Get Mystery Box with random crypto!

ገራዶ ሚዲያ

Logo of telegram channel geradomedia — ገራዶ ሚዲያ
Logo of telegram channel geradomedia — ገራዶ ሚዲያ
Channel address: @geradomedia
Categories: News
Language: English
Subscribers: 679
Description from channel

🔸ሁሉን አቀፍ የመረጃ ምንጭ!🔸
✍ ፃፉልን @geradomediabot
fb.com/geradomedia
twitter.com/geradomedia

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages 56

2021-02-05 21:55:03
የአፍሪካ ኅብረትና የጆ ባይደን አስተዳዳር....?

የአሜሪካው አድስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳዳር ከአፍሪካ ኅብረት ጋር ጠንካራ ትስስርን እንደገና ለመገንባት ቁርጠኛ መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስታወቁ፡፡

ፕሬዝዳንቱ በውጭ ጉዳይ ፖሊሲያቸው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ገለፃ ካደረጉ በኋላ በሰጡት አስተያየት ከአፍሪካ ኅብረት ጋር ያለውን ትስስር እንደገና እንደሚገነቡት ቃል ገብተዋል፡፡

ቀዳሚያቸው ዶናልድ ትራምፕ ከ2 ዓማት በፊት ‹‹አፍሪካዊያንን የማይረቡ አገራት ያሉበት አኅጉር›› ሲሉ መግለፃቸው ቁጣን ቀስቅሶ እንደነበርና ኅብረቱን ከዩናይትድ ስቴትስ ማራራቁ ይታወቃል፡፡

ምንም እንኳን ትራምፕ ‹‹እኔ ዘረኛ አይደለሁም›› ሲሉ ሊያስተባብሉ ቢሞክሩም በተግባር ግን ለጥቁር ቆዳ ቀለም ሕዝቦች ያላቸው ጥላቻ በተለያየ ጊዜ ሲገለጥ ኖሯል፡፡

ነጩን ቤተ መንግሥት የተረከቡት ባይደን ግን ከኅብረቱ ጋር የነበረውን ጠንካራ ትስስር እንደሚመልሱት ነው የገለፁት፡፡ ፕሬዝዳንቱ አክለውም ኅብረቱ በአኅጉሪቱ ያሉ ግጭቶችን በመፍታት ጠንካራ እንዲሆን እገዛ እንደሚያደርጉ ነው ያሳወቁት፡፡

ዩናይትድ ስቴትስና አፍሪካ በባራክ ኦባማ ዘመንም ጠንካራ ትስስር ነበራቸው፡፡ (AhaduTV)

t.me/geradomedia
5.5K viewsGashu, 18:55
Open / Comment
2021-02-05 21:54:39 በአጭር ጊዜ ውስጥ የሴት ጓደኛ እንድትኖርክ ትፈልጋለህ

በአጭር ጊዜ ውስጥ የወንድ ጓደኛ እንዲኖርሽ ትፈልጊያለሽ

ስለፍቅር ጥልቅ እውቀት እንዲኖራችሁ
OPEN የሚለውን ብቻ ይጫኑ!

OPEN
2.2K viewsGashu, 18:54
Open / Comment
2021-02-05 21:10:34 የጡረታ መዋጮ የማይከፍሉ የግል ድርጅቶች የንግድ ፍቃዳቸው እንዳይታደስ የሚያደርግ አሠራር ተዘረጋ!

የጡረታ መዋጮ የማይከፍሉ የግል ድርጅቶች የንግድ ፍቃዳቸው እንዳይታደስ የሚያደርግ የጋራ አሠራር መዘርጋቱን የግል ድርጅቶች ማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ አስታወቀ። አብዛኞቹ የግል ድርጅቶች የሠራተኞቻቸውን የጡረታ መዋጮ በአግባቡ እየከፈሉ ቢሆንም፣ አንዳንዶች ጊዜውን ጠብቀው ያለመክፈል፣ የተወሰኑት ደግሞ ከእነጭራሹ እንደማይከፍሉ ሁኔታ መኖሩን ኤጀንሲው ገልጿል።

የኤጂንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ገመቹ ወዩማ፣ ከጡረታ መዋጮ ጋር በተያያዘ በአንዳንድ ድርጅቶች ላይ የሚስተዋለውን መዘግየት እና ለመክፈል አለመፈለግ ችግሮች ለመፍታት በአካል ጭምር በመሄድ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ሲሠራ መቆየቱን ተናግረዋል። በመሆኑም በተለያዩ ምክንያቶች የጡረታ መዋጮ የማይከፍሉ ድርጅቶች እንዲከፍሉ እና ሓላፊነታቸውን እንዲወጡ ለማድረግ ኤጀንሲው ከገቢዎች ሚኒስቴር ጋር ቅንጅታዊ አሠራር መዘርጋቱን ጠቁመዋል።

በዚሁ መሠረት የጡረታ መዋጮ የማይከፍሉ የግል ድርጅቶች በዓመቱ መጨረሻ የንግድ ፈቃድ እድሳት እንዳይደረግላቸው የሚያደርግ አሠራር ተዘርግቷል ነው ያሉት። ኤጀንሲው በበጀት ዓመቱ አጋማሽ ከግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ መዋጮ ክፍያ 5 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ገቢ መገኘቱን የገለጹት አቶ ገመቹ፣ ገቢው በስድስት ወራት ለመሰብሰብ ከታቀደው 106 በመቶ መሆኑንም መናገራቸውንም ኢዜአ ዘግቧል።

t.me/geradomedia
5.1K viewsGashu, edited  18:10
Open / Comment
2021-02-05 19:20:06
ኤርትራ የዩናይትድ ስቴትስን መግለጫ እንደማትቀበለው ገለፀች!!

የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገ/መስቀል ዛሬ በኤርትራ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ የፌስቡክ ገፅ ላይ የወጣውን መግለጫና ሀገሪቱን በሚመለከት እየተሰራጨ ያለውን ሀሰተኛ እና ግምታዊ ውንጀላ ሀገራቸው እንደማትቀበለው ገልፀዋል። ኤርትራ በትግራይ ውሥጥ ወታደሮቿ እንደሚገኙ/በትግራይ ክልል ጦርነትም እንደተሳተፈች በተደጋጋሚ በተለያየ መልኩ ቢገለፅም የሀገሪቱ መንግስት ጉዳዩን እያስተባበለ ይገኛል። #Tikvah

t.me/geradomedia
5.3K viewsGashu, 16:20
Open / Comment
2021-02-05 19:15:35 በአጭር ጊዜ ውስጥ የሴት ጓደኛ እንድትኖርክ ትፈልጋለህ

በአጭር ጊዜ ውስጥ የወንድ ጓደኛ እንዲኖርሽ ትፈልጊያለሽ

ስለፍቅር ጥልቅ እውቀት እንዲኖራችሁ
OPEN የሚለውን ብቻ ይጫኑ!

OPEN
1.8K viewsGashu, 16:15
Open / Comment
2021-02-05 16:31:26
የህዳሴ ግድብ ግንባታ 78.3 በመቶ አፈጻጸም ላይ ደረሰ!

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈጻጸም 78 ነጥብ 3 መድረሱን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ። ሚኒስቴሩ ባለፉት ስድስት ወራት ያከናወናቸውን ተግባራትና የግድቡን ግንባታ ሂደት በተመለከተ መግለጫ የሰጡት የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ እንደገለጹት፤ የግድቡ ግንባታ የሲቪል ስራዎች አፈጻጸም 91 በመቶ ደርሷል።

አጠቃላይ የግድቡ ግንባታ አፈጻጸም ደግሞ 78 ነጥብ 3 በመቶ መድረሱን አመልክተዋል። በቀጣይ ወራት የግድቡን ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ለማሳካት እንደሚሰራ መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

t.me/geradomedia
5.4K viewsGashu, 13:31
Open / Comment
2021-02-05 12:22:05
በትግራይ ቀውስ የዩናይትድ ስቴትስ ስጋትና ጥያቄ....

የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በትግራይ ክልል ባለው ቀውስ ስጋት እንዳደረባቸው ገልፀው ተጨማሪ የሰው ሕይወት እንዳይጠፋ ያልተገደበ የሰብኣዊ እርዳታ ሊደረግ ይገባል አሉ፡፡

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር በስልክ የተወያዩት ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ እና ሊካሄድ የታሰበው ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አገራቸው ድጋፍ እንደምታደርግ ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በበኩላቸው ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ሁሉን ዐቀፍ ለውጥ ለመደገፍ ላሳየችው ተነሳሽነት ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል፡፡

በሌላ ዜና ዩናይትድ ስቴትስ ‹‹በትግራይ ክልል የኤርትራ ወታደሮች እንዳሉ የሚያሳይ ተጨባጭ መረጃ አለኝ፤ የሰብኣዊ መብት ጥሰትንም እየፈፀሙ ነው›› በማለት በአስቸኳይ እንዲወጡ መጠየቋን በኤርታር የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ አሳውቋል፡፡

በክልሉ የተፈፀሙ ፆታዊ ጥቃት፣ ዘረፋ በስደተኛ ካምፖች ላይ ጥቃት እና ሌሎችም የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች በገለልተኛ አካል ተጣርተው ተጠያቂ መሆን ያለባቸው ሰዎች ሕግ ፊት እንዲቀርቡ መጠየቄን እቀጥላለሁም ነው ያለችው፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ምርመራውን በራሴ አቅም አከናውናለሁ የሚል አቋም ነው ያለው፡፡

የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥታት በትግራይ ክልል የኤርትራ ወታደሮች ተሳትፎ አለ የሚለውን ሪፖርት እንደማይቀበሉት ሲገልፁ ከርመዋል፡፡ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ወደ አስመራ ‹‹ሮኬት ሲተኮስብት የነበረ ኃይል ወደ ድንበር አይጠጋም ማለት አይቻልም›› ከሚል ምላሽ በስተቀር ወደ ኢትዮጵያ ሉኣላዊ ግዛት የሆነችው ትግራይ ገብቷል የሚል መረጃን አይቀበለም፡፡

(አሐዱ ቴሌቪዥን)

t.me/geradomedia
5.6K viewsGashu, 09:22
Open / Comment
2021-02-05 12:21:53 በአጭር ጊዜ ውስጥ የሴት ጓደኛ እንድትኖርክ ትፈልጋለህ

በአጭር ጊዜ ውስጥ የወንድ ጓደኛ እንዲኖርሽ ትፈልጊያለሽ

ስለፍቅር ጥልቅ እውቀት እንዲኖራችሁ
OPEN የሚለውን ብቻ ይጫኑ!

OPEN
2.1K viewsGashu, 09:21
Open / Comment
2021-02-05 10:37:40
#ቀለብ_ከተማሪ

ከወራት በፊት ጦርነትን ካስተናገዱ የትግራይ ክልል ከተሞች መካከል አንዷ በሆነችው መቐሌ የሚገኘው የመቐሌ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎቹን ከነገ ጀምሮ መቀበል ይጀምራል። ተማሪዎችም ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲመጡ በጦርነቱ ምክንያት ለችግር ለተዳረጉ ነዋሪዎች የሚሆኑ ለቀን ፍጆታ የሚውሉ ግብዓቶችን ይዘው እንዲመጡ የሚያበረታታ "ቀለብ ከተማሪ" የተሰኘ ዘመቻ ተጀምሯል።

ለተጨማሪ መረጃ በ +251914768256 እና +251914857638 ላይ ይደዉሉ ወይም በቴሌግራም @Aa_tre ላይ ያናግሩ!

ወደ ዩኒቨርስቲው ከነገ ጀምሮ የምትገቡ ተማሪዎች የምትችሉትን አድርጉ!

* ይህ ስራ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ በኩልም እውቅና አለው ተብሏል።

t.me/geradomedia
5.3K viewsGashu, edited  07:37
Open / Comment