🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ገራዶ ሚዲያ

Logo of telegram channel geradomedia — ገራዶ ሚዲያ
Logo of telegram channel geradomedia — ገራዶ ሚዲያ
Channel address: @geradomedia
Categories: News
Language: English
Subscribers: 679
Description from channel

🔸ሁሉን አቀፍ የመረጃ ምንጭ!🔸
✍ ፃፉልን @geradomediabot
fb.com/geradomedia
twitter.com/geradomedia

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages 53

2021-02-10 19:57:45 ምርጫ ቦርድ የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ የዕጩዎች ምዝገባ ቀንን ይፋ አደረገ!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ መስተዳድሮች የዕጩዎች ምዝገባ ቀንን ይፋ አደረገ፡፡ ቦርዱ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ፣ በኦሮሚያ እና በሃረሪ ክልላዊ መንግስታት የሚወዳደሩ እጩዎች የሚመዘገቡበትን ቀንም ይፋ አድርጓል፡፡

በመሆኑም በሁለቱ ከተማ መስተዳድሮች እና ቀደም ሲል በተጠቀሱት ክልሎች የሚገኙ እጩዎች ምዝገባ ከየካቲት 8 እስከ የካቲት 21 ቀን 2013 ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 እንደሚከናወን ቦርዱ አስታውቋል፡፡

በእጩነት የሚመዘገቡት በቀጣዩ ሃገራዊ ምርጫ በግል ወይም በፖለቲካ ድርጅት አባልነት ለመወዳደር የሚፈልጉ ናቸው፡፡ በአካል ቀርቦ መመዝገብም ይጠበቅባቸዋል፡፡

በፖለቲካ ድርጅት ተወክለው የሚቀርቡ እጩዎች በፓርቲው መወከላቸውን እና በእጩነት ለመቅረብ መስማማታቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ከእጩነት ማመልከቻ ቅጽ እና ከሌሎች አስፈላጊ ሰነዶች ጋር አያይዘው በሚወዳደሩበት የምርጫ ክልል መመዝገብ እንደሚችሉ ነው ቦርዱ ያስታወቀው።

አንድ እጩ በአንድ ጊዜ መወዳደር የሚችለው/የምትችለው በአንድ የምርጫ ክልል እና ለአንድ ምርጫ አይነት ብቻ ነውም ብሏል ቦርዱ።

በእጩነት ለመመዝገብ የሚያስፈልጉ መስፈርቶችን ያስቀመጠው ቦርዱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለክልል ምክር ቤት የሚወዳደሩ ዕጩዎች ምዝገባ የሚከናወነው በየምርጫ ክልሎቹ እንደሆነም ይፋ አድርጓል፡፡

ዕጩ ሆኖ ለመመዝገብ ለፌዴራል እና ለክልል ምክር ቤቶች በግል የሚወዳደሩ ዕጩዎች 2 ሺ 500፤ አካል ጉዳተኛ ዕጩዎች ደግሞ 1 ሺ 500 የድጋፍ ፊርማ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

በፖለቲካ ፓርቲ አባልነት እጩ ሆነው መቅረብ የሚፈልጉ ደግሞ ለዚህኛው ጠቅላላ ምርጫ ብቻ በሚል በተወካዮች ምክር ቤት በተወሰነው መሰረት የድጋፍ ፊርማ ማቅረብ አይጠበቅባቸውም።

ቦርዱ የተቀሩትን ክልሎች የእጩዎች ምዝገባ ሰሌዳ በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

6ኛው ሃገር አቀፍ ምርጫ እና የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ውሳኔ ተዳብለው ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ/ም ይካሄዳሉ መባሉ የሚታወስ ነው፡፡

Via AlAin

t.me/geradomedia
5.1K viewsGashu, 16:57
Open / Comment
2021-02-10 19:56:52
4.7K viewsGashu, 16:56
Open / Comment
2021-02-10 17:59:43
የኮሮና ቫይረስ ክትባት ሀገር ውስጥ ሲገባ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዜጎች.....

"....የጤና ባለሞያዎችና ሰራተኞች እንዲሁም በተመሳሳይ ስራ መስክ ውስጥ ያሉ፣ የህዝብ ትራንስፖርት ላይ አገልግሎት የሚሰጡ፣ እድሜያቸው የገፋ፣ ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸው፣ በስራቸው ምክንያት ተጋላጭ የሚሆኑ እንደ አስተማሪዎች፣ የፀጥታ አካላት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

እንደ ሀገር ክትባቱን ለማምጣት እና ተደራሽ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን በምን ያህል ፍጥነት ክትባቱ ይዳረሳል የሚለው እየተሰራ ያለው እቅድ እንዳለ ሆኖ በዓለም አቀፍ የክትባት አምራቾች አቅርቦት መጠን የሚወሰን ሲሆን ክትባቱ ቢመጣም በሚቀጥለው 1 ዓመት ውስጥ ሁሉንም ማህበረሰብ ማዳረስ ስለማይቻል አሁንም ዋናው ትኩረታችን የመከላከል ስራዎችን አጠንክረን መቀጠል ነው መሆን ያለበት።" - ዶ/ር ሊያ ታደሰ (የጤና ሚኒስቴር)

t.me/geradomedia
5.2K viewsGashu, 14:59
Open / Comment
2021-02-10 11:24:06
የመምህራን 9 ወር የተጠራቀመ የደሞዝ ጭማሪ (JEG) ቅሬታ አስነሳ!

በአገራችን የተለያዩ ክልሎች የሚገኙ መምህራን የዘጠኝ ወር የተጠራቀመ የደሞዝ ጭማሪ (JEG) መንግስት ቃል በገባልን መሰረት አልተከፈለንም ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ከሀምሌ 2011 ዓ/ም ጀምሮ እስከ መጋቢት 2012 አመት ያለው የዘጠኝ ወር ክፍያ እንዳልተከፈላቸውና የዘጠኝ ወሩን ውዝፍ (JEG) በ2013 በጀት አመት ተካቶ ይከፈላችኋል ተብሎ ቃል ቢገባላቸውም እስካሁን ምንም ክፍያ ሳይፈጸም የበጀት አመቱ አጋማሽ ላይ መደረሱን ነው የተናገሩት።

በአዲስ አበባ ለሚገኙ መምህራን ሙሉ በሙሉ (JEG) ሲከፈል የሌሎች ክልሎች ግን እስከ አሁን አለመከፈሉን ቅሬታቸውን ያቀረቡ መምህራን አክለው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ም/ ፕሬዚዳንት ሽመልስ አበበ በበኩላቸው በክልል መምህራን በኩል የሚቀርቡት ጥያቄዎች አግባብነት ያላቸው እንደሆኑ ማህበሩ ያውቃል ሲሉ ገልጸዋል።

በአንድ ዘርፍ ላይ ያሉ ሰዎች ለአንዱ ተከፍሎ ለአንዱ የሚቀርበት አግባብ እንደሌለ ያስረዱት ፕሬዝዳንቱ መቼ እንደሚከፈል ነው እንጂ ያልታወቀው ክፍያው መፈፀሙ እንደማይቀር ጠቁመዋል።

በጉዳዩን በተመለከተ በአዲስ ማለዳ ጋዜጣ የተጠየቁት የገንዘብ ሚኒስቴር ህዝብ ግንኙነት ሰመሪታ እንደተናገሩት ጉዳዩ በበላይ አካላት እየታየ እንደሆነ ተናግረዋል።

By: Addis Maleda Newspaper

t.me/geradomedia
5.7K viewsGashu, edited  08:24
Open / Comment
2021-02-10 07:20:21
5.6K viewsGashu, 04:20
Open / Comment
2021-02-09 21:48:06
የኮሮና ቫይረስ መነሻ.......

የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮና ቫይረስ መነሻ ከውሃን ቤተ ሙከራ ሳይሆን ከእንስሳት መሆኑን በጥናቱ አረጋገጠ፡፡ የድርጅቱ ልዑክ ቻይና በመገኘት የኮሮና ቫይረስን መነሻ ሲያጠና ቆይቷል፡፡ የልዑክ ቡድኑ መሪ ፒተር ቤን ኢምባረክ መነሻውን ለማወቅ ተጨማሪ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸውም ገልጸዋል፡፡ ጥናቱን የድርጅቱ ልዑክ እና ቻይና የጤና ኮሚሽን በጋራ ማጥናታቸው ነው የተነገረው፡፡ውሃን በቻይና ምዕራባዊ ሁቤ አውራጃ የምትገኘ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ኮሮና ቫይረስ የተገኘባት ከተማ መሆኗ ይታወሳል፡፡ ባለሙያዎች ወረርሽኙ ወደ ሰዎች ከመሰራጨቱ በፊት ከእንስሳ እንደመጣ ቢያምኑም እንዴት ሊከሰት እንደቻለ እርግጠኞች አይደሉም ተብሏል፡፡

(Via BBC)

t.me/geradomedia
5.8K viewsGashu, edited  18:48
Open / Comment
2021-02-09 21:44:41 በአጭር ጊዜ ውስጥ የሴት ጓደኛ እንድትኖርክ ትፈልጋለህ

በአጭር ጊዜ ውስጥ የወንድ ጓደኛ እንዲኖርሽ ትፈልጊያለሽ

ስለፍቅር ጥልቅ እውቀት እንዲኖራችሁ
OPEN የሚለውን ብቻ ይጫኑ!

OPEN
1.6K viewsGashu, 18:44
Open / Comment
2021-02-09 19:45:33
“ሰብአዊነትና ፍቅር፤ ለትግራይና መተከል” በሚል መሪ ሃሳብ ድጋፍ ማሰባሰብ ተጀመረ!

“ሰብአዊነትና ፍቅር፤ ለትግራይና መተከል” በሚል መሪ ሃሳብ የድጋፍ ማሰባሰብ መርሃ ግብር ተጀመረ። የድጋፍ ማሰባሰብ መርሃ ግብሩ መጀመርን አስመልክቶ አስተባባሪ ኮሚቴው ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።

በዚህም ከዚህ ቀደም በአገር ውስጥና በውጭ አገሮች በተናጠል ሆነው የሰብአዊ ድጋፍ ሲያሰባስቡ የነበሩ አካላትን ወደ አንድ ማዕከል በመምጣት “ሰብአዊነትና ፍቅር፤ ለትግራይና መተከል” በሚል መሪ ሃሳብ ከዛሬ ጀምሮ ድጋፍ ማሰባሰብ መጀመራቸው ተገልጿል።

የድጋፍ ማሰባሰብ ሥራው በኢትዮጵያ በጣይቱ ሆቴል፣ በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ዋና ጽህፈት ቤት እና በክልል የቀይ መስቀል ቅርንጫፎች ቁሳቁስ የማሰባሰብ ሥራ እንደሚሰራ ተጠቁሟል። በገንዘብ ድጋፍ የሚያደርጉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ስም በተከፈተ የሒሳብ ቁጥር “10003277016559” ድጋፍ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።

በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንም በግሎባል አሊያንስ በኩል በተከፈተ “በትግራይና መተከል ለተጎዱ ወገኖቻችን የበኩልዎን ይረዱ ዘንድ እናሳሰባለን” በሚል በተከፈተ "ጎ ፈንድ ሚ" አካውንት አማካኝነት ድጋፍ ማድረግ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

ኮሚቴው ኢትዮጵያዊነት ከቃል በላይ በተግባርና በአብሮነት የሚገለፅ በመሆኑ በአገር ውስጥም በውጭም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ከዛሬ የካቲት 2 ቀን 2013 ጀምሮ የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል። #ENA

t.me/geradomedia
5.2K viewsGashu, 16:45
Open / Comment
2021-02-09 17:52:05
"9 ሚሊየን የኮቪድ-19 ክትባት ወደ ሃገር ቤት ለማስገባት እየተሰራ ነው" - ዶክተር ሊያ ታደሰ

በመጋቢት ወር መጨረሻ አልያም ሚያዚያ ወር መጀመሪያ ላይ እስከ 9 ሚሊየን የኮቪድ19 ክትባት ወደ ሃገር ቤት እንዲገባ እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ፡፡

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በክትባቱ እና "እንድናገለግልዎ ማስክዎን ያድርጉ" በሚሉት ዘመቻዎች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

ለክትባቱ በዋናነት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዜጎችን የመለየት ስራ እየተሰራ ነውም ብለዋል።

በዚህም የጤና ባለሙያዎች፣ የማህበራዊ ጤና ሰራተኞች፣ የህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አካላት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል ማለታቸውን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘግቧል።

t.me/geradomedia
5.1K viewsGashu, 14:52
Open / Comment
2021-02-09 11:56:41
በረሃብ አድማ ላይ የሚገኙት ፖለቲከኞች....

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ከፍተኛ አመራር አቶ ደጀኔ ጣፋ በረሃብ አድማው ተዳክመው በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል መግባታቸውን ከ Oromo Prisoners Defense Team የተገኘው ሪፖርት ያሳያል።

ትላንትና ምሽት 3 ሰዓት ላይ አቶ ሸምሰዲን ጠሃ በአድማው በመዳከሙ ምክንያት ከምሽቱ ከቃሊቲ ማረሚያ ወደ ሆስፒታል በአንቡላንስ መወሰዱ ሪፖርት ተደርጎ ነበር። በአጠቃላይ አድማውን እያደረጉ ያሉት 20 ሲሆኑ ሌሎችም ያሉበት ሁኔታ እጅግ በጣም አሳሳቢ መሆኑ ተገልጿል። #tikvah

t.me/geradomedia
5.3K viewsGashu, edited  08:56
Open / Comment