🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ገራዶ ሚዲያ

Logo of telegram channel geradomedia — ገራዶ ሚዲያ
Logo of telegram channel geradomedia — ገራዶ ሚዲያ
Channel address: @geradomedia
Categories: News
Language: English
Subscribers: 679
Description from channel

🔸ሁሉን አቀፍ የመረጃ ምንጭ!🔸
✍ ፃፉልን @geradomediabot
fb.com/geradomedia
twitter.com/geradomedia

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages 57

2021-02-05 09:21:13 በአጭር ጊዜ ውስጥ የሴት ጓደኛ እንድትኖርክ ትፈልጋለህ

በአጭር ጊዜ ውስጥ የወንድ ጓደኛ እንዲኖርሽ ትፈልጊያለሽ

ስለፍቅር ጥልቅ እውቀት እንዲኖራችሁ
OPEN የሚለውን ብቻ ይጫኑ!

OPEN
1.2K viewsGashu, 06:21
Open / Comment
2021-02-04 22:23:14
"ሰልፎቹን አስመልክቶ ከአንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች የቀረበውን ቅሬታ ቦርዱ በሚዛኑ ማየት አለበት" - አቶ ፍቃዱ ተሰማ

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ባሉ ከተሞች በተካሄዱ የድጋፍ ሰልፎች "በህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ ተመዝግበን እያለን ስማችን ጠፍቷል" በሚል አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያቀረቡትን ቅሬታ ተመስርቶ ያስተላለፈው ውሳኔ በሚዛናዊነት መታየት አለበት የሚል አቋም እንዳላቸው የኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ገለጹ፡፡

ሃላፊው ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ የክልሉ ህዝብ በራሱ ተነሳሽነት ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ለብልጽግና ፖርቲ ያለውን ድጋፍና ክብር አሳይቷል ብለዋል፡፡ ህዝብ የተሰማውን ለምን በእዚህ ደረጃ ተነሳስቶና ፈንቅሎ ወጣ? የሚለው መታየት አለበት፣ ትችቱን ያነሱ ወንድሞቻችንም በእኛ በኩል ምን ጉድለት አለ? ብለው ራሳቸውን ማየት ያስፈልጋቸዋል ብለዋል፡፡

ህዝቡ በራሱ የቀሰቀሰውና የጣው ሰልፍ እንደመሆኑ መወቀስ ያለበት ያስተላለፈው መልእክት ብቻ ሳይሆን እነዚህ አካላትስ በተለያየ ጊዜ ምን ሲያደርጉ እንደነበር ብሎ ቦርዱ መጠየቅ ነበረበት ብለዋል አቶ ፈቃዱ፡፡

ህዝብን እንደህዝብ የሚያንኳስሱ፣ የሚያጋጩ፣ ኢትዮጵያን የሚያፈርሱ፣ የጁንታው ተላላኪ በመሆን የሚሰሩ አካላት ህዝቡም ያውቃል እነርሱም ያውቃሉ ብለን እንገምታለን ተጨባጭ ማሳያዎችም አሉ ብለዋል፡፡

ምርጫ ቦርድን እናከብራለን፣ ህጉንም ከማንም በላይ እናከብራለን ኢትዮጵያ ጠንካራ ገለልተኛ ተቋም እንዲኖራት ከማንም በላይ እንፈልጋለን ብለዋል፡፡ ለእዚህም እንሰራለን፣ እንታገላለን፣ እንረባረባለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡ (ኢ ፕ ድ)

t.me/geradomedia
5.5K viewsGashu, 19:23
Open / Comment
2021-02-04 22:22:51 በአጭር ጊዜ ውስጥ የሴት ጓደኛ እንድትኖርክ ትፈልጋለህ

በአጭር ጊዜ ውስጥ የወንድ ጓደኛ እንዲኖርሽ ትፈልጊያለሽ

ስለፍቅር ጥልቅ እውቀት እንዲኖራችሁ
OPEN የሚለውን ብቻ ይጫኑ!

OPEN
2.1K viewsGashu, 19:22
Open / Comment
2021-02-04 22:05:46
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ140 ሺህ በለጠ!

- በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 6 ሺህ 2 የላቦራቶሪ ምርመራ 749 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 140 ሺህ 157 ደርሷል።

- በሌላ በኩል የዛሬውን 254 ጨምሮ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 124 ሺህ 242 ሆኗል።

- አሁን ላይ ቫይረሱ ካለባቸው 13 ሺህ 787 ሰዎች መካከል 209 ሰዎች በጽኑ ሕሙማን መከታተያ ክፍል ውስጥ ይገኛሉ። በተጨማሪም የ4 ሰዎች ሕይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 126 ደርሷል።

t.me/geradomedia
4.9K viewsGashu, 19:05
Open / Comment
2021-02-04 20:56:20
#የበጎ_ሰው_ሽልማት

ለሀገርና ለህዝብ አርአያነት ያለው ታላቅ ተግባር ያከናወኑ ኢትዮጵያውያንን በየአመቱ ዕውቅና የሚሰጠው የበጎ ሰው ሽልማት፤ የዘንድሮ የእጩዎች ጥቆማ የካቲት አንድ 2013 እንደሚጀምር አዘጋጆቹ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት መግለጫ አሰታውቀዋል።

ለዘንድሮው ሽልማት አስር ዘርፎች የተመረጡ ሲሆን እነሱም፦ መምህረነት፣ ሳይንስ (ህክምና፣ ቴክኖሎጂ፣ ምሕንድስና፣ ኬሚስትሪ፣ አርክቴክቸር....)፣ ኪነ ጥበብ፣ በጎ አድራጎት፣ ቢዝነስና ፈጠራ፣ መንግስታዊ ተቋማት ሀላፊነት፣ ቅርስና ባህል፣ ማህበራዊ ጥናት፣ ሚዲያና ጋዜጠኝነትና ለሀገሪቱ እድገት በጎ ስራ ያከናወኑ ዲያስፖራዎች ናቸው።

ለአንድ ወር በሚቆየው የእጩዎች ጥቆማ ለመስጠት በቫይበር፣ ቴሌግራም፣ ኋትስአፕ እንድሁም በስልክ ቁጥር 0977 23 23 23 መጠቀም የሚቻል ሲሆን በተጨማሪም በኢሚይል አድራሻ begosewprize@gmail.com ወይንም በፖስታ ሳጥን ቁጥር 150035 ጥቆማ መስጠት አንደሚቻል አዘጋጆቹ ገልፀዋል።

በጎ ሰው ሽልማት ድርጅት እስከአሁን ከ160 ሰዎችን የሸለመ ሲሆን ሽልማቱ ካባ በመሰልበስ የምስጋና ሰርተክፌት የሚሰጥበት አመታዊ ፕሮግራም ነው። #FBC

t.me/geradomedia
5.3K viewsGashu, 17:56
Open / Comment
2021-02-04 13:42:24
"የተፈናቀሉ ዜጎች ምርጫ ይመርጣሉ" - ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ

የተፈናቀሉ ዜጎች ባሉበት ማዕከል ሆነው በዘንድሮው ምርጫ እንደሚሳተፉና ምርጫ እንደሚመርጡ ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ተናገሩ። ከአካባቢያቸው በችግር ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች መብታቸውን በፍፁም አያጡም ያሉት ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ተፈናቃዮቹ በያሉበት ማዕከል ሆነው የሚመርጡት የምርጫ ውጤትም ቀድሞ ከመጡበት አካባቢ የምርጫ ውጤት ላይ የሚደመር መሆኑን ገልፀዋል። #Tikvah

t.me/geradomedia
5.6K viewsGashu, edited  10:42
Open / Comment
2021-02-04 13:20:44
በትግራይ ክልል ምርጫ የሚከናወንበት ሁኔታ......

በትግራይ ክልል አሁን ባለው ሁኔታ ከሌሎች ክልሎች እኩል ምርጫ ሊደረግ እንደማይችል የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ዛሬ በማህበራዊ ሚዲያ ከህዝብ ለተሰበሰቡ ጥያቄዎች በቦርዱ የፌስቡክ ገፅ ላይ በቀጥታ ምላሽ በሰጡበት ወቅት አረጋግጠዋል።

ወ/ሪት ብርቱካን በምላሻቸው፥ "... በክልሉ ያለው ሁኔታ ሲሻሻል በጥቂት የቀናት ልዩነት ከሌሎቹ ክልሎች ከሚደረገው ምርጫ ጋር አንድ ላይ ውጤቱ Merge የሚያደርግበትን ሁኔታና ፓርላማ በሚከፈትበት ጊዜ የሁሉም ውጤት አብሮ የሚቀርብበት ሁኔታን ለማየት ተስፋ እናደርጋለን" ብለዋል።

ከትግራይ ክልል ጋር በተያያዘ አስፈላጊው ቁሳቁስ መሟላቱን እና ዝግጅት መጠናቀቁን፤ ምርጫው ዘግይቶም ቢካሄድ ከሌሎች ክልሎች ጋር ውጤቱ የሚገለፅበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የተለያዩ አሰራሮች እንደሚኖሩም ወ/ሪት ብርቱካን ተናግረዋል። #Tikvah

t.me/geradomedia
5.5K viewsGashu, 10:20
Open / Comment
2021-02-04 13:20:31 በአጭር ጊዜ ውስጥ የሴት ጓደኛ እንድትኖርክ ትፈልጋለህ

በአጭር ጊዜ ውስጥ የወንድ ጓደኛ እንዲኖርሽ ትፈልጊያለሽ

ስለፍቅር ጥልቅ እውቀት እንዲኖራችሁ
OPEN የሚለውን ብቻ ይጫኑ!

OPEN
1.9K viewsGashu, 10:20
Open / Comment
2021-02-04 10:44:08
ወደ መቐለ ተልኮ መደረሻው ሳይታወቅ የቆየው 1.3 ቢሊየን አዲሱ ብር ተገኘ!

በምርጫ ቦርድ ተዘርዞ ህልውናው እንዲከስም የተደረገው ቀድሞ የትግራይ ክልልን ሲያስተዳድር የነበረው ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሃት) እና በማዕከላዊው መንግስት መካከል ጦርነት የተቀሰቀሰ ዕለት ጥቅምት 24 ቀን 2013 አ.ም ምሽት ወደ ትግራይ መቐለ በአሮጌው ብር እንዲቀየር በብሄራዊ ባንክ በአውሮፕላን የተላከው አዲሱ 1.3 ቢሊየን ብር መዳረሻው መታወቁን ዋዜማ ራዲዮ ሰምቻለሁ ብላለች።

በአሮጌው ብር እንዲቀየር የተላከው 1.3 ቢሊየን ብር መቐለ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ አንድ ክፍል ውስጥ ነው ታሽጎ የተገኘው።

ህወሃት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ፈፅሟል በተባለበትና ግጭቱ ወደለየለት ጦርነት በተሸጋገረበት በዚያ ዕለት አሮጌውን የብር ኖት እንዲተካ የተላከው ብር መዳረሻ አልታወቀም ነበር።

በወቅቱም መንግስት ገንዘቡን በትግራይ ክልል ላሉ የተለያዩ ባንኮች አከፋፍያለሁ ብሎ በብሄራዊው የቴሌቭዥን ጣብያ ማስነገሩ ይታወሳል። ማይጨው፣ አደዋ፣ ሽሬ እንዳስላሴ እና አዲግራት ላሉ የተለያዩ ንግድ ባንኮች ብሩ ተከፋፍሏል ተብሎም ነበር። ሆኖም በወቅቱ በክልሉ ከነበረው ሁኔታ አንጻርና እንደተባለውም ብሩ በክልሉ ላሉ የባንክ ቅርንጫፎች እንዳልተከፋፈለ ዋዜማ ራዲዮ ዘግባ ነበር።

የ1.3 ቢሊየን አዲሱን ብር እጣ ፈንታም የፌዴራል መንግስት የመቐለ ከተማን ከተቆጣጠረም በኋላ በመቐለ ያለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደ አዲስ ስራ እንኪጀምር እንዳላወቀ ተሰምቷል። ሰሞኑን በመቐለ ያለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ እንደገና ስራ ሲጀምር ግን የቅርንጫፉ ሰራተኞች ብሩን በአንድ ክፍል ታሽጎ ማግኘታቸውን ዋዜማ ራዲዮ ከምንጮቼ መረጃ አግኝቻለሁ ብላ ዘግባለች።

t.me/geradomedia
5.4K viewsGashu, 07:44
Open / Comment
2021-02-04 10:43:52 ምን ይፈልጋሉ? ምርጧን ቻናል ተቀላቀሏት!

ለመቀላቀል ከስር ይጫኑ

https://t.me/joinchat/RAn9b5UCOVFhyJKe
378 viewsGashu, 07:43
Open / Comment