Get Mystery Box with random crypto!

ገራዶ ሚዲያ

Logo of telegram channel geradomedia — ገራዶ ሚዲያ
Logo of telegram channel geradomedia — ገራዶ ሚዲያ
Channel address: @geradomedia
Categories: News
Language: English
Subscribers: 679
Description from channel

🔸ሁሉን አቀፍ የመረጃ ምንጭ!🔸
✍ ፃፉልን @geradomediabot
fb.com/geradomedia
twitter.com/geradomedia

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages 58

2021-02-03 21:57:10
#ምርጫቦርድ

ጥር 25 ቀን 2013 ዓ.ም በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ለብልጽግና ፓርቲ የተደረጉ የድጋፍ ሰልፎች ላይ የተነሱ ጉዳዮችን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ መግለጫ ሰጥቷል። ቦርዱ በመግለጫው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ያቀረበውን ቅሬታ እንዲሁም በሚዲያ ክትትል ክፍሉ አማካኝነት ክትትል በማድረግ በአሜሪካ ድምጽ፣ በዋልታ፣ በፋና፣ በኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ እንዲሁም በነዚሁ ሚዲያዎች የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በቀጥታ የተላለፉ መልእክቶችን መመልከቱን ገልጿል።

ሙሉ መግለጫው telegra.ph/NEBE-02-03

t.me/geradomedia
6.1K viewsGashu, edited  18:57
Open / Comment
2021-02-03 21:55:08 ምን ይፈልጋሉ? ምርጧን ቻናል ተቀላቀሏት!

ለመቀላቀል ከስር ይጫኑ

https://t.me/joinchat/RAn9b5UCOVFhyJKe
2.3K viewsGashu, 18:55
Open / Comment
2021-02-03 20:21:47 #የዩኤኢ_ኤምባሲ_ላይ_ጥቃት.......

ከውጭ የሽብር ቡድን አባላት ተልእኮ በመቀበል አዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ (ዩኤኢ) ኤምባሲ ላይ የሽብር ጥቃት በመፈጸም በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ እንዲሁም የአፍሪካና የዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ተቋማት መቀመጫ የሆነችውን የአዲስ አበባን በጎ ገጽታ ለማበላሸት በዝግጅት ላይ የነበሩት ቡድኖችን የብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት 15 የሽብር ቡድኑ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጓል።

አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ለመገናኛ ብዙኀን በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፣አሸባሪዎች ለጥቃት ሊጠቀሙባቸው ያዘጋጇቸው ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎች እና ለፍንዳታ ሥራ የሚውሉ ተቀጣጣይ ቁሳቁሶች እና የተለያዩ ሰነዶች ተገኝተዋል።

የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ከኅዳር 2013 ዓ.ም ጀምሮ ከሌሎች የሀገር ውስጥ እና የውጭ መረጃ ተቋማት ጋር በመሆን ጥብቅ ክትትል እና የመረጃ ልውውጥ በማድረግ የታቀደውን የሽብር ጥቃት ማክሸፍ ችሏል።

የሽብር ጥቃቱን ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ ከነበሩት መካከል የቡድኑን አባላት ሲመራ የነበረው የ35 ዓመቱ ዓሊ አህመድ አርዳይቶ ከፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመር ቢሮ ጋር በመቀናጀት በቁጥጥር ሥር እንዲውል መደረጉን መግለጫው አመልክቷል።

ለዓሊ አህመድ አርዳይቶ ለሽብር ጥቃቱ ማቀነባበሪያነት እንዲውል በዐሥር ሺዎች የሚቆጠር የአሜሪካ ዶላር እንደተላከለት ከተሰበሰቡ መረጃዎች ማረጋገጥ እንደተቻለ ተጠቁሟል።

ከዚህ ግለሰብ ጋር ግንኙነት የነበረው እና የሽብር ጥቃት ለመፈጸም በህቡዕ ሲያሴር የቆየው መሐሙድ አብዱልቃኒ የተባለ ሌላ ተጠርጣሪም ከቀናት በኋላ በቁጥጥር ሥር በዋለበት ወቅት በመኖሪያ ቤቱ የጦር መሣሪያዎች፣ ለፍንዳት ስራ የሚውሉ ተቀጣጣይ ቄሳቀሶች እና ሰነዶች መያዛቸውን አስታውቋል።

ሌላ ተመሳሳይ ተልእኮ የተሰጠው ቡድን በሱዳን ካርቱም በሚገኘው የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ ላይ ተመሳሳይ የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን ተጠቅሷል።

የሽብር ቡድኑ መሪ ከውጭ አመራር የሚሰጠው ኑሮውን በስዊዲን ያደረገው አህመድ እስማኤል የተባለ ግለሰብ ነው።

የሽብር ጥቃት ዕቅድ በማውጣት እና ከሽብር ቡድኑ አባላት ጋር ግንኙነት በመፍጠር በአዲስ አበባ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ኤምባሲ የደህንነት መረጃዎች እንዲሰበሰቡ አቅጣጫ ሲሰጥ ቆይቷል።

ከአውሮፓ፣ አፍሪካ እና እስያ የመረጃና ደህንነት ተቋማት ጋር የተቀናጀ የመረጃ ልውውጥ እና ብርቱ ክትትል በማድረግ አህመድ እስማኤል በስዊዲን ሀገር በቁጥጥር ሥር እንዲውል መደረጉን መግለጫው አመልክቷል።

t.me/geradomedia
6.0K viewsGashu, edited  17:21
Open / Comment
2021-02-03 17:31:07
“በትግራይ ያለው ሁኔታ በጽኑ ያሳስበኛል” - አንቶኒዮ ጉቴሬዝ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በትግራይ ያለው ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው ገለጹ፡፡ ጉቴሬዝ በቃል አቀባይ ጽህፈት ቤታቸው በኩል ባወጡት መግለጫ ድርጅታቸው አስቸኳይ ሰብዓዊ ፍላጎቶችን ለማሟላት በኢትዮጵያ ጽህፈት ቤቱ በኩል ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያለውን ጥብቅ ትስስር ጠቃሚነት አንስተዋል፡፡

አሁንም ለችግር የተጋለጡትን ለመጠበቅ እና ሰብዓዊ ሁኔታዎችን ለማቅለል ቀጣይነት ያላቸው አስቸኳይ እርምጃዎች እንደሚያስፈልጉ ነው ዋና ጸሃፊው አስምረው የተናገሩት፡፡

ጉቴሬዝ በዚህ ሁኔታ የኢትዮጵያ መንግስት ከሰሞኑ ጉብኝት ያደረጉትን የድርጅቱን ከፍተኛ አመራሮች ተቀብሎ ያስተናገደበትን አዎንታዊ ሁኔታ አድንቀዋል፡፡

አመራሮቹ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ስለ ሁኔታው የጎበኙት ዋና ጸሃፊው በተጎዱ የክልሉ አካባቢዎች፣ ለሃገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና ለመጠለያ ጣቢያዎች ያልተቆራረጠ እና ዘላቂ ሰብዓዊ አቅርቦት እንዲኖር ለመንግስት ባቀረቡት ጥሪ መሰረት ነው፡፡

ከሰሞኑ የድርጅቱ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ እና የደህንነት ዋና ጸሀፊ ጊልስ ሚካድ ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል፡፡

በተለይ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነሩ ከሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታው አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጋር በመሆን ትግራይ ክልል የሚገኘውን የማይ ዐይኒ የኤርትራውያን ስደተኞች መጠለያ ጣቢያን መጎብኘታቸው ይታወሳል፡፡ የዓለም ምግብ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቢዝሌይ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እንደነበርም አይዘነጋም፡፡ #AlAin

t.me/geradomedia
5.8K viewsGashu, edited  14:31
Open / Comment
2021-02-03 17:30:59 ምን ይፈልጋሉ? ምርጧን ቻናል ተቀላቀሏት!

ለመቀላቀል ከስር ይጫኑ

https://t.me/joinchat/RAn9b5UCOVFhyJKe
808 viewsGashu, 14:30
Open / Comment
2021-02-03 12:59:58
የማይካድራው ጭፍጨፋ ዓለም አቀፍ የሽብር ወንጀል ሆኖ ተመዘገበ!

ህወሓት አደራጅቶታል በተባለው እና “ሳምሪ” በተሰኘው ኢ-መደበኛ የወጣቶች ቡድን በማይካድራ የተፈጸመው ጭፍጨፋ በርካታ ንፁሃን የተገደሉበት ዓለም አቀፍ የሽብር ወንጀል ሆኖ ተመዘገበ፡፡ ወንጀሉ የተመዘገበው በዓለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም ኢንተርፖል ነው፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ባሳለፍነው ህዳር ወር የተፈጸሙ የሽብር ወንጀሎችን ዝርዝር ያወጣው ተቋሙ የማይካድራው ጭፍጨፋ በርካታ ንፁሃን ዜጎች ህይወታቸውን ያጡበት ኢሰብዓዊ ድርጊት ነው ሲል አስቀምጧል፡፡ ጭፍጨፋው በመላው ዓለም ከተፈጸሙ 10 ተመሳሳይ የሽብር ወንጀሎች ቀዳሚው ነው ያለም ሲሆን ቦኮሀራም በተጠቀሰው ወር በናይጄሪያ ከፈፀመው የሽብር ወንጀል እንደሚበልጥ ነው የገለጸው፡፡

የተቋሙ የሽብር ወንጀል መከላከል ዳይሬክቶሬት ጭፍጨፋው ማንነትን መሰረት አድርጎ የተፈጸመ ነው ማለቱንም ነው ከፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ የሚያመለክተው፡፡ ዳይሬክቶሬቱ 600 ንጹሃን መጨፍጨፋቸውንም ይፋ አድርጓል፡፡

ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም በማይካድራ እና በአካባቢው የተፈጸመው ጭፍጨፋ በወቅቱ በስልጣን ላይ በነበረው የአካባቢው መስተዳድር የጸጥታ መዋቅር አስተባባሪነት መፈጸሙን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ኅዳር 15 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጣው የመጀመሪያ ደረጃ ቀዳሚ ሪፖርት ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡

ኮሚሽኑ በሪፖርቱ ጭፍጨፋው በጦር ወንጀለኝነት ጭምር ሊያስጠይቅ የሚችል “የግፍና ጭካኔ ወንጀል” ነው ያለ ሲሆን ከ600 የሚልቁ ንጹሃን መገደላቸውን ማስታወቁም አይዘነጋም፡፡ #AlAin

t.me/geradomedia
5.8K viewsGashu, 09:59
Open / Comment
2021-02-03 12:00:02
በመቐለ ከተማ ትምህርት የካቲት 1 ይጀመራል ተባለ!

የመቐለ ከተማ ሰለምና ጸጥታ የተረጋጋ በመሆኑና የኮሮና መከላከያ ጥንቃቄን ተግባራዊ በማድረግ በሁሉም ደረጃ ባሉ የትምህርት ክፍሎች ከየካቲት 1 ቀን 2013 አንስቶ ትምህርት መስጠት እንደሚጀመር የከተማዋ ጊዜያዊ ከንቲባ ኣቶ አታኽልቲ ኃለስላሴ አስታውቀዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ከተጠቀሰው እለት ጀምሮ ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ አቶ አታኽልቲ ጥሪ አቅርበዋል።

በአሁኑ ወቅት በመቐለ ከተማ የሚገኙ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መደባኛ ስራቸውን እያከናወኑ መሆኑንም ከንቲባው ማስታወቃቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል።

በመላው ትግራይ ክልልም የቅድመ መደበኛ እና መደበኛ ትምህርት ቤቶች በየደረጃው ሊከፈቱ መሆኑን እና ሁሉም የትምህርት ማህበረሰብ አባላት ዝግጅት እንዲያደርጉ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

t.me/geradomedia
5.4K viewsGashu, 09:00
Open / Comment
2021-02-03 11:59:53 ምን ይፈልጋሉ? ምርጧን ቻናል ተቀላቀሏት!

ለመቀላቀል ከስር ይጫኑ

https://t.me/joinchat/RAn9b5UCOVFhyJKe
1.8K viewsGashu, 08:59
Open / Comment
2021-02-03 10:00:44
#የአብን_ክስ

በትላንትናው እለት በኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ለመደገፍ በተካሄዱ ሰልፎች ላይ አማራ ብሔራዊ ንቅናቄን (አብን) የሚያወግዙ መፈክሮች መስተጋባታቸውን ተከትሎ ፓርቲው ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በፃፈው ደብዳቤ ከሷል። ደብዳቤው ምርጫ ቦርድ በአመራሮቹ ላይ እርምጃ እንዲወስድ እንዲሁም “ለፈጸሙት አስነዋሪ ፍረጃ” ይቅርታ እንዲጠይቁ እንዲያደርግ ጠይቋል፡፡

* ሙሉው የደብዳቤው መልዕክት ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

t.me/ggeradomedia
5.1K viewsGashu, edited  07:00
Open / Comment
2021-02-03 09:48:47 ምን ይፈልጋሉ? ምርጧን ቻናል ተቀላቀሏት!

ለመቀላቀል ከስር ይጫኑ

https://t.me/joinchat/RAn9b5UCOVFhyJKe
712 viewsGashu, 06:48
Open / Comment