Get Mystery Box with random crypto!

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 128.58K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
Buy ads: https://telega.io/c/bewketuseyoum19
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 200

2021-11-03 08:45:15

2.8K viewsAbela, 05:45
Open / Comment
2021-11-03 08:07:11
… እምቢ ለሃገሬ …

ምን አጠፋ ጋራው ምን በደለ ወንዙ!?
ሴፉን ያስመዘዘው፣
እብሪት ነው ጦሰኛው ጥጋብ ነው መዘዙ።

ዘራፍ አካኪ ዘራፍ…
ዘራፍ አካኪ ዘራፍ…
ዘራፍ… ዘራፍ… ዘራፍ… ዘራፍ…

ቁጣው የነብር ፥ ግርማው ያምበሳ
መካች የሌለው ፥ ቆርጦ ሲነሳ፤
ሃሞቱ ሙሉ ፥ ልቡ የኮራ
ጠላት ሰባሪ ፥ ባንዲት ስንዘራ፤
ደሙ ኩምጡ ፥ ገፁ የነቃ
ለናት ሃገሩ ፥ ቋሚ ጠበቃ።

ዘራፍ አካኪ ዘራፍ… (×2)
ዘራፍ… ዘራፍ… ዘራፍ… ዘራፍ…

ገና ከድሮው ፥ ገና ከጥንቱ
ያባቶቼ ነው ፥ አርበኝነቱ፤
ታሪኬን ረስቶ ፥ እኔን ባይፈራ
እሰጠዋለው ፥ አይኑን ላሞራ፤
ወሰኔን አልፎ ፥ ቢገኝ ከደጄ
እሰብረዋው ፥ አጥንቱን በጄ፤

ክንዴ ነበልባል ፥ መዳፌም እሳት
ያስከፉኝ ጊዜ ፥ የተቆጣው ለት
ለወደድኩትም
አልመለስም ፥ እንኳን ለጠላት።

ዘራፍ ጎበዝ ፥ ዘራፍ ጀግናው
ያባቱ ልጅ ፥ የሳተናው
ዘራፍ ጎበዝ ፥ ዘራፍ ወንዱ
የሳቱ ልጅ ፥ ያርበድብዱ።

እንኳን በወሬው ፥ ልርድ ልሰጋ
ባካል ቢመጣም ፥ እኔን ፍለጋ
እወጋዋለው ፥ በጦር ጋሻዬ
እቆርጠዋለው ፥ በጎራዴዬ
ቢያቅተኝ እኳን ፥ አለ በሬዬ
አይጠመድም ፥ ለዛ ወመኔ
አይታዘዝም ፥ በጭራሽ ለሱ
ይገለበጣል ፥ እንደ ጉሊሱ
ይከሰከሳል ፥ እንደ ጠርሙሱ።

ዘራፍ አካኪ ዘራፍ…
ዘራፍ አካኪ ዘራፍ…
ዘራፍ… ዘራፍ… ዘራፍ… ዘራፍ…

(መሰለ ከልካይ)
ከ"ታጋቾቹ" የተቀነጨበ።

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.6K viewsAbela, 05:07
Open / Comment
2021-11-02 22:17:41 ፨ጀግናው ፨

አዝማሪው ገዳዩን
ዞሮ የወድሳል
ሽማን በኣፍ ሸምኖ
እንዲሁ የለብሳል
የገዳይ ቤተሰብ
ገዳይን ጀግና ሲል
ንጉሳችን ብሎ
በህሊና ው ሲስል
የተገዳይ ደግሞ
በሃዘን ይለቀሳል
መጓዙን አቁሞ
አዝግም የነክሳል
ሁሉም ለእራሱ እምነት
ቅዱስ ነው ይለዋል
የሌላውን ደግሞ
እንዲው የረክሠዋል
ሁሉም ለእራሡ እምነት
እውነት ትክል ነው
ላንዱ ጠላት ሆኖ
ደግሞም እያየን ነው ::
አዝማሪሙ ገዳዮን
ዙሮ የወድሳል
የሸሸውን ደግሞ ፍሪ ርካሽ ብሎ
ስም ሠቶ ያረክሳል
.. ሺገዳዩ ጀግና
ፈሪውን አበሮ መንግስቱን ወርሠ
በዙፋኑ ዙፋን
ጨምሮ ነገሠ ...
እየለ በቃላት
ሰሎ አሸምንሙኖ
ገዳይ የበርታል
የለብሠዋል ጃኖ



እኛም ለምንሞተር ሰዎች ስንባል እኮ ሰዉ ገድለን "ጀግና ` ..
የምንባባል ::::::::: .....


_-_-_-_-_-_- -_-_-_-_-_-_
           #ገብረስላሴ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
306 viewsAbela, 19:17
Open / Comment
2021-11-02 21:05:05
1.4K viewsAbela, 18:05
Open / Comment
2021-11-02 19:13:33 ሚስቴን ዳርኳት

ዕፁብ ነው...
የሷ አፍቃሪያን አጃኢብ ያስብላል
መልኳ ተንኮለኛ ያየውን ይጥላል

ቀን ለኔ ወቶልኝ በሚስትነት ያዝኳት
ምዬ ተገዝቼ በወጉ አገባሇት
የሷ ማለት የኔ
የኔ ማለት የሷ
ሁኗል ከዚ ወዲህ
አፍቃሪዋ ሳይሆን
አፍቃሪያችን በዙ ሊባል ነው ከንግዲ።

ይህም ቢሆን እንኳን
አንዱ የሷ አፍቃሪ ቅናት የወረሰው
እሷን ሚጠጓትን ወንዱን የጨረሰው
ወደኔ ተጠግቶ
ሳይጥለኝ አንክቶ
እህቴ ናት ብዬ ማስወራቱን ጀመርኩ
መቼም ከመወጋት ወንድምነት መረጥኩ

አዬ...
አካል ቡጢን ፈርቶ በምላሴ ሸጥኳት
እህቴ ናት ብዬ እኔው ሚስቴን ዳርኳት

ዮኒ
ኣታን
@yonatoz

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.5K viewsAbela, edited  16:13
Open / Comment
2021-11-02 14:50:06 ቀረሽ ወደኋላ

የልጆችሽ ቀለም መልኩ ልዩነቱ
ከጥቅሙ ይልቅ በዛና ጉዳቱ
አንዱን ለሌላኛው ካሳ ስትገብሪ
ሆንሽና ቀረሽው የሬሳ ቆጣሪ።

ከ"ጉራማይሌ"

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
3.4K viewsAbela, 11:50
Open / Comment
2021-11-02 11:35:06 ሀገር ሚያህል ፥ ዋርካ ከሰው ተጠልሎ፣
ለቆረጥነው ነገ ፥ ታሪክ ተቀጥሎ፣
ዛሬ ለሆድ አድሮ ፥ በጥጋብ ሲባዝን፣
ሰርገን እየገባን ፥ በሰርጉ ተከዘን።

[ጥያቄ

ውድቀት ቢያሸንፍም ፥ ድልን አሳስቆ
ዛፍ እንዴት ፥ ይገፋል በቀጭን ሸንበቆ?

#ናታን_ኤርሚያስ
@UniqueDy

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.0K viewsAbela, 08:35
Open / Comment
2021-11-02 09:24:59 ላንዲት ማስቲካ ሻጭ ህፃን

በደብተርሽ ምትክ
ትንሽ ሱቅ ታቅፈሽ
ካልፎሂያጅ እግር ስር፤
እንደ ድንቢጥ ከንፈሽ
ጋሼ ግዙኝ ስትይ፤ አንጋጠሽ ወደ ላይ
ለጉድ ተጎልቸ፤ ምታረጊውን ሳይ
ራሴስ ይታመም፤ ምላሴን ምን ነካው
ግራዋ ይመስል፤ መረረኝ ማስቲካው !!
አፈር ጠጠር ለብሶ ፤በዶዘር ተድጦ
መስኩ ከነጎርፉ ፥
ሰማይ ከነዶፉ ፥ ለጌቶች ተሽጦ
አተር ነው እያሉ፤ አፈር ዘግኖ መፍጨት
ገነት ነው እያሉ፤ መስክ ላይ መፈንጨት
ጠበል ነው እያሉ፤ ተጎርፉ መራጨት
ይህንን ማን ሰጦሽ
ገና በልጅነት፤ ልጅነት አምልጦሽ፡፡
በምቢልታ በዋሽንት፤ በከበሮ ታጥሮ
በክራር ተማግሮ
በቆመ ከተማ
እምባሽ ቅኝት የለው ፤ ለሰው አይሰማ፡
ጠዋት የፎከረ ፤ ቀትር ላይ ሲረታ
ዛሬ ዝሎ ሲወድቅ ፤ ትናንት የበረታ
ኑሮን ያህል ሸክም ፤ ያላንቀልባ ሲያዝል፡፡
ምን ጸጋ ለብሶ ነው፤ ትከሻሽ የማይዝል፡፡

በእውቀቱ ስዩም

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
198 viewsAbela, 06:24
Open / Comment
2021-11-02 07:42:35
896 viewsAbela, edited  04:42
Open / Comment
2021-11-01 22:59:15 ምርጥ የግጥም ቻናል
177 viewsAbela, 19:59
Open / Comment