Comment
2021-02-07 12:42:25
5.3K viewsGashu, 09:42
Open / Comment
2021-02-06 20:21:53
#የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ

የኮቪድ-19 ቁሳቁስን ሲያጓጉዝ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሁን ደግሞ የቫይረሱን ክትባት ወደ አፍሪካ አህጉር ማጓጓዝ መጀመሩን በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ አሳውቋል።

t.me/geradomedia
5.9K viewsGashu, 17:21
Open / Comment
2021-02-06 14:06:22
በትግራይ ክልል የሰብአዊ ድጋፍ ስርጭት ያለበትን ሁኔታ የሚመለከት ልዑክ መቐለ ገባ!

በሠላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚልና በዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቤስሊ የተመራ የልዑካን ቡድን በትግራይ ክልል የሰብአዊ ድጋፍ ስርጭት ያለበትን ሁኔታ ለመመልከት መቐለ ገባ።

የልዑክ ቡድኑ አባላት በትግራይ ክልል በሚኖራቸው ቆይታ በመቀሌና በአካባቢው እንዲሁም በኩሃ ያለውን የሰብአዊ ድጋፍ ስርጭት ሁኔታን ተዘዋውረው እንደሚጎበኙ ኢዜአ ዘግቧል።

በተጨማሪም በትግራይ ክልል እየተሰጠ ባለው የሰብአዊ ድጋፍ ዙሪያ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደርና ከብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሥራ ኃላፊዎች ጋር እንደሚወያዩም ይጠበቃል።

t.me/geradomedia
6.3K viewsGashu, 11:06
Open / Comment
2021-02-06 14:06:07 በአጭር ጊዜ ውስጥ የሴት ጓደኛ እንድትኖርክ ትፈልጋለህ

በአጭር ጊዜ ውስጥ የወንድ ጓደኛ እንዲኖርሽ ትፈልጊያለሽ

ስለፍቅር ጥልቅ እውቀት እንዲኖራችሁ
OPEN የሚለውን ብቻ ይጫኑ!

OPEN
3.5K viewsGashu, 11:06
Open / Comment
2021-02-06 13:17:42
34ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ተጀምሯል!

34ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ እንደወትሮው ሁሉ መሪዎችን በአካል ባያገናኝም የውይይት አጀንዳዎችን በመምረጥ በበይነ መረብ መካሄድ ጀምሯል፡፡ የሕብረቱ መሪዎች ስብሰባውን በአካል ያላደረጉበት ምክንያት የኮሮና ቫይረስ ሲሆን ወረርሽኙም አንዱ የጉባዔው አጀንዳ ነው፡፡ በዚህም መሰረት የመሪዎቹ ጉባዔ ዛሬና ነገ ይካሄዳል፡፡

የአፍሪካ አህጉር የኮሮና ክትባቶችን በፍትሃዊ መንገድ እንዲያገኝ የሚለው ጉዳይ በመሪዎቹ ውይይት እንደሚደረግበት ይጠበቃል፡፡ በአፍሪካ ያላባሩት ግጭቶች፣ ጽንፈኝነት እና ሽብርተኝነትም በጉባዔው ውይይት እንደሚደረግባቸው ይጠበቃል፡፡ ሕብረቱ ቀደም ብሎ እንደገለጸው ወደ ሥራ የገባው የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነትም በአሁኑ የመሪዎች ጉባዔ ላይ ሌላ አጀንዳ ነው፡፡

ምንም እንኳን እንደከዚህ ቀደሙ የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት መሪዎች በአዲስ አበባ ባይገኙም አጀንዳዎቹ በቀጥታ በበይነ መረብ ውይይት ይደረግባቸዋል፡፡ ተሰናባቹ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ ያለፈው አንድ ዓመት የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር የነበሩ ሲሆን ኃላፊነቱን ዛሬ ለዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አቻቸው አስረክበዋል፡፡ ለሚቀጥሉት 12 ወራት ሕብረቱን የሚመሩት የዲ.አር. ኮንጎ ፕሬዝደንት ፌሊክስ ቺሲኬዲ ኃላፊነቱን ለመረከብ ትናንት ምሽት ነው አዲስ አበባ የገቡት፡፡

የሕዳሴ ግድቡን ድርድርም በቀጣይነት በአፍሪካ ሕብረት ጥላ ስር ፕሬዝደንት ፌሊክስ ቺሲኬዲ የሚመሩ ይሆናል፡፡ ተሰናባቹ የሕብረቱ ሊቀመንበር ሲሪል ራማፎዛ 34ኛውን የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ካሉበት ፕሪቶሪያ ሆነው በቀጥታ ከፍተዋል፡፡

(Via AlAin)

t.me/geradomedia
5.4K viewsGashu, 10:17
Open / Comment
2021-02-06 09:47:44
#መረጃዎችን_እናጣራ

ሀሰት የሆነን መረጃ ከወዳጃችን/ቤተሰባችን ስለተላከልን ብቻ ሳናጣራ በስህተት ከማሰራጨት እንቆጠብ። ወዳጃችንም/ቤተሰባችንም ሀሰተኛ መረጃውን በስህተት/በመታለል ልኮልን ሊሆን ይችላልና። ስለዚህ መረጃዎችን እናጣራ!

#Misinformation #Disinformation

t.me/geradomedia
5.4K viewsGashu, 06:47
Open / Comment
2021-02-06 09:46:36 በአጭር ጊዜ ውስጥ የሴት ጓደኛ እንድትኖርክ ትፈልጋለህ

በአጭር ጊዜ ውስጥ የወንድ ጓደኛ እንዲኖርሽ ትፈልጊያለሽ

ስለፍቅር ጥልቅ እውቀት እንዲኖራችሁ
OPEN የሚለውን ብቻ ይጫኑ!

OPEN
1.3K viewsGashu, 06:46
Open / Comment