Get Mystery Box with random crypto!

GOD'S GOSPEL

Logo of telegram channel godsgospel — GOD'S GOSPEL G
Logo of telegram channel godsgospel — GOD'S GOSPEL
Channel address: @godsgospel
Categories: Uncategorized
Language: English
Subscribers: 980
Description from channel

KNOWING God and making Him KNOWN!❤
እግዚአብሔርን ማወቅ እና ማሳወቅ!

for more information use
👉 @BiniGrham

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


The latest Messages 2

2022-04-15 11:55:38 Samuel Tesfamichael
New Album
260 viewsBini Grham, edited  08:55
Open / Comment
2022-02-17 09:21:42 Lust is pleasure for 5 mins and years of guilt.

ዝሙት ለ5 ደቂቃዎች ደስታ እና ለዓመታት ፀፀት ነው።

-Dr. Myles Munroe
66 viewsBini Grham, 06:21
Open / Comment
2022-02-14 17:50:02 #Valentine'sDay
ሁላችሁም ስለዚህ Valentine's ቀን የተወሰነ እውቀት እንዳላችሁ እርግጠኛ ነኝ። ነገር ግን ስንቶቻችሁ ይሄንን በዓል በተመለከተ ሙሉ እውቀት አላችሁ? ይሄንን ቀን እና በዓል በተመለከተ እጅግ በጣም ብዙ ክርስቲያኖችን ጨምሮ ትክክለኛው እውቀት ስለሌላቸው በጥቅሉ "የፍቅር ቀን" ወይም "የፍቅረኛሞች ቀን" ነው በማለት ነው የሚገልጹት። ቀኑ በዘመናዊው ዓለም ፍቅረኛሞች ስጦታ የሚለዋወጡበት ቀን እና የፍቅር ጊዜ አብረው የሚያሳልፉበት ቀን እንደሆነም ይነገራል። እኛ በኢየሱስ ክርስቶስ የምናምን ግን ነገሮችን ሁሉ በጥንቃቄ መመርመር እና ከስህተት እራሳችንን የመጠበቅ ሃላፊነት አለብን።

Valentine's day ስያሜውን ያገኘው Valentine ከተባለ የካቶሊክ ቤተ እምነት አባት ነው። ነገሩ እንደዚህ ነው ይህ Valentine የተባለ ሰው በዘመኑ የነበረው የመንግስት ስርዓት አንዳንድ ፖለቲካዊ ትርፎችን ለማግኘት ጋብቻን ይከለክላል፥ ይሁን እንጂ Valentine የተባለው ሰው የመንግስት አዋጅ ባለመቀበል በስውር ወንዶችንና ሴቶችን ያጋባ ነበር፥ በኋላም Valentine በዚህ ድርጊቱ ምክንያት በመንግሥት ተይዞ የመንግስትን ስርዓት ባለመታዘዝ ተፈርዶበት ተገደለ። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነበር ሰይጣንን እና ልጆች ይሄንን አጋጣሚ በመጠቀም ቀድሞ LUPERCALIA በመባል የሚታወቀውን የሮም በዓል በተንኮል ስሙን Valentine'sDay በሚል ቀይረው ያመጡት። ለምን በዓሉ Valentine'sDay ተባለ ለሚለው ጥያቄ የሚሰጠውም መልስ Valentine የተባለውን "ለፍቅር የሞተ" ሰው ለማሰብ ነው የሚል ነው። ይህም በዓሉን ክርስቲያናዊ በዓል ለማስመሰል ነው።
LUPERCALIA የ Valentine's በዓል አባት ነው ማለት ይቻላል። የLUPERCALIA በዓል LUPERCUS በመባል የሚታወቀውን የሮም ጣኦት ለማምለክ የሚከበር በዓል ነበር። በዚህ በዓል ላይ ከሚደረጉት ነገሮች አንዱ በእጣ ሴቶችን እና ወንዶችን ማገናኘት፥ ኢ-ሞራላዊ የሆኑና ከጋብቻ ውጭ የሆኑ ግብረስጋ ግንኙነቶችን መፈጸም ጨምሮ ውሾችን LUPERCUS ለተባለው ጣኦት መስዋዕት አድርጎ ማቅረብ ነበር።
Valentine'sDay ስሙን ለወጠ እንጂ የቀደመው የአባቱ የLUPERCALIA በዓል ባሕርያት የሚታዩበት ነው። ድንግል ሴቶች ባላቸው ላልሆነ ሰው ክብራቸውን በፈቃዳቸው የሚሰጡበት እና ለሰይጣን የሚሰውበት በዓል ነው።
ክርስትያን በፍቅር ግንኙነት ውስጥ ለአጋሩ ፍቅሩን የሚገልጥበት ጤነኛ የሆነ መንገድ አለ። ስጦታ መለዋወጥ አይደለም ችግሩ ከበስተጀርባው ያለው ስውር እጅ ነው። ክርስቲያን ፍቅረኛማቾች የፍቅር ግንኙነታችሁን ዛሬ ValentinesDay እያሉ ዓለማዊያን በሚያከብሩበት መንገድ የምታከብሩ ከሆን ዓለምን እየመሰላችሁ እንደሆነ እውቁ፥ ዓለምን እየወደዳችሁም ጭምር ነው። ሌላ ቀን ምረጡ ለፍቅር አጋራችሁ በራሳችሁ መንገድ ስጦታ ስጡ እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና ቅዱሳን ሁኑ።
ተጨማሪ እውቀት ለማግኘት የራሳችሁን ጥናት አድርጉ።

ይሄንን ከወቅን በኋላ በመንገዳቸው ብንሄድ የእግዚአብሔር ጠላቶች ሆነናል።“አመንዝሮች ሆይ፥ ዓለምን መውደድ ለእግዚአብሔር ጥል እንዲሆን አታውቁምን? እንግዲህ የዓለም ወዳጅ ሊሆን የሚፈቅድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል።”
— ያዕቆብ 4፥4

በመጨረሻም የምናደርገው እያንዳንዱን ነገር በእውቀት ይሁን፤ ፀጋ ይብዛላችሁ።
SHARE &JOIN
@TheDeepThingsOfGod
@TheDeepThingsOfGod
101 viewsBini Grham, 14:50
Open / Comment
2022-02-10 13:45:19 #ምልክቱ ላይ ሳይሆን #ምክንያቱ ላይ


በመንፈስ ቅዱስ #የመሞላት ዋና ዓላማ(ምክንያት) #ልሳን_መናገር ሳይሆን #የኢየሱስ_ምስክር መሆን ነው::
በልሳን መናገር የመሞላታችን #ምልክት ሲሆን የኢየሱስ ምስክር መሆን ግን የመሞላታችን #ምክንያት(ዓላማ) ነው::

#ምልክቱ ላይ ሳይሆን #ምክንያቱ ላይ እናተኩር::

የእግዚአብሔር ወንጌል #መስካሪ ካልሆንን #ችግር አለ:: ችግሩም #ዘወትር በመንፈስ #የአለመሞላት ችግር ነው::
መንፈስ ቅዱስን #መቀበል እና በመንፈስ ቅዱስ #መሞላት #የተለያዩ ነገሮች ናቸው: መቀበል #የአንድ_ጊዜ ተግባር ነው መሞላት ግን #የዘወትር_ተግባር ነው::

መስካሪነት #የመቀበል ሳይሆን #የመሞላት ውጤት ነው!!

Join
@Godsgospel
@Godsgospel
171 viewsBini Grham, 10:45
Open / Comment
2022-02-03 14:09:34 #Love_of_Money

ነገር ግን የዚህ ዓለም ገንዘብ ያለው፥ ወንድሙም የሚያስፈልገው ሲያጣ አይቶ #ያልራራለት ማንም ቢሆን፥ #የእግዚአብሔር_ፍቅር በእርሱ እንዴት ይኖራል? ..1ኛ ዮሐ3: 17

የዚህ ዓለም ገንዘብ በእጃችን እያለ #የሚያስፈልገውን_አጥቶ ለሚቸገረው ሰው #ልንተውለት #ልንሰጠው ካልቻልን የእግዚአብሔር #ፍቅር የለንም #ፍቅራችን_ለገንዘባችን ነው ማለት ነው::
ገንዘብን #አለመውደድ ወይም ገንዘብን #መተው ማለት #የሚያስፈልገውን_ላጣ ወገን መለገስ ማለት ነው::
ለአንድ ክርስቲያን ሰጪነት #የማይቀያየር_ህይወቱ ሊሆን ይገባል::

#Join
@GodsGospel
@GodsGospel
526 viewsBini Grham, 11:09
Open / Comment
2022-01-29 07:33:29 #Preaching_JESUS


መድረክ የያዛችሁ ወንድሞች #የለበሳችሁት_ልብስ የንግግር ችሎታችሁ የዞራችሁት #አህጉር ያጠለቃችሁት #ጫማ ያደረጋችሁት #ሰዓት አይነቱ እና ዋጋው ለእግዚአብሔር ህዝብ #ምንም_አያደርግለትም #አያንጸውም የማይጠገበውን የማይለወጠውን #ወንጌሉን_ስበኩት ቃሉን ስበኩት ከቃሉ ፈውስ አለና።
አማኝ የሚታነጸው #በእግዚአብሔር_ቃል_እውነት ነው። ወንጌል ይሰበክ ሰዎች አይሰበኩ #ቃሉ ይሰበክ #ቁስ_አይሰበክም ዘላለማችንን የቀየረው ቃሉ እንጂ ቁስ አይደለምና ወንጌሉን #ረብ_በሌለው ቁስ አትቀይሩት:: ኢየሱስን ትቶ #ምድራዊ_ቅራቅንቦን አግዝፎ መስበክ ነውር ነው። የእግዚአብሔርን ህዝብ #ኢየሱስን አሳዩት እራሳችሁን አታሳዩት።

የእግዚአብሔርን ቃል #ቀላቅለው_እንደሚሸቃቅጡት እንደ #ብዙዎቹ አይደለንምና፤
— 2ኛ ቆሮ 2፥17


Join @godsgospel
@godsgospel
396 viewsBini Grham, edited  04:33
Open / Comment
2022-01-26 22:37:57 ያላችሁ #ህብረት #መድረሻችሁን ይወስናል::
(Your association determines your destination).

ከጠቢባን ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል የሰነፎች ባልንጀራ ግን ክፉ መከራን ይቀበላል።ምሳሌ 13፥20

ያላችሁ ህብረት ወይ #ይሰራችኋል ወይ #ይሰብራችኋል። #ከጠቢባን ጋር ከተጓዛችሁ #ጠቢብ ትሆናላችሁ: #የሞኞች_ጓደኛ ከሆናችሁ ግን ራሳችሁን #ለጥፋት እያዘጋጃችሁ ነው። ምንም ያህል #የተቀባችሁ ብትሆኑም #ከተሳሳተ ሰው ጋር #ብትጓዙ ምንም አትጠራጠሩ #የተሳሳተ ሕይወት ይኖራችኋል።

አትሳቱ ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል። 1ኛ ቆሮ 15: 33


#Join
@GodsGospel
@GodsGospel
58 viewsBini Grham, 19:37
Open / Comment
2022-01-24 12:11:20
Anyone can believe when God is #already moving. But real faith is when you step out when it #seems that God is #not_moving.
- Reinhard Bonnke
34 viewsBini Grham, edited  09:11
Open / Comment
2022-01-23 07:53:29 Check out መልህቅ Podcast: https://t.me/melhikpodcast
75 viewsBini Grham, 04:53
Open / Comment
2022-01-20 12:14:22
If you want to increase in the life of God, then you must settle it in your heart that you will not at any time resist the Holy Spirit.

- #Smith_Wigglesworth
70 viewsBini Grham, edited  09:14
Open / Comment