Get Mystery Box with random crypto!

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Topics from channel:
Meri
Block
Ethiopia
Fiker
Size
Баллон
Join
Share
Shaer
Available
All tags
Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 94.83K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
✥--------------------✥
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 6

2023-04-18 21:10:10 «ከአባቴ ቀጥሎ እንዳንቺ ያዋረደኝ ፣ ትንሽ እንደሆንኩ እንዲሰማኝ ፣ ራሴን እንድጠላ ያደረገኝ ሰው የለም። ከዛሬ ነገ ትወጂኛለሽ፣ በፍቅርሽ እፈወሳለሁ ብዬ ጠበቅኩሽ። በየቀኑ ናቅሽኝ!! ለፍቅሬ ምላሽሽ ሁሌም እንደበረዶ የቀዘቀዘ ቃላት ነው የምትወረውሪልኝ። <አንተም ወንድ ሆነህ?> ያላልሽኝን ቀን ብቆጥረው ከእጄ ጣት አይበልጥም!! ለአባቴ እንደልጅ እንደሰው ነው የከሸፍኩበት። አንቺ ግን ወንድነቴንም ነው የቀማሽኝ!! አብሬሽ ባሳለፍኩት እያንዳንዱ ቀን ትንሽ በትንሽ በራስ መተማመኔን እየሸረፍሽ ካንቺ ሌላ ሴት እንደወንድ እንኳን የማትቆጥረኝ እየመሰለኝ አብሬሽ ቆየሁ። ምክንያትሽን ሳትነግሪኝ ለወራት ስትዘጊኝ እጠብቃለሁ። ምክንያትሽን ሳትነግሪኝ ስትመለሺ እቀበልሻለሁ። ላንቺ ምንም ነኝ!! በፈለግሽ ሰዓት ሄደሽ ስትመለሺ የምታገኚኝ እቃሽ ነኝ!! እኩል ድርሻ ባለን ቤት ላይ እንኳን ፈላጭ ቆራጯ አንቺ ነሽ!! አንቺ አለቃ እኔ ባሪያሽ ነኝ!! ንገሪኝ ለመጥላት በቂ ምክንያት አይደለም?»

አልመለስኩለትም። ቁጢጥ ካልኩበት ተነሳሁ!!!! ቆሜ ምን እንደማስብ አላውቅም ግን ፈዝዣለሁ። እሱ ከአሁን አሁን ምን ታደርገኛለች ብሎ በሰቀቀን እየጠበቀኝ ነው።

«ይቅርታ!!! ይሄ ሁሉ አይገባህም ነበር። እንዲህ እንዲሰማህ ማድረጌንም አላውቅም ነበር። ስቀህ ማለፍህ ልክ የሆንኩ እንዲመስለኝ አድርጎኛል። ይቅርታ አድርግልኝ!! ከልቤ ነው አንተ ጥሩ ሰው ነህ!! ቢያንስ ለእኔ ጥሩ ሰው ነበርክ!! አይገባህም ያልኩህ የእውነቴን ነው። » አልኩት። ሞቶ መንግስተሰማያት ደርሶ ይሁን በእውኑ እዚህ ምድር ላይ ሆኖ ይሄን ከእኔ አፍ መስማቱ እያወዛገበው አይኑን ጎልጉሎ ያየኛል።

«ሙከራህን ብትደግመው የምምርህ እንዳይመስልህ!! ቤቱን ልሸጠው እፈልጋለሁ!! ህገወጥ ስራውን የምታቆም ከሆነ የእኔን ድርሻ ልሽጥልህና የቤት ኪራይ እየከፈልክ ስራበት። አይ ካልክ ግን ቤቱን ለቀህ ትወጣለህ!! እኔ ጨርሻለሁ!!» ብዬው ወጣሁ።

ከወጣሁ በኋላ ያ ስሜት ተሰማኝ!! ባዶ የሆነ ስሜት!! ጣዕም አልባ ስሜት!! የምሄድበትን ሳላውቅ እየነዳሁ ስዞር ቆይቼ አመሻሽ ላይ አባ መልከፃዲቅ ያሉበት ቤተክርስቲያን ሄድኩ!! እግራቸው ላይ ተደፍቼ ማልቀስ ፈልጌ ነው።ኮቴን ክለብ እረስቼው የለበስኩት እጁ የተጋለጠ ነገር ስለነበረ ሱቅ ገብቼ ነጠላ እና ሹራብ ደርቤ ቀጠልኩ።
በሩን አልፌ ቦታዬጋ ስደርስ አይኔ ከቆቡ ውስጥ ተጎልጉሎ ሊወጣ ደረሰ። አባ የሚቀመጡባት ጉቷቸው ላይ ተቀምጠው ጎንጥ እኔ በምቀመጥበት ቦታ እግራቸው ስር ተቀምጦ ያወራሉ። እግሬ ተወለካከፈብኝና ቆምኩ። አየኝ!! ምንም ቀን እንዳልዘጋኝ!! ልቤ በመከፋት ተኮማትራ ከእጄ ጭብጥ እንዳላሳነሳት፣ መከፋት እና ተስፋ መቁረጥ እንዳላሸከመኝ ሁሉ ፈገግ አለ።

.......... ይቀጥላል........

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
4.0K viewsAbela, 18:10
Open / Comment
2023-04-18 20:55:06 ሙሉሰውም ጭንቅላቱ የተዛባ እስኪመስለኝ ድረስ የሚሰራው ሁሉ የሚበላሽበት ፣ ከቀን ወደቀን የደጋፊዎቹ መወድስ እየቀነሰ የሚተቸው ሰው ቁጥር እየበዛ ጭራሹኑ አስተካክሎ የሚከውነው ነገር ጠፋው!! እዚህ ነጥብ ላይ እየፈራሁት መጥቼ ነበር። የሆነ ቀን ገድሎኝ ራሱን ሊገድል ይችላል ብዬ ማሰብ ጀምሬ ነበር። ግን ለምንድነው የማልረካው? እሱን በቁሙ ገድዬው ሌሎቹን ጨርሼ አሁንም የተሸነፍኩ ዓይነት ስሜት የሚሰማኝ ለምንድነው? ያ ሁሉ ቁስል እነርሱን ስበቀል የሚድን መስሎኝ አልነበር? ለምን አሁንም እንደድሮ ያመኛል? ያደረግኩት ክፋት እና በቀል ጥያቄዬን እንዳልመለሰ ወይም ህመሜን እንዳልፈወሰ እያወቅኩም በክፋት መቆመሬን ቀጠልኩበት።

ገንዘብ ካለ ሲደመር ስልጣኑ ያለው ሰው ካወቅኩ የማላገኘው ነገር ጥቂት መሆኑን ስረዳ የማይጣሱ ብዙ መስመሮች ጣስኩ። ከአንድ ባልደረባው ጋር በአንድ ውሳኔ ሳይግባቡ ቀርተው እራሱ ስንቴ መጥቶ የባለገበትን ቤት እንደማስፈራሪያ ተጠቅሞ የሙሉ ሰውን እጅ ጠመዘዘው። ሙሉሰው አይደለም የማይፈልገውን ውሳኔ መወሰን ቢሞት ራሱኮ ግድ አይሰጠኝም ግን ሰው መበቀል እና ክፋት ደሜ ውስጥ ያለ ነገር መሰለኝ። ሰውየው ሲባልግ በድብቅ ቀረፅኩት። የተከበረ ባለትዳር እና የልጆች አባት ስለሆነ የቀረፅኩትን ቪዲዮ ሳሳየው ሽንቱን ሱሪው ላይ ሊሸናው ምንም አልቀረውም። የሚገርመው ግን <ከዚህ በላይ ምን ሊመጣ?> ብሎ ይሆን አልገባኝም። እየመጣ መባለጉን አላቆመም!! በድብቅ ካሜራ እንደቀረፅኩት ለአንድ ሰው ትንፍሽ ቢልና አንድ ደንበኛ ባጣ በራሱ እንዲፈርድ አስጠንቅቄዋለሁ። እውነትም ለማንም ትንፍሽ ሳይል ቀርቶ ይሆን ወይም የነገራቸውም ሰዎች እንደእርሱ ሱሳቸው በልጦባቸው አላውቅም የቀረ የለም። ለምናልባቱ የምፈልጋቸውን ሰዎች የፖርን ፊልም ማስቀመጤ አልቀረም። አስፈልጎኝ የምጠቀምበት ቀን እስኪመጣ ድረስ

የሙሉ ሰውን ከቀልቡ አለመሆን ተከትሎ ህዝቡ በሱ ላይ እንዲነሳ አጋጋይ በዛ!! ጨዋ ናቸው የሚባሉት እንኳን እሱን ለመጣል ተወለካከፉ!! ጨዋታው ስላዝናናኝ ብቻ ቆሻሻቸውን እየፈለጉ ሲሸነፉ ማየት የበላይነት ስሜት ስለሚሰጠኝ ወደድኩት። ለእኔ ቀላል ጨዋታ እንደሆነው ለእነሱ አልነበረም እና ከሙሉሰው ጀርባ ነገር የምቀምረው እኔ መሆኔን ሲያውቁ ሁለት ተቃራኒ ጠላቶች አፈራሁ። የተወሰኑት ሊያጠፉኝ የሚያደቡ ሲሆኑ የተቀሩት መዝራት የፈለጉትን ክፋታቸውን እና ወጥመዳቸውን በእኔ ተከልለው መከወን የሚፈልጉ ጥቅመኞች (አጋጣሚውን ካገኙ በራሴው ወጥመድ የሚያጠምዱኝ ሴረኞች ናቸው።) ሁለቱም ወገን በአይነቁረኛ የሚፈራኝ እና የሚጠላኝ ሰውም ሆንኩ። ባሎች ለሚስቶቻቸው ስለእኔ አሙላቸው። ሚስቶች ተሰብስበው ስጋዬን በሉት። በውስጣቸው ግን እነርሱ በባላቸው ላይ የሌላቸው ስልጣን እኔ ስላለኝ ቀኑ!! ተሰብስባ በመንገሽገሽ ስሜን የምትጠራ ለብቻዋ ስትሆን ልታገኘኝ ትፈልጋለች።

እኔም ሲሰለቸኝ እሱም ሲታክተው አንድ ቀን ቤቱ ሄድኩ!! ባልገድልህም ሞተሃል ይበቃሃል ልለው ነበርኮ አካሄዴ! ከልቤ በቅቶኝ በቃህ ካሁን በኋላ የምፈልገውን አግኝቻለሁ እና በቀሌ በቅቶኛል!! ትቼሃለሁ!! ልለው ነበርኮ!!

ሞትን ራሱ በዓይኑ ያየ የሚመስል ህፃን እያባበለ ደረስኩ!! በፊት እቤቱ የነበረው ዘመዱ እኛ መረጃ ከያዝንበት በኋላ አዳሪ ትምህርት ቤት እንዲያስገባው ያስገደድኩት እኔ ነበርኩ። የህፃኑን መንሰፍሰፍ ሳይ ዘንግቼው የነበረው ያኔ ሱሪውን ዝቅ አድርጎ የመለሰው መጣብኝ። ሲያየኝ ከመደንገጡ፣ መቀበጣጠሩ፣ ውክቢያው፣ ህፃኑ እንዲሄድ ማካለቡ ……. የሆነው ነገር ያልገባኝ መስዬ ተረጋጋሁ!! ህፃኑ የጎረቤት ልጅ መሆኑን አረጋግጬ ልጁን አባብዬ ወደቤቱ መልሼ ምንም እንዳልተፈጠረ ወይም እንዳልገባኝ መሰልኩ። እስኪረጋጋ እና ድንጋጤው እስኪለቀው ጠበቅኩት። ስመጣ አስቤው የመጣሁትን ነገርኩት።

«እውነትሽን ነው? በምን አምንሻለሁ? ቪዲዮዎቹን ካልሰጠሽኝ በምን አምናለሁ? የሆነ ቀን ሀሳብሽን ብትቀይሪስ?» አለኝ

«ከቃሌ ውጪ ምንም ማስተማመኛ የለህም!! ግን ሁሉንም ነገር ወስጄብሃለሁ ከዚህ በኋላ ምን ቀረኝ ብዬ ካንተጋ አኩኩሉ እጫወታለሁ? ግን እኔስ በምን አምንሃለሁ? ማረችኝ ብለህ ልትገድለኝ ብትሞክርስ? ማረችኝ ብለህ አሁንም የሌላ ለጋ ህፃን ህይወት እንደማታበላሽ በምን አውቃለሁ?» ስለው ከተቀመጠበት ዘሎ ተነሳ!! የዚህ ቀን ነው እንደአጓጉል አድርጌ ገድዬው እጄን ለፖሊስ የሰጠሁት!!!

* * * * * * * * *

ዳዊት በሩን አልፎ ሲገባ ዋናው የጭፈራ ወለል መሃል ቆሜ ቤቱን እየቃኘሁ ነበር። ሌባ አይኖቹ እየተቁለጨለጩ ወደኋላም ወደፊትም ከማለቱ በፊት ፊቴን ማጥናት ያዘ።

«አለቃ የለብኝም ብለህ በፈለግክ ሰዓት ነውኣ የምትገባ የምትወጣው?» አልኩት ሊገድለኝ የድሮ ፍቅረኛውን እንደላከብኝ ምንም ፍንጭ እንደሌለኝ መስዬ

«የኔፍቅር አትደውይልኝም ነበር? መጥቼ እጠብቅሽ ነበርኮ» ብሎ በመገላገል እየተነፈሰ ሊያቅፈኝ ተጠጋኝ!! አንገቱን አንቄ ወደላይ አንጠለጠልኩት እና እግሩ አየር ላይ ሲወራጭ ፣ የግንባሩ ደምስር ሲፈጥ እያፀዱ የነበሩት ሁለት ሴቶች መሄድም መቆምም ተወዛግቦባቸው ሲያዩኝ ቆይተው አንዷ መጥታ እግሬ ስር ወድቃ ትለምነኝ ጀመር።
«ተነሺ ከእግሬ ላይ!!» ብዬ ጮህኩባት

«በእመቤቴ ይዤዎታለሁ!! እንደው በሚወዱት ይሁንብዎ!! እጆት ላይ ይሞታል!! ኸረ እንኳን አንጠልጥለውት በአንድ ጥፍ ባህር የሚሻገር ነፍሰ ቀጭን ሰበብ ይሆንብዎታል።»

«ተነሺ ከእግሬ ላይ አልኩኮ!! እንዲሞት አይደል እንዴ ታዲያ!» ጮህኩኝ ድጋሚ

«እኔንም እንደፈለጉ ያድርጉኝ ከፈለጉ አልነሳም!!» ብላ አንድ እግሬ ላይ ተጠመጠመች። ሌላን ሰው ለመታደግ መሬት መንበርከኳ ገረመኝ። ትንፋሽ አጥሮት ሲልሞሰሞስ እያየሁት አሰብኩ!! ንዴት ላይ ሆኜ በፍፁም የማስብ ሰው አልነበርኩምኮ!! የድሮዋ እኔ ብሆን እጄ ላይ ይህችን ደቂቃ አይቆይም! ገና ሲመጣ ዘግቼው ነበር። ሆኖልኝ ቆይቶ እንኳን ቢሆን እግሬ ስር የተደፋችውን ሴት ታግሼ ተነሺ አትነሺ ግብ ግብ አልገጥምም! ይሄኔ ገንብሬ ጥያት ነበር!! አሁን ተቀይሬያለሁ ወይም ለመቀየር እየሞከርኩ ነው! መሬቱ ላይ ለቀቅኩት!! ሴትየዋ ከእግሬ ላይ ተነሳች። እየተንከባለለ አስሎ ሲያበቃ! መሬቱ ላይ ቁጢጥ ብዬ

«ለምን? ለምን እንዳደረግከው ብቻ እውነቱን ንገረኝ!! ከዋሸኸኝ ኪዳንን ይንሳኝ እጨርስሃለሁ!!» አልኩት! ለገንዘብ ብሎ እንደማያደርገው አውቃለሁ። የገንዘብ ችግር የለበትም!!

« ግልፅ አይደል እንዴ? ስለምጠላሽ!» አለኝ እስከዛሬ አናግሮኝ በማያውቀው ጥላቻ እና ድፍረት። ደነገጥኩ። ወዲያው ከአፌ ቃል አልወጣም!!

«ልትገድለኝ እስከሞከርክ ቀን ድረስ እወድሻለሁ ስትለኝ አልነበር? እየጠላኸኝ ነው አብረኸኝ የነበርከው? ደግሞስ ምን አድርጌህ ነው እስከመግደል የምትጠላኝ?» ስለው ተነስቶ እዛው መሬቱ ላይ ተቀመጠ እና ቆመው ሲያዩን የነበሩትን ሴቶች አያቸው። እየተሯሯጡ ወደ ውስጥ ገቡ።
3.0K viewsAbela, 17:55
Open / Comment
2023-04-18 20:55:06 የመኖር አካፋይ የመሞት ሲሶ መንገድ መሃል........


(ሜሪ ፈለቀ)

ክፍል 29

ሰውነቴን ያጋራሁት ወንድ ሊያስገድለኝ ከመሞከሩ በላይ የተሸነፍኩለት ሰው ስልኩን ዘጋግቶ መጥፋቱ ልቤን ሊያበድነው ይገባ ነበር? ክህደት ያውም ለመግደል እስከመሞከር የደረሰ ክህደት ይበልጣል ወይስ መተው? ጭፈራ ቤቱ እስክደርስ በዳዊት ከምናደደው እኩል በጎንጥም እየተናደድኩ ነበር የምነዳው! እንደደረስኩ በሩን በረጋግጄ ስገባ ለወትሮው የሚውልበት ቢሮው ዳዊት የለም። እሱ እስኪመጣ እየጠበቅኩ ቤቱን እየተዘዋወርኩ ማየት ጀመርኩ። ገና ረፋድ ስለሆነ ከሚያፀዱት ሰዎች ውጪ ማንም የለም!! ምንድነው የማደርገው አሁን? መቼም እንደድሮው ስራ ብዬ አልቀጥልበትም! ወይም ቢያንስ የአገልግሎቱን ዝርዝር ማስተካከል ይኖርብኛል!! ከዋናው ጭፈራ ቤት ይልቅ ከሀያ እጥፍ በላይ ገቢ የሚያስገኙት ባለሀብቱ እና ባለስልጣናቱ የሚያዘወትሯቸው በድብቅ የሚከወኑት የሴቶቹ ገላ እና የሚሸጡት አደንዛዥ እፆች ናቸው!! እነዚህ አገልግሎቶች ከተቀነሱ እንደማንኛውም የከተማዋ ጭፈራ ቤቶች ሰካራም የሚራገጥበት ወለል ብቻ ነው የሚቀረው!

እዚህ ቤት ስንቷ ወጣት የሀብታም እና የባለሀብት መዝናኛ ሆናለች!! (ስንቷ ክብሯን ሸጣ ሆዷን ሞልታለች! ወይም እናቷን አሳክማለች።) እዚህ ቤት ስንቱ ወጣት የማይወጣበት ሱስ ውስጥ ተዘፍቋል! (VIP ደንበኛ የሚባሉት ኮኬይን የሚገዙት ናቸው!! ሺሻ እንዲሰራላቸው ያዛሉ ኮኬይን ተደባልቆ ያጨሱታል። ኪሳቸውም ጤናቸውም አብሮ ይጨሳል።) እዚህ ቤት ስንቱ ባለጌ በሚስቱ ላይ ማግጧል (ስንቷ ምስኪን ሚስት እቤቷ ልጆቿን አቅፋ አልቅሳለች) ፣ እዚሁ ቤት ስንቱን ብልግና ማየት ተለማምጄ እንደ ጤንነት ቆጥሬዋለሁ!

ከሙሉሰው ጋር ተጋብተን ትንሽ እንደቆየን ፣ እንግዳ ወይ ጓደኞቹ እቤቱ ሲመጡ እቤቱ ሄጄ እንደሚስት ስብር ቅንጥስ ብሉልኝ ጠጡልኝ ማለት የለመድኩ ጊዜ ፣ እኔ ጠባቂ መሆኔ ቀርቶ በጠባቂ መታጀብ የጀመርኩኝ ጊዜ (አስፈላጊ ሆኖ አልነበረም! ለምን ጠባቂ እንደሚያጅበውም አይገባኝም!! ታይታ ካልሆነ በቀር) ፣ በቴሌቭዥን እንኳን ለማየት ወራት ከምንጠብቃቸው ባለስልጣናት ጋር የተለያዩ ክስተት እና ድግሶች ላይ የባሌን እጅ ቆልፌ መታየት የለመድኩ ጊዜ ፣ አንቱ የምለው ባለስልጣን ሚስት ባሏን ስታማልኝ የለመድኩ ጊዜ ፣ ራሴን ከእነርሱ እንደአንዳቸው ስቆጥር ያልታየ ድግስ ደግሼ እቤት እንዲታደሙልኝ ማድረግ የጀመርኩ ጊዜ፣ ………. ያኔ ጭፈራ ቤቱን በእኔ ስም እንዲያዞርልኝ አስደረግኩት። (እንደ ዓረፍተነገሩ እጥረት ሂደቱ ቀላል አልነበረም!! ትልቁ የገቢ ምንጩ ነው!! ባለስልጣናቱ የሚመጡት እሱን ስለሚያምኑት ነው!! )

ሌላው ጭንቅላቱን የምዘውርበት ጉድፉ ጭፈራ ቤቱ ነው! <ሌላውን ነውርህን ተወውና በወጣት ሴቶች ገላ እንደምትነግድ ፣ እፅ እንደምትነግድ ቢያውቅ እንደቅዱስ መልዓክ የሚያይህ ህዝብ ይቅር የሚልህ ይመስልሃል? > ራስምታት የሚቀሰቅስበት ርዕስ ነው።) ስራውን ለመልመድ ትንሽ ወራት ፈጀብኝ ግን ስለምደው ከእርሱ በተሻለ ያዝኩት ምክንያቱም እኔ ሙሉ ሀይሌን ተጠቅሜ እንጂ እንደእሱ ድብብቆሽ እየተጫወትኩ እና በትርፍ ጊዜዬ አልነበረም የምሰራው። ወደአካውንቴ ከሚያስገባልኝ ጠርቀም ያለ ገንዘብ በተጨማሪ ቁጭ ብዬ ራሴን የምሰማበት ጊዜ ስለማይሰጠኝ ወደድኩት።

እቅዴ በምፈልገው መንገድ እየሄደ ያልሞላልኝ ያን እናቴ ስትሞት መሳሪያ ዘቅዝቆ ይዞባት ተራ ሲጠብቅ የነበረ ደመኛዬን መድፋት ነበር። የሚኖረው አዲስአበባ ቢሆንም እዚህ ግባ የሚባል ማዕረግም ሀብትም ያለው ሰው አልነበረም!! ከሙሉሰው ጋር ግን በየእለቱ የሚገናኙ ሰዎች ባይሆኑም ቢያንስ የአንዳቸውን ፌስቡክ ፖስት አንዳቸው ሼር የሚደራረጉ ወዳጃሞች ናቸው!! እቅዴ ግልፅ ነበር ለሁለታችንም!! አንድ ቅዳሜ <ኸረ ተጠፋፋን ለምን ምሳ አንበላም?> ብሎ ሙሉሰው እንዲቀጥረው፣ ከዛ ሲገናኙ እኔ ባለሁበት ምሳ ልንበላ! (የመጨረሻዋን ምሳ) ስንጨርስ መኪናውን እኔ ልሾፍር ፣ ከዛማ ከከተማ አርቄ ወስጃቸው ትክክለኛ ማንነቴን ነግሬው ሬሳውን ለጅብ ጥዬ መምጣት ነበር እቅዴ!! ይሄን ከ10 ጊዜ በላይ ለሙሉሰው ነግሬዋለሁ!!

የዚህን ወቅት ከእኔ የሚያመልጥበት መንገድ መሞከሩን ተስፋ አልቆረጠበትም ነበር። በእቅዱ መሰረት መጥተን ከምሳ ወጥተን ወደመኪናችን ስንሄድ ሙሉሰው ለሰውየው እኔ ያልሰማሁትን ግን ሲመስለኝ እራሱን እንዲከላከል ወይ ልገድለው እንደሆነ አልያም ማን እንደሆንኩ ብቻ አላውቅም የነገረው መልዕክት አደባባይ ላይ ሽጉጥ አስመዝዞታል!! (ሙሉሰው አስቦበት ያደረገው ነገር መሆኑ በሚያቃጥርበት መልኩ ሰውየው መሳሪያ ስላልታጠቀ የሱን ሽጉጥ መውሰድ የሚችልበት አቋቋም ላይ ኮቱን ገልጦለት ነበር የቆመው) ሀሳቡ እሱ ማድረግ ያልቻለውን ሰውየው እኔን እንዲገድልለት ነበር። ተቀደመ እና ሰውየው እዛው ሞተ። በሰውየው ሞት ከማዘን በእኔ አለመሞት ሲበሳጭ ላየው ግራ ያጋባ ነበር። አደባባይ ላይ ስለነበር የሆነው ሁሉ የሆነው ታሰርኩ!! የዚህን ጊዜ ነው እስር ቤት ከእሙጋ የተዋወቅነው። ነገር የማትፋታ ጋዜጠኛ ነበረች። ያልሆነ ነገር እያነፈነፈች አላፈናፍን ስትላቸው ነው እረፍት እንድታደርግ ያስገቧት!! እሷ እስር ቤቱን ለምዳዋለች። ሲፈቷት ደግሞ ሲያስሯት፣ ደግሞ የሆነ ነገር ትቆፍራለች ደግሞ ይከቷታል። ለመጀመሪያ ጊዜ በህይወቴ ሳይከብደኝ ያወራኋት ፣ ሳልደብቅ ያጫወትኳት ፣ ሳትፈርድብኝ የሰማችኝ ፣ ውርደት እና ክፋቴን እንኳን የተረዳችኝ የመጀመሪያ ጓደኛዬ ሆነች። ከሶስት ወር በኋላ ምርጫ ስላልነበረው ሙሉሰው በሚኬደው ሄዶ እራሱ አስፈታኝ። እሙም ከወራት በኋላ ተፈትታ ከእስር ቤት ውጪ ጓደኝነታችን ቀጥሎ ነበር።
ወጥቼ ብዙም ሳይቆይ አንድ ባንክ ውስጥ በራሱ ፣ በእህቱ ፣ በአንድ የሩቅ ዘመዱ …… ደማምሮ የያዘውን 48% አክሲዮን ተቀበልኩት። እኔም በራሴ ፣ በኪዳን እና በእሙ ስም አደረግኩት!! የዚህን ጊዜ <እንደውም መልቀቂያ አስገብቼ ስልጣኔን እለቃለሁ!! ከዛ ምን ይመጣል?> ብሎ ፎክሮ ነበር። እንደባለስልጣን ሳይሆን እንደተራ መናኛ ሰው ራሱ የሚጠብቀው ነገር ቅሌት መሆኑን እየደጋገምኩ ማስታወስ ነበረብኝ። ይፎክራል እንጂ እንደማያደርገው አውቃለሁ። የስልጣን ፍቅሩ ነፍሱን እስከመገበር የሚያደርሰው ነው። ቀስ በቀስ ሀብቱን ስቀበለው። <አይኔ እያየ አትበያትም! ገድዬሽ ከሀገር እጠፋለሁ!> የሚልበት ቀን ብዙ ነበር!!

ከዚህ በኋላ ግን ሁሉም ሲኖረኝ ፣ ከህፃንነቴ ጀምሮ የኖርኩለትን ጠላቶቼን የመግደል ህልም ሳሳካ ፣ ካሰብኩት በላይ ገንዘብ እና አቅም ሲኖረኝ ………. ሁሉም ቀስ በቀስ ጣዕሙን እያጣብኝ መጣ!!! የምኖርበት ህልም አጣሁ!! ለራሴ ስል የምለው ምንም ነገር ጠፋኝ!! ለካንስ በበቀል ስካሬ ውስጥ ወጣትነቴን ሰውቼዋለሁ፣ ሴትነቴን ሰውቼዋለሁ፣ እናት የመሆን እድሌን ቀርጥፌዋለሁ ፣ ሚስት የመሆን መንገዴን ዘግቼዋለሁ ፣ ከሁሉ በላይ ግን ሰው መሆንን ገብሬ ከሰውነት ወርጃለሁ!! ………… ከዛማ በህይወቴ ከኪዳን እና በጥቂቱ ከእሙ ውጪ ምንም ነገር ፈገግ የማያስብለኝ ፣ ልኩን ከስህተቱ ያደበላለቅኩ ፣ ባህልን ከዘመናዊነት ያቀላቀልኩ ፣ ብልግናን ከጨዋነት ያጣረስኩ ፣ ምን ለምን እንደማደርግ የተወናበደብኝ ሆንኩ!! ሲረጥቡ መበስበስ ለምጄ የለ? ተበሳበስኩት!!
2.4K viewsAbela, 17:55
Open / Comment
2023-04-18 20:03:44
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ከፍተዋል። JOIN በማድረግ መረጃዎቻቸውን ይከታተሉ።
134 viewspetelare Stay true, 17:03
Open / Comment
2023-04-18 19:59:13
የተወለዱበትን ወር በመምረጥ ኮከቦን ይመልከቱ
203 viewspetelare Stay true, 16:59
Open / Comment
2023-04-18 19:35:44 ተጋባን እንጂ አብረን አንኖርም ነበር። በአደባባይ እሱ የሚገኝባቸው ቦታዎች ግን እገኛለሁ። በዚህ አጋጣሚ ከባለስልጣኑ ማህበረሰብ ጋር የመቀላቀል እድል ኖረኝም አይደል? ሳይወድ በግዱ እየገለፈጠ <ሚስቴን ተዋወቁልኝ> ይላል። ሰዎቹን ማጥናት ተጨማሪ ስራዬ ሆነ። የመጀመሪያ ስራዬ የነበረው ሌሎቹን የአባቴን ገዳዮች ራሱ እንዲነግረኝ ማድረግ ነው። የድሮ አብሮአደጎቹጋ ሁሉ ደውሎ የዛን ቀን አብረውት የነበሩትን አጣራ!! የምፈልገው አንድ እሱን ሁለት እናቴ ስትደፈር መሳሪያ ይዞ ቆሞ የነበረውን ሶስት የአባቴን ሬሳ ተሻግሮት ያለፈውን አራት እኔ በመልክም በስምም የማላውቀው አባቴ ላይ የተኮሰው ሰውዬ!! አባቴ ላይ የተኮሰውን ሰውዬ እራሱ ሙሉሰው እንዲገድለው አደረግኩ! ተጨማሪ ወንጀልም እንደማስረጃ ለመያዝ!! ሰውየው <ባልታወቀ ሰው ተገድለው ተገኙ> ተብሎ ተቀበረ። የአባቴን ረሳ ተሻግሮት ያለፈው ኮቴውን ብቻ የማስታውሰው ሰውዬ ከልጅነት ቀዬዬ እልፍ ብሎ ያለች ሰፋ ያለች ከተማ ውስጥ ሹም ሆኖ ነበር የሚሰራው!! እሱን ፀጥ ለማድረግ ግርግር አላስፈለገም ነበር።

እናቴ ስትደፈር መሳሪያ ይዞ ቆሞ ሲያያት የነበረውን ሰውዬ ለራሴ ቆጥቤ አስቀመጥኩት!!
እየቆየ ቀን ቀንን ሲተካ ኮሽ ባለ ቁጥር የሚደነግጥ፣ ወኔው የተሰለበ ድንዙዝ እየሆነ መጣ። ያልሞተም ህያው ያልሆነም ድንዙዝ ሆነ። ባልደረቦቹ <ደህና ነው?> ብለው እኔን ይጠይቁኛል። <ኸረ ደህና ነው!> እላለሁ!!

ከአረቡ አለቃዬጋ እዚህጋ ተፋታን!! አንዳንዴ የሆነ ነገር ስፈልግ እደውልለታለሁ። የሚፈልገው ነገር ሲኖር ይደውልልኛል። ሊያስፈልጉኝ የሚችሉ ቁልፍ ሰዎችን መቆለፊያ ተንኮል የጠቆመኝ እሱ ነው!! ወሳኝ ስልጣን ላይ ያሉትን ሰዎች ቆሻሻ መያዝ!! እዚህ ነጥብ ላይ ከእርሱ የተሻለ ለመረጃ ቅርብ የነበርኩት እኔ ነበርኩ። ምክንያቱም የከፍተኛ ባለስልጣን ሚስት ነኛ!! የታዘዘውን ያቀርባል!! የደሳለንኝ ከውጪ ሀገር ባለሃብት ጋር ተሻርኮ የወርቅ ማዕድን የተገኘበትን መሬት ለአበባ ልማት አንድ ሀገር ሄክታር የተፈራረመበትን ከሰዎቹ ጋር የነበረውን ኮንፍራንስ የሚያሳይ ቪዲዮ ጭምር ያቀበለኝ እራሱ ነው!!!

በዚህን ወቅት ነው ብዙ ክፋቶችን ፣ ብዙ ተንኮሎችን ከዛም ዛሬ መረጃ እንዲያቀብለኝ የምጠብቀውን ሰዌን ጨምሮ ብዙ ሰዎች ያወቅኩት።

**********
ከጎንጥ በፊት ህይወት ያልነበረኝ ይመስል የምሄድበት ወይ የምሰራው ጠፋኝ!! ቀኑ አልገፋ ብሎኝ እሙጋ ሄጄ የተፈጠረውን አንድ በአንድ ነግሪያት ራሱ ጊዜው አልሄደም። ወደከተማ ተመልሼ ደጋግሜ ብደውልለት ስልኩ አይሰራም!! እንዲህ በአንድ ቀን ሳቄንም ተስፋዬንም ይዞብኝ እብስ የሚለው ምን ቀን ነው እንዲህ ልቤን ለራሴ ሳላስቀር የሰጠሁት? ምን ቀን ላይ ዓለሜ በእርሱ ውስጥ የታጠረው? ማልቀስ አማረኝ ከዛ ደግሞ ሽንፈት መሰለኝና ዋጥኩት። ሲመሻሽ ቤተክርስቲያን ገባሁ ግን ግራ ተጋባሁ!! ለእግዚአብሄር ስለወንድ ይፀለያል? ምን አድርግልኝ ተብሎ ነው የሚፀለየው? ተውኩት!! ዝምብዬ ለረዥም ሰዓት ተቀምጬ ወጣሁ!!

ውሸቱን ነበር! ቢወደኝ ኖሮ ሁለት ቀን ሙሉ እንደምጨነቅ እያወቀ ስልኩን አጠፋፍቶ አይጠፋም!! የእኔ መጨነቅ ይቅር እሱስ አልናፍቀውም? አሁንም እየሰለለኝ ይሆን? አዳር ያልሆነ አዳር አድሬ ጠዋት መረጃውን ላከልኝ!! መጀመሪያ ያየሁት የጎንጥን ነው!! ምንም የተለየ ነገር የለውም!! ተጨማሪ መረጃ ብሎ የጨመረው እኔ የማውቀው ነው!! ስልኩን ደወልኩ

«እንዴት ምንም ተጨማሪ ማስረጃ አታገኝም!?»

«አንቺኮ የፈረንጅ ፊልም ላይ እንደምታዪው ካልሆነ የምትይው ነገር አለሽ!! ሜላት ኢትዮጵያ ውስጥ ነን መረጃዎች በሙሉ አይመዘገቡም!! ከዛ ደግሞ ሰውዪሽ ሌላ ምንም ድብቅ ነገር የሌለው ከሆነስ?»

«ይኖረዋል!! ስለማታውቀው ነው ይኖረዋል!»

«የተቀሩትን መረጃዎች ግን አይተሻቸዋል?» አለኝ አይተሻቸው ቢሆን ኖሮ ስለሰውዬሽ አትጨቃጨቂኝም ነበር በሚል ለዛ። ስልኩን ዘግቼ የተቀረውን ፎልደር ከፈትኩ!!

«ይሄ የውሻ ልጅ አውቄዋለሁ!! እገለዋለሁ!!» አልኩ ለራሴ ጮክ ብዬ!! ኮቴን እንደነገሩ ደርቤ መኪና ውስጥ ገብቼ ወደክለቡ ነዳሁት!!

.......... ይቀጥላል........

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
414 viewsAbela, 16:35
Open / Comment
2023-04-18 19:35:44 ከዛን ቀን በኋላ በአፉ ምንም ባይናገርም አስተያየቱ ተቀየረ። ዓይኖቹን ሳይነቅል ሲያፈጥብኝ ቆዳዬን ያሳክከኛል። ተስተካክዬ መቆም ያቅተኛል። ከቀናት በኋላ ሆነ ብሎ እዛ ቤት እንድንሄድ አደረገ እና በሴቶቹ ፋንታ ሙሉሰው እንዲመጣ ጠየቀ። ሙሉሰው ከአንድ ጠባቂው ጋር መጥቶ በወዳጅ ሰላምታ ማሽቃበጥ ያበዛበት ዓይነት ሰላም ብሎት ተቀመጠ። ዘለሽ እነቂው እነቂው የሚለኝን ስሜቴን ተቆጣጥሬ ቆምኩ። ሆነ ብሎ እሱ ፈላጭ ቆራጭ መሆኑን ሊያሳያኝ ያደረገው ነገር እንደሆነ ያስታውቅበታል። ቢገጣጠም የማይቀና አማርኛ እያወራ በአይኑ እኔን ያጠናል። ሙሉሰው ወጥቶ ሲሄድ «የዚን ያህል ቀላል ነበር።» ብቻ ብሎ ዝም አለ።

ለሳምንታት በራሴ መንገድ መረጃ ላገኝ ዳከርኩ። ሌላው ቀርቶ ጭፈራ ቤቱ እንኳን ድንገት የሆነ ሰዓት ነው እንጂ የሚመጣው ማንም ሰው የሚመጣበትን ሰዓት አያውቅም። ድንገት እድለኛ ሆኜ እንኳን ባገኘው ጠባቂ አለው!! ከዛ ግን ያ ሰይጣን ሰውዬ ያቀበለኝ ሀሳብ ውስጤ ቀስ በቀስ ማደጉን ያወቅኩት። ባገኘሁት አጋጣሚ ልገድለው አለመፈለጌ ገባኝ!! ቁጭ ብዬ አስቤ አስቤ ማሰሪያዬ <ከነነፍሱ እፈልገዋለሁ! የዛን ቀን አብረውት የነበሩትን ስማቸውን የማላውቃቸውን ጨምሮ መረጃ ይሰጠኛል። እንደውም እሱ መጨረሻ ላይ ነው መሞት ያለበት!> የሚል ሆነ። ሊሆን የማይችል ቅዠት ይመስለኛል ግን ማሰብ ማቆም አቃተኝ። ግን እንዴት? አላውቅም!!!

«እሺ!» አልኩኝ ጠብ የሚል ነገር ከሌለው ብዙ ልፋት በኋላ!! «ነገር ግን በቅድሚያ የማገኘውን ነገር በዝርዝር ማወቅ እፈልጋለሁ!»

ክብሬን ሸጬ በቀል ሸመትኩበት!!! ካሰብኩት በላይ ነገሮች ቀለሉልኝና የሚያስፈልገኝ ነገር ሁሉ ኖረኝ። እኔ ግን ጎደልኩ!! ለቀናት እራሴው እሺ ብዬ ተስማምቼ የተኛሁ ሳይሆን እንደእናቴ የተደፈርኩ አይነት ስሜት ተሰማኝ። በእንባ የማላጥበው ዓይነት መቆሸሽ ሆነብኝ!! <ጥላቻ ከፍቅር ያይላል> ያለው ይሄን መሰለኝ። የገዛ ሰውነቴ የሆነ ቦታ አስቀምጬው መንቀሳቀስ ብችል አሰኘኝ። ይሄን የውስጤን ጩኸት ላለመስማት በነጋ በጠባ ሴራ መጎንጎን ሆነ ስራዬ!! ከረጠቡ አይቀር መበስበስ ነው በክፋት ተጠመቅኩ። ተንኮል አስራለሁ እፈታለሁ!! ደጋግሜ ረከስኩ!! ደጋግሜ ራሴን ረሳሁ።

ሙሉሰውን እንዲወደኝ አድርጌው አይደለም ያገባሁት!! እጁ ባይያዝበት የመጀመሪያ መግደል የሚፈልገው ሰው እኔ ነኝ!! እንዲያገባኝ አስገድጄው እንጂ!! አብዛኛው ባለስልጣን አንድ የሆነ ድክመት ወይ አንድ የሆነ ቆሻሻ ይኖረዋል። ወይ በሚስቱ ላይ ሲማግጥ ወይ በሃገር ላይ ሲማግጥ ብቻ የሆነ መረጃ ይገኝበታል። ሙሉሰው አስለፋን!! ጭራሽ ምንም ማግኘት ከበደ። በዘመድ አዝማዱ ስም ጭምር የያዛቸው ንብረቶች እና ከሀገር የዘረፋቸው ሀብቶች ማስፈራሪያ ሊሆን ቢችልም በቀላሉ በገንዘብ ሃይል መረጃዎቹን ድራሻቸውን ማስጠፋት ይችላል። የራቁት ጭፈራ ቤቱ ውስጥ በጓሮ ተሹለኩልከው የሚገቡትን ባለስልጣናት በቀላሉ በሴቶቹ ማጥመድ ይቻላል። እሱ ግን ከሴት ጋርም በፍፁም ምንም አይነት ንኪኪ የሌለው ሆኖ ተገኘ። ምናልባት ቤቱ የሱ ስለሆነ ሰራተኞቹ ባሉበት መልከስከስ ስለማይፈልግ ነው ብለን አስበን። (በሃሳቡ ተስማማሁ እንጂ ሀሳቡን የሚያመነጨው አለቃዬ ነው) እቤቱ የምትሰራዋን ሰራተኛ ያዝናት። ጭራሽ እንደውም በበጎ አድራጎት የሚታወቅ ከላዩ ላይ ዝንቡን እሽ ብል ግር ብሎ የሚወጣለት ህዝብ ያሰለፈ ሰው ነው። እጅ ወደመስጠቱ ስንቃረብ ከስንት መላምትና ልፋት በኋላ ማንም ሰውጋ የማይሰማ ማንም ሰው የማይገምተው ብልግና እቤቱ ሸሽጎ እንደሚኖር ደረስንበት። ሊያሳድገው ከገጠር ያመጣው እቤት አብሮት የሚኖር ዘመድ አለው። ደፍሮት አሁንም እያስገደደው ያባልገዋል። ከዚህ ሰውዬጋ መዋል ከጀመርኩ በኋላ ብዙ ለጆሮ የሚሰቀጥጡ ብልግናዎች ሰምቻለሁኮ ይሄ ግን ወደር የማይገኝለት ነበር። ከብዙ ሙከራ በኋላ ብልግናውን ቀረፅነው!! ይሄ ነው እጄ ላይ የጣለው!!

ለዘመናት የናፈቅኩት ቀን ተከሰተ እና ፊት ለፊት ተገናኘን። ውርደቱ እጄ ላይ እንዳለ ስነግረው ፊቱን ማየት ለቀናት ሲያቅበጠብጠኝ ነበር። እዛው የራቁት ጭፈራ ቤቱ ከአለቃዬ ጋር ሄደን እሱ ሲመጣ እንዲጎበኘው መልዕክት አስቀመጠ። እዚህ ጋር የማይገባኝ አለቃዬ በእኔ በቀል የሚሰክረው ጉዱ ነበር። ልክ መጥቶ እንደተቀመጠ።

«ሜላት እባላለሁ! ወይም ደግሞ አባቴ ባወጣልኝ ስም አምሳል!» አልኩት እና የአባቴን ማንነት ቀዬዬን እና የዛን ቀን ተፈጥሮ የነበረውን ሳላዛንፍ ነገርኩት። ምንም ታክል የፀፀት ስሜት ሽው ባላለው አነጋገር

«ጦርነት ነው የገጠምነው!! ልንስማችሁ አልነበረም የመጣነው!! እንኳን አንቺ ማን እንደሆንሽ አባትሽንም አላስታውሰውም!» ሲለኝ እሱን ለመበቀል የሄድኩት መንገድ ልክ ነው ብዬ አመንኩ። ቪዲዮውን ላኩለት እና ምንም ከማሰቡ በፊት አንድ ቅጂ አለቃዬ ጋር ፣ ሌላ ቅጂ ተቀባብሎ ሌላ ሰው ጋር መኖሩን ነገርኩት!! አንድ ነገር ሊያደርገኝ ቢያስብ መረጃውን ከመውጣት እንደማያግደው ሲያውቅ ተሰበሰበ።

«እሺ ምንድነው የምትፈልጊው? ምን ያህል?» ብሎ ራሴን የሸጥኩበትን በቀሌን በገንዘብ ተመነብኝ

«ገንዘብ አይደለም የምፈልገው!! እንድታገባኝ ነው የምፈልገው!!» ስለው በቁሙ ቃዠ።

«ቀልድ ነው የያዝሽው? ጤነኛ ነሽ?» ሲል አለቃዬ በወልካፋ አማርኛ ቅልብ አድርጎ
«ውነቷን ነው! ቀልድ የለም!» አለው።
«ምን አስበሽ ነው?»

«አታስብ ጠዋት ከእንቅልፋችን አንድ ላይ ተነስተን ፣ ደህና አደርሽ ፣ ደህና አደርክ የምንባባል፣ ቁርስ አንድ ላይ የምንበላ ሰዎች አንሆንም!! አንድ ቤትም አንኖርም! ሚዲያዎች የሚዘግቡት ሰርግ ደግሰህ እንጋባለን!! አብረን አንኖርም እንጂ የትም ቦታ ስትሄድ እጄን እጅህ ውስጥ ሻጥ አድርገህ ትሄዳለህ!! ከዛ የቀረውን እያኖርን እንመካከራለን!! ውሳኔህን እንድታሳውኝ 2 ቀን እሰጥሃለሁ። ያው አማራጭ የምትለውን በሙሉ አይተህ እንደማያዋጣ ትደርስበታለህ!!» ተወራጭቶ ወጣ!! እንደምገምተው አማራጭ ሊሆን ይችላል ብሎ የሚያስበውን ሁሉ አስቧል። ጉዱን ለማንም እንደማያዋየው ግልፅ ነው!!

ቪዲዮው ቢወጣ በመድፈር ወንጀል ብቻ አይደለም የሚከሰሰው በፍቅር ከፍ አድርጎ የሰቀለው ራሱ ህዝብ በድንጋይ ወግሮ እንደሚገድለው ያውቃል። ሰው ገደለ፣ ሀገር ከዳ ፣ ሰረቀ …… ምንም ቢባል ኸረ ምንም ጥፋት ቢሆን ይታለፍለታል። ይሄን ግን አያልፉለትም።
በሁለተኛው ቀን መስማማቱን ላከብኝ!! በአደባባይ ሀገር ጉድ ያሰኘ ሰርግ ደግሶ አገባኝ!! ኪዳን ዩንቨርስቲ ገብቶ ነበር። ማንን እንደማገባ ሲያውቅ ለብዙ ሳምንታት አኩርፎኝ ነበር።
349 viewsAbela, 16:35
Open / Comment
2023-04-18 19:35:44 የመኖር አካፋይ የመሞት ሲሶ መንገድ መሃል........


(ሜሪ ፈለቀ)

ክፍል 28

«ታውቂዋለሽ እንዴ? ምነው?» ሲለኝ
<አዎ አውቀዋለሁ! በአንዲት ሰዓት ውስጥ በፍቅር እና በደስታ ከታቀፍኩበት የቤተሰቤ እቅፍ ውስጥ አስወጥቶ ህይወቴን ያመሳቀለው ሰው ነው!> ማለት ብፈልግም …. እንኳን ከዚህም ከዛም ቃርሜ እና በ6 ወር ከስልጠናው ጋር ተምሬ የምኮላተፍበት አረብኛ ቀርቶ የራሴው አማርኛ እንኳን የህመሜን ያህል ገላጭ ቃል የለውም።

«ክፉ ሰው ነው!» ብዬ ብቻ አለፍኩት። ከዛን በኋላ ግን ለሰዓታት መረጋጋት እስኪያቅተኝ ሰውነቴ ምሬት ተፋ። ፊቴ እስኪያስታውቅበት ድረስ ያለፈው ሁሉ መጠቃት፣ እልህ ፣ ቁጣ ……. እንደአዲስ በደምስሬ ከደሜ ጋር ተዘዋወረ። እቤት ደርሰን መውጫ ሰዓቴ ደርሶ ልወጣ ስል ሌሎቹን ጠባቂዎች አስወጥቶ ብቻዬን ሊያወራኝ እንደሚፈልግ ነገረኝ። ከትዕዛዝ ውጪ ምንም አይነት ነገር አውርተን ስለማናውቅ ግር እያለኝ ተቀመጥኩ።

«ምን አድርጎሽ ነው? የሞት መልዓክ ያየሽኮ ነው የመሰልሽው!» አለኝ

«በልጅነቴ ወላጆቼን ያሳጣኝ ሰው ነው!» አልኩት በደፈናው።

«ጥላቻ ከፍቅር ያይላል። በቀልም ከወሲብ እርካታ በላይ ፍሰሀን ያጎናፅፋል!» አለ ለእኔ ይሁን ለራሱ የተናገረው መለየት በሚቸግር አነጋገር። ቀጠል አድርጎ «ድፍረትሽ ያስታውቃል። ሞትን እስካለመፍራት የሚደፍረው ውስጡ የሚገፋው ጥላቻ እና ያረገዘው በቀል ያለው ሰው ነው። ፍቅር እና ተስፋ ልቡን የሞላው ሰው ፈሪ ነው። ነገን ይፈራል፣ ማጣትን ይፈራል ፣ ሞትን ይፈራል!! በልምድ ብቻ ያገኘሽው ድፍረት እንዳልሆነ ያስታውቃል።» ያለው በትክክል የገባኝ ከብዙ ጊዜ በኋላ በቀልም ጥላቻም ገፍትረው ልቆም ያላቀድኩበት ውሳኔ ላይ ሲያቆሙኝ ነው!! ይሄን አጀንዳ አንስቼ አይደለም ከሱ ጋር ከኪዳን ጋር እንኳን የምጋራው ባላመሆኑ ዝም አልኩ።

«ብዙ ሰው ባያውቅም ሰውየው የቤቱ ባለቤት ነው! ከዚህ በኋላም ተደጋጋሚ ጊዜ ልትገጣጠሚ ስለምትችዪ እንደፕሮፌሽናል ጠባቂ የግል ስሜትሽን ውጠሽ ስርዓት ባለው መልኩ ለመታየት ሞክሪ!!» አለኝ እንደትዕዛዝ ነገር! ከዛ ሁሉ ትኩረት የሰጠሁት <የቤቱ ባለቤት> የሚለውን ነው። ያውቀዋል ማለት ነው!!?? « ምን ልታደርጊው ነው የምታስቢው?» ሲለኝ ለምን ወይም እንዴት ይሄን ጥያቄ እንደጠየቀኝ አላሰብኩትም። «እገድለዋለሁ!» ያልኩት ጮክ ብዬ መሆኑን ከእርሱ እኩል ነው የሰማሁት። የሆነ የፌዝ ነገር (ቀሽም! የሚል ዓይነት ነገር) ሳቅ ብሎ

«አትቸኩዪ! በቀል የሚጣፍጠው ሰውየው ሲሰቃይ የማየት እድል ሲኖርሽ ነው!! ከገደልሽውማ ገላገልሽው! ስንት ዓመታት ተሰቃይተሻል? ስንት ዓመታት ባሰብሽው ቁጥር ህመም ተሰምቶሻል? ለዓመታት የተሰቃየሽው ስቃይ በሱ ቅፅበታዊ ሞት ይካካሳል? ይድናል? ገደልሽው! ከዛስ? እድሜ ልክሽን እስር ቤት ትማቅቂያለሽ!! በህይወት እያለም ደስታሽን ቀምቶሽ በሞቱም ደስታሽን ቀምቶሽ! ይሄ ፍትህ ነው ብለሽ ታስቢያለሽ?» ቃላቶቹን ረጋ ብሎ የሚያወራበት ለዛ ልቡ ቀዝቃዛ እና ክፉ መሆኑን ያሳብቅበታል። ያልገባኝ ለምን እኔን እንደሚያቀሳስረኝ ነው!! ሲያወራው ግን እውነትም በቀል እሱ አፍ ላይ ትጣፍጣለች። በቀልን ሳስብ የማስብ የነበረው መግደልን እንጂ በቀል እንዲህ ተሽሞንሙና እና ረቅቃ አስቤያት አላውቅም!!! ሲያዩትኮ ሰውየው ፍፁም ትሁት እና ሳቂታ፣ ካገኘው ሁሉ ጋር ጨዋታ ወዳድ ነው የሚመስለው። ከሴት ጋር ተያይዞ ካለው ስድነቱ ውጪ እቤቱ እንግዳ ጠፍቶ የማያውቅ ቸር ነው ብዬ ነበርኮ የማስበው!

«ለድፍረቴ ይቅርታ ይደረግልኝና አንተ ብትሆን ምን ታደርጋለህ? ቤተሰብህን ፣ ህይወትህን ፣ ቤትህን ፣ ልጅነትህን የቀማህን ሰው ምን ታደርገዋለህ? በድጋሚ ስለድፍረቴ ይቅርታ!»

« ድክመቱን ማግኘት ነው!! በዛ ድክመቱ ገብተሽ የሚወደውን ነገር አንድ በአንድ መንጠቅ! ልክ በቁሙ እያለ መጀመሪያ ተራ በተራ ጣቶቹን፣ ቁስሉ ደርቆ ተሻለኝ ሲል ክንዱን ፣ ቆየት ብለሽ ሙሉ እጁን ፣ ከዛ የሌላኛው እጁን ጣቶች ፣ ክንድ ፣ ሙሉ እጅ ….. እያደረግሽ አካሉን እንደመክተፍ!! ግደዪኝ ብሎ እስኪለምንሽ ወይም ራሱን ለመግደል እስኪወስን ያለውን ማሳጣት!» ሲል የተናገረውን እያንዳንዷን ድርጊት ተግብሮት እንደሚያውቅ ነው። በትክክል እንዲገባኝ የፈለገ ይመስል ወሬውን በምልክት አጅቦ ነው አስረግጦ ያስረዳኝ። አወራሩ የጭካኔ ጥግ የሆነ ወሬ እያወራ ሳይሆን የልደት ኬክ ስለመቁረስ ዓይነት ያለ ጨዋታ እንደሚያወራ ቃላቶቹን በፍቅር ነው ምላሱ ላይ የሚያሽሞነሙናቸው። ለሆነ ቅፅበት አጠገቡ መሆኔን ሁሉ ፈራሁት!!! መልሼ ፍርሃቴ ራሴኑ አሳቀኝ እንጂ! እኔ ከእርሱ በምን ተሽዬ ነው? በተናገረው ነገር ተስቤ በቀልን እሱ በገለፀው መንገድ ጭንቅላቴ ውስጥ ላጣጥመው እኮ ሞክሬያለሁ።

«እርዳታዬን ከፈለግሽ መጠየቅ ብቻ ነው የሚጠበቅብሽ!! ስለሰውዬው ማወቅ የምትፈልጊው ነገር ካለ የሀገሩ ዜጋ አለመሆኔን አትዪ ሁሉም ቦታ አይን አለኝ፣ የሚያስፈልግሽ ገንዘብ ወይም ፋሲሊቲ ምንም ቢሆን !!» አለኝ።

«እውነትህን ነው? ለምን ልትረዳኝ ፈለግክ?» ጥርጣሬም መገረምም ጨረፍ አድርጎኝ የጠየቅኩት ጥያቄ ነበር።

«ፍትህ ሲዛባ ደስ አይለኝም!! የተፃፉ ህጎች ለሁሉም ሰው እኩል ፍትህ አይሰጡም!! ጉልበተኞችን ያሾልካሉ።» ሲለኝ የከተማው ብልጣብልጥነት ብዙም ያልዘለቀው ልቤ አመነው። ወይም ድክመቴን አግኝቶብኛል። አመስግኜው ስለሰውየው ሊጠቅመኝ የሚችል መረጃ ምንም ቢሆን እርዳታውን እንደምፈልግ ነግሬው አቋራጭ መንገድ በማግኘቴ ተደስቼ ሳልጨርስ በምትኩ ከእኔ የሚፈልገው ነገር መኖሩን ነገረኝ። በጅልነቴ ብግን ያልኩት ሰውየው እውነተኛ ማነነቱን በግልፅ አሳይቶኝ እንኳን የሚቀጥለው ጥያቄ ከደግ ልብ የመነጨ እንደሚሆን መጠበቄ!!

ልክ ልከኛ ነገር ያወራ ይመስል፣ ልክ ከእዛጋ ያን ወረቀት አቀብዪኝ እንደማለት ነገር ቀለል አድርጎ …… አንድ ከየትኛው አረብ ሀገር እንደሆነ የማላውቀው አዘውትሮ እሱጋ የሚመጣ ሰውዬ ስለሚቋምጥልኝ ከእርሱ ጋር በመተኛት ውለታውን እንድከፍለው ነገረኝ። በተጨማሪ ሰውየው የምፈልገውን የሚያደርግልኝ ሀብታም መሆኑን አከለበት። ለሆነ ደቂቃ ምንም የምለው ቃል ራሱ ቸግሮኝ ዝም ብዬ እንደሆነ መዓት ሳየው ቆየሁ። ትንሽ ቆይቼ ግን ከአፌ ከወጣ በኋላ የፀፀተኝን ወሬ አወራሁ!!
«አላደርገውም!! ወንድ አልወድም ከወንድ ጋር መተኛትም አልወድም!! ሴት መሆኔን እርሳው!! ህፃን ሆኜ ነው እናቴን አይኔ ስር ሲደፍሯት ያየሁት!! እንደማንኛዋም ወጣት ሴት ያለ ስሜት አይደለም ያለኝ!! ሳስበው ራሱ ትዝ የምትለኝ እናቴ ናት!! ይዘገንነኛል። ምንም ነገር ይቀራል እንጂ አላደርገውም!!» ያልኩት እንዲያዝንልኝ ነው? ፣ እንዲረዳኝ ነው? ፣ ልዋጭ ሳይፈልግ ሙሉሰውን የማጠምድበት መላ እንዲዘይድልኝ ነው? ምን አስቤ እንደሆነ አላውቅም!! ከዚህ ሁሉ ውስጥ እሱ በድፍኑ የተሰማው ሌላ ነው።

«ጭራሽ ወንድ አላውቅም እያልሽ ነው?» ከማለቱ ዓይኖቹ ሰውነቴ ላይ በመቀላወጥ ተርመሰመሱ። በጣም እየቀፈፈኝ ተነስቼ እየቆምኩ

«አዎን ምነው?» ስለው ምንም ድንቅፍ ሳይለው ከዛኛው ሰውዬ ጋር የመተኛቱን ሀሳብ እንደቀየረ (ልክ እኔ የተስማማሁ ይመስል) እና በምትኩ ከእርሱ ጋር እንድተኛና ከፈለግኩ የሙሉሰውን ጭንቅላት ከሰውነቱ ቆርጦ እንደሚያመጣልኝ ነገረኝ። ማለት በቃ በምንም የማንግባባ የተለያየ ቋንቋ የምናወራ ሰዎች መሆናችን ሲገባኝ ተነስቼ ወደቤቴ ሄድኩ። ያወራሁትን አልሰማም?
448 viewsAbela, 16:35
Open / Comment
2023-04-18 15:35:28 ለባሉ
_
ፊዬሪ ነሽ ጮራ
የልቤ አስመራ?

የነፍሴ  ማክተሚያ
የዘመን ማደሪያ

የክታብ ጦርነት የባሉ ማዕረግ
ለጥቁርም ብራ'ነት የኔ የዘር ሀረግ
የግርማ ልጅ ሰዊ የሱዋ የሴት ደግ

ፊዬሪዋ ግዕዝ አስመራነት !
አምሳለ ደግነት አምሳለ እንባነት፣

---
ግዕዝ ሙላት

መታሰቢያነቱ

ለደራሲ በዓሉ ግርማ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.0K viewsAbela, 12:35
Open / Comment
2023-04-18 14:09:02 . ግን ለምን?

ከቤተስኪያን ግቢ ፊቷን ተከናንባ
ፀጥ ካለው ግቢ አጎንብሳ ገብታ
ከበሩ ስር ስትደርስ ዝቅ ብላ ተደፍታ
'ምስጋና ለአምላኬ ሁሉን ለምታቀው
የታመመ ባሌን ከህመም ላዳንከው
የወለድኩት ልጄን ብሩክ ላደረከው
አመሠግናለሁ
ነገም አለኝታህን እጠባበቃለሁ

ደህና አርግልኝ ባሌን ሰላም ወጥቶ ይግባ
አሳድገው ልጄን ከፍ ይበል ያባባ
(ጠብቃት ሀገሬን ይከበር ድንበሯ)
የታረዘን አስብ ሸክፍ የደሀ እንባ
ይፅደቅ የሞተ ሰው ይዳን የታመመ
ይርካ ውሀ የጠማው ይጥገብ የተራበ'
ብላ ትነሳለች
ከብብቷ ጉያ
ካለች ጥቁር ቦርሳ
...ሳንቲም ታወጣለች
አንዷን ፍሬ መዛ ሙዳይ ታገባለች
ፀጥ ካለው ግቢ አፀድ ከበዛበት
እልፍአእላፍ ሰላምን ከሚጎነጩበት
ወጥታ ትሄዳለች
ገንዘብ ስጠች አትል ወይ ወርቅ አልጠየቀች
ማጌጥ አላማራት ውበት አለመነች
::::::::::::::::::::::::::://:::::::::::::::::::::::::::
አጉል ቀኑ ቀድሞት ከዘመን ተኳርፎ
የዛች የምስኪን ባል ከዕድሜው ላይ ፎርፎ
ፀጥታ በራቀው ጩኸት በበዛበት
ዝምታ ቅጥ ባጣ ሁካታ ባለበት
በመጠጥ ዱቅዱቅታ በዘፈን አታሞ
በሽቶ በጠረን በእልፍ ሴት ተከቦ
ከጨለማው መሀል በታየች ብልጭታ
ከሰይጣን ቁጭ ብሎ ትዝ ቢለው ጌታ
ይሄንን ለመነ...
'ያቺ አሮጊት ሚስቴን ድፋልኝ ልቅበራት
ያገሩን ቆንጆ ሴት እንዳሻኝ ልግመጣት'
የምን ጥያቄ ነው? ምን ይሉት ልመና
ምን አይነት ፍላጎት?ምን አይነት ፅሞና?
ሰላም እንዲያረገው ደስ ብሏት ሳትጨርስ
ስለት አስገብታ
አልፈልግም ትሂድ ግደላት ውሰዳት
የሚሉት ውትወታ?
::::::::::::::::::::::::::://:::::::::::::::::::::::::
የዛች የምስኪን ሴት የአብራኳ ክፋይ
የአምላክ ማመስገኛ የአካሏ ምሳይ
ቃል በደንብ ሳይፈታ ገና ባ'ፍላነቱ
ያ ችኩል ያ ፈጣን ያ ልጇ ወጣቱ
ከሀያ አመት በላይ አብራው ለኖረችው
አዝላ ተንከባክባ ጡቷን ላጠባችው
አንዲት መስመር ሳይፅፍ...

በአንድ ቀን እይታ ድንገት ለከነፈ
5 ገፅ በሙሉ አንድ ደብዳቤ ፃፈ
'እኔ ያንቺ ብቻ ነኝ' ብሎ ለፈለፈ
ሌላውን ረስቶ ያቺን ልጅ አመነ
'እሷን ብቻ ስጠኝ' እያለ ለመነ
:::::::::::::::::::::::::://::::::::::::::::::::::::::
አይ የዚች አለም ጉድ - ግራ አይሉት ወይም ቀኝ
ከላይ ቢሉት የለ - ከታች ቢሉ አይገኝ
አሁን ያቺ ጎጆ ያቺ ሶስት ጉልቻ
በማን ነው የቆመች በማንስ ትክሻ?

የማን ነው ትክክል የትኛው ነው ስህተት?
የቱ ነው እውነቱ የማንስ ነው ሀሰት?
ማን ተጠራጠረ ማንስ ነው ባለእምነት?

እሷ ስለልጇ ለባሏ ላ'ገሯ
ታርዞ ላየችው ላለፈ በበሯ
ለሁሉ ስትለምን
እሷን ማን ዞሮ አየ - ግን ለምን ግን ለምን?


በአቤኒ የተፃፈ


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.2K viewsAbela, 11:09
Open / Comment