Get Mystery Box with random crypto!

GOD'S GOSPEL

Logo of telegram channel godsgospel — GOD'S GOSPEL G
Logo of telegram channel godsgospel — GOD'S GOSPEL
Channel address: @godsgospel
Categories: Uncategorized
Language: English
Subscribers: 980
Description from channel

KNOWING God and making Him KNOWN!❤
እግዚአብሔርን ማወቅ እና ማሳወቅ!

for more information use
👉 @BiniGrham

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


The latest Messages 6

2021-11-24 16:28:12 የቀጠለ...#3

እስራኤል እንደ ሀገር 73ኛ ዓመታቸውን አክብረዋል።

ይህ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ ይህ #ትውልድ አያልፍም (ማቴ 24፡34፣ መዝሙረ ዳዊት 102፡18፣ ሆሴዕ 6፡2)
*ትውልድ*=100 አመት
ይህ 100 ዓመት የጀመረው #እስራኤል ሀገር ስትሆን እ.ኤ.አ. በ1948 ነው።

ስለዚህም 1948+100አመት=2048 ዓ.ም

2048-2021=27ዓመታት። እና
27ዓመት -7 ዓመት የመከራ ዓመታት =20 ዓመት።

ስለዚህ አሁን እስከ ንጥቀት 20 ዓመታት ድረስ ብቻ አለን።( ይህ እውነት ነው..እመኑ።)
የቤተ ክርስቲያን ዘመን እየቀረበ ነው። በጣም ከምታስቡት በላይ #ባለቁ_ሰዓታት ውስጥ ነው ያለነው።

#ከመቼውም ጊዜ በላይ #ወንጌል_መሰበክ ያለበት ጊዜ ነው። መልዕክቱ ግልጽ ነው ጆሮ ያለው ይስማ።

ለክፋት ጊዜ የለም
ለቅናት ጊዜ የለም
ለጥላቻ ጊዜ የለም
ለዘረኝነት ጊዜ የለም
ለራስ ወዳድነት ጊዜ የለም

አሁንም #በእውነትና_በእምነት ውስጥ እንዳላችሁ ራሳችሁን መርምሩ። ንስሐ ግቡና ወደ መጀመሪያው ፍቅራችሁ ተመለሱ...ተጽዕኖአችሁን #ለወንጌል ተጠቀሙበት።ወደኋላ አትበሉ።ጊዜው እጅግ በጣም አጭር ነው።የሰማችሁትና ያመናችሁት ኢየሱስ #ከምትገምቱት በላይ #ፈጥኖ_ይመጣል።

በቀን ለአንድ ስው #ወንጌልን ለመስበክ ጥረት አድርጉ። ይህን ማድረግ ከቻልን:-
1×30=30 ነፍሳት በወር
30×12 ወር =3,600 ነፍሳት በዓመት
3600×20= 72,000 ነፍሳት በ 20 ዓመት


“ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ #ዘመኑን_እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ #ቀርቦአልና።”
—ሮሜ 13፥11

Join and share it
@godsgospel
@godsgospel
632 viewsBini Grham, 13:28
Open / Comment
2021-11-24 10:15:35
All we NEED is #JESUS the Messiah!!
85 viewsBini Grham, edited  07:15
Open / Comment
2021-11-22 21:10:05
IT IS NOT GIVEN TO YOU TO #CREATE YOUR PURPOSE BUT THE ASSIGNMENT GIVEN TO YOU IS TO #DISCOVER YOUR PURPOSE.

#Prophet_Emmanuel_Makandiwa
51 viewsBini Grham, edited  18:10
Open / Comment
2021-11-19 08:48:09 ...የቀጠለ #2


1948 + 100

ኢየሱስ ይህ ሁሉ ነገር(የቤተክርስቲያን መነጠቅ፣ ታላቁ መከራ፣ የክርስቶስ ተቀዋሚ) እስኪሆን ድረስ #አንድ_ትውልድ(100 ዓመት) #አያልፍም ብሎናል።
{የበለስ ዛፍ (እስራኤል ) ወደ ምድሯ ከተመለሰችበት ዓመት(1948) ጀምሮ።}


አስተውሉ፡ ኢየሱስ ያለን #ቀኒቱንና_ሰዓቲቱን የሚያውቀው እንደሌለ ነው፣ #ቀኒቱንና_ሰዓቲቱን አታውቁም ነው እንጂ አመት ወይም ወቅቱን አይደለም። ዓመት ወይም ወቅቱን ለማወቅ #ቅዱሳት_መጽሐፍት ፍንጭ ይሰጡናል።

ኢየሱስም እነዚህ ሁሉ ነገሮች እስኪሆኑ ድረስ ትውልድ እንደማያልፍ በግልፅ ነግሮናል። #በመፅሃፍ_ቅዱስ_መሰረት ዘመኑ እስኪያልቅ 27 አመት ብቻ ቀረን(1948+100=2048)

#2048_የኢየሱስ_መምጫ_አመት_ነው_እያልኩ_አይደለም። ግን እነዚህ ሁሉ ነገሮች እንዲፈጸሙ #የጊዜ_ገደቡ ነው።


ወንድሞቼ ሆይ #ንጥቀት ዛሬም ነገም ሊሆን ይችላል የምናውቀው በመፅሃፍ ቅዱስ ትንቢት የጊዜ ቀመር መሰረት የቀሩን ዓመታት ከሶስት 10 ዓመታት #አይዘሉም። #በክስተቶች_ቅደም_ተከተል መከራው ከመምጣቱ #በፊት መጀመሪያ የሚቀድመው #የእውነተኛ_ቅዱሳን_መነጠቅ ነው። ስለዚህ ንጥቀት መቼ ይሆን?? ዛሬም ነገም ሊሆን ይችላል። አስተውሉ እናም #መንገዳችሁን_አስተካክሉ።(1948+100= 2048)


በመንፈሳዊው ዓለም ነገሮች በፍጥነት እየተከሰቱ ነው። ህይወታችሁን በእግዚአብሔር እውነት #አሁን ካላስተካከላችሁ በኋላ ላይ #ይቆጫችኃል። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ እውነተኛ ክርስቲያኖች ሁኑ። ሙሽራው #የማያፍርባችሁ ሁኑ።
ተቀደሱ፣ ጸልዩ፣ አጥኑ እና #ቃሉን አሰላስሉ።

መንፈስ የሚለውን
ጆሮ ያለው ይስማ! ‌‌

Join and share it
@godsgospel
@godsgospel
161 viewsBini Grham, edited  05:48
Open / Comment
2021-11-17 14:26:39 GOD'S GOSPEL pinned « የጌታችን ምጽአት ፅሑፉን እስከ መጨረሻው አንብቡት ማቴዎስ 24 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³⁰ “በዚህ ጊዜ የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ላይ ይታያል፤ የምድር ወገኖች ሁሉ ያለቅሳሉ፤ የሰው ልጅም በሰማይ ደመና ሆኖ በኀይልና በታላቅ ክብር ሲመጣ ያዩታል፤ ³¹ መላእክቱንም ከታላቅ የመለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፤ እነርሱም ምርጦቹን ከአራቱም ነፋሳት፣ ከሰማያት ከአንዱ ዳርቻ ወደ ሌላው ዳርቻ ይሰበስባሉ።…»
11:26
Open / Comment
2021-11-16 14:29:30
#BILL_GATES CAUGHT ON VIDEO ADMITTING #VACCINES_WILL_CHANGE OUR #DNA.

watch,listean and share

@godsgospel
121 viewsBini Grham, 11:29
Open / Comment
2021-11-16 14:26:03
ISRAELI SCIENTIST LAYS IT ALL OUT - THEY WANT TO #ROBOTIZE EVERYONE - THEY ARE INSANE.
116 viewsBini Grham, edited  11:26
Open / Comment
2021-11-15 20:50:42 @ThedeepthingsOfTheSpirit

Join him now

He is going to start a deep study on the book of Romans.
I guarantee your transformation by the power of word and Spirit of God through him!

Join him NOW( @ThedeepthingsOfTheSpirit)
49 viewsBini Grham, 17:50
Open / Comment
2021-11-15 20:33:08
የሮሜ መጽሐፍ ጥናት

@TheDeepThingsOfTheSpirit
@TheDeepThingsOfTheSpirit
47 viewsBini Grham, 17:33
Open / Comment
2021-11-13 16:55:40 የጌታችን ምጽአት

ፅሑፉን እስከ መጨረሻው አንብቡት

ማቴዎስ 24 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁰ “በዚህ ጊዜ የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ላይ ይታያል፤ የምድር ወገኖች ሁሉ ያለቅሳሉ፤ የሰው ልጅም በሰማይ ደመና ሆኖ በኀይልና በታላቅ ክብር ሲመጣ ያዩታል፤
³¹ መላእክቱንም ከታላቅ የመለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፤ እነርሱም ምርጦቹን ከአራቱም ነፋሳት፣ ከሰማያት ከአንዱ ዳርቻ ወደ ሌላው ዳርቻ ይሰበስባሉ።
³² “ከበለስ ዛፍ ይህን ትምህርት ተማሩ፤ ቅርንጫፏ ሲለመልም፣ ቅጠሏ ሲያቈጠቍጥ፣ ያን ጊዜ በጋ እንደ ተቃረበ ታውቃላችሁ።
³³ እንደዚሁም እነዚህን ሁሉ ስታዩ፣ እርሱ በደጅ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ።
³⁴ እውነት እላችኋለሁ፤ ይህ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም።
³⁵ ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን ፈጽሞ አያልፍም።


የበለሱ ዛፍ ምሳሌ ትርጉም ምን ማለት ይሆን??

ኢየሱስ ስለሚመጣበት ወቅት #ፍንጭን ሰጥቶናል።
የበለሷ ዛፍ:
1.ስትለመልም
2.ቅጠሏ ሲያቈጠቍጥ፣
-ያን ጊዜ በጋ እንደ ተቃረበ ታውቃላችሁ።

ኢየሱስ የበለስ ዛፏን እንደምትለመልምና ቅጠል መሰብሰብ #ከጀመረች_አንስቶ
1.የኢየሱስን ዳግም ምፅአት፣
2.የእውነተኛ ክርስቲያኖች መነጠቅ፣
3.የሃሰተኛው ክርስቶስ መነሳትና
4.በሰው ልጅ ታሪክ ዓለም ታይቶ የማይታወቀውን መከራ እንደሚሆን ድረስ አንድ ትውልድ(100 ዓመታት) #እንደማያልፍ_በግልፅ ነግሮናል።

"ይህ ሁሉ (ከላይ የተጠቀሱት) እስኪፈጸም ድረስ ይህ ትውልድ #አያልፍም።"ብሎ ተናግሯል።

እግዚአብሔር በኢዩኤል 6:7 ላይ የበለስ ዛፉ #የእርሱ ምድር ፣ #እስራኤል እንደሆነች #በግልፅ ይናገራል። በታሪክ እንደምንረዳው #በ70 AD ላይ እስራኤል ሃገር ተበታትና አይሁዶች በየሃገሩ እንደስደተኛ እንደኖሩ እናውቃለን። ለ2000 አመታት እስራኤላውያን ከምድራቸው ተባረው በተለያየ ሃገር ሲኖሩ ቆይተዋል። ነገር ግን #በ1948 ከሁለት ሺህ አመታት በኋላ በመሰባሰብ በቀድሞ ምድራቸው ላይ የሰፈሩ የአረብ ነዋሪ ፍልስጥኤማውያንን በመዋጋት እስራኤል እንደገና ሃገር መሆን ችላለች። ይህች ታናሽ ሃገር የመፅሃፍ ቅዱሳችን #መሃከለኛ ታሪክ እንደሆነች የታወቀ ነው። የምናነበው መፅሃፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ከህዝቡ ከእስራኤላውያን ጋር የነበረው ግንኙነት የሚያሳይ ነው። ጌታችንም ኢየሱስ ክርስቶስ የመጣው ለእነርሱ ነበር። "ወደ ገዛ ወገኖቹ መጣ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም ነገር ግን ለተቀበሉት ሁሉ በስም ለሚያምኑ (እኛ አህዛቦች) የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ስልጣንን ሰጣቸው" ዮሐንስ 1:12።
ስለዚህ የመጨረሻውን ዘመን እንድናውቅ ራሱ ኢየሱስ ከሰጠን ማስጠንቀቂያና ማንቂያ ደውሎች አንዱ የሆነው ክስተት #ለሁለት_ሺህ አመታት ከዓለም ካርታ ጠፍታ የነበረችው #እስራኤል_ወደ_ካርታ_መመለሷ ነው።

እስራኤል ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ #በ1948 ጦርነት በዙሪያዋ ያሉ የአረብ ሃገራትን እስካሁን ድረስ በታሪክም እንደተማርነው #ተዓምራት በሚመስል መንገድ ለብቻዋ 6 አረብ ሃገራትን ድል ነስታ የጥንት ጊዜ ምድሯን ተቆጣጠረች። ይህ ከሆነ በኋላ አይሁዶች በራሳቸው ዕብራይስጥ ቋንቋ "አሊያህ" ብለው በሚጠሩት የአይሁዶች ወደ ሃገራቸው መመለስ (ሁለተኛው ዘፀዓት) በ1948 ጀመረ። እስራኤላውያን ሁሉ ከዓለም ጫፍ እስከጫፍ እንደስደተኛ ከተቆጠሩበት ምድር ወደ እናት ሃገራቸው መመለስ ጀመሩ። ሃገራቸውንም ለማመን በሚከብድ ፍጥነት ማልማት ጀመሩ። ዛሬ ላይ ትልቅ ኢኮኖሚ ካላቸው ሃገራት መካከል እስራኤል አንዷ ናት። በእኛም ሃገር በኢትዮጵያ ለብዙ መቶ አመታት ፣ የእጅ ባለሞያተኛ በመሆናቸው ብቻ አይሁዶች እየተጠሉ እንደኖሩ እናውቃለን ፣ በጎንደር አካባቢ እንደኖሩ እስካሁንም ያልሄዱ ጥቂት አይሁዶች እንደሚኖሩ እናውቃለን(ፈላሻዎች)። #የአይሁች_ወደ_እስራኤል_መመለስ_እና_የእስራኤል_ምድር_ማቆጥቆጥ ፣ #ማደግና #በፍጥነት_መበልፀግ_ወደ_በለስ_ዛፍ_ቅጠሎች_መመለስን_ያሳያል።
እጅግ ለማመን በሚያስቸግር መንገድ እስራኤል በ21ኛው ክፍለ ዘመን የቴክኖሎጂን ኢንደስትሪ #በቅድሚያ የምትመራ ብቸኛ ሃገር #እስራኤል ናት። በህክምና፣ በግብርና ፣ በአዳዲስ ፈጠራ፣ በመከላከያ ጦር፣ በትምህርት #ከቀዳሚ ሃገሮች የምትጠቀስ ሃገር ናት። #ይህ_ሁሉ_የበለሷን_ዛፍ_መለምለም_ያሳያል።

ኢየሱስ ዳግመኛ መምጣትና የእውነተኛ ክርስቲያኖች ንጥቀት፣ የሃሰተኛው ክርስቶስ መነሳት የበለስ ዛፏ ማቆጥቆጥ ከጀመረች አንስቶ አንድ ትውልድ(100 አመት) #እንደማያልፍ በግልፅ ተናግሯል።


በታሪክ ውስጥ የትኛውም ትውልድ የበለስ ዛፏን ማቆጥቆጥ #ያየ_የለም።
እኛ ግን በአይናችን ይሄ ሁሉ ትንቢት ሲፈፀም እያየን ነው።

ከምንግዜው በላይ ልንነቃና በእያንዳንዱ ቀናችን እግዚአብሔርን በመፍራትና በመታዘዝ፣ ራሳችንን ከክፉ በማራቅ፣ የክርስቶስን ወንጌል እየተናገርን ብዙዎችን ከሲዖል የምንናጠቅበት ያለቀ ሰዓት ላይ እንጂ ወደኋላ ተመልሰን ከሃጢአት ጋር የምንጫወትበት ጊዜ ላይ አይደለንም።

ይሁ ሁሉ ሲሆን መዳናችሁ ከትላንት ይልቅ እንደቀረበ #እወቁ ያለው ጌታ እንድናስተውልና ንስሃ ገብተን ፣ ከጌታ ጋር ያለን ግንኙነት የምናድስበት፣ ራሳችንን በቃል፣ በፀሎት በቀረችንም #ጥቂት ጊዜ ብትሆን ለጌታ የምንሮጥበት ጊዜ እንጂ ራሳችንን የምናስቀድምበት ጊዜ ላይ አይደለንም።

ልብ ያለው ያስተውል!
ኢየሱስ ሊመጣ በደጅ ነው፣ ቤተክርስቲያን ግን ከባድ እንቅልፍ ላይ ናት። ራሳችሁን አንፁ፣ አስተካክሉ፣ አዘጋጁ።

ኢየሱስ ይመጣል!
አሜን!

#የፓስተር_በቀለ_ወልደ_ኪዳን
"ከሌሊቱ ስንት ሰዓት ነው?" የሚለውን መፅሃፍ እንድታነቡ አበረታታችኋሁ።

በተጨማሪም ይህን video አሁኑኑ ተመልከቱ


644 viewsBini Grham, edited  13:55
Open / Comment