Get Mystery Box with random crypto!

🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺

Logo of telegram channel nesiha_ouserya — 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺
Logo of telegram channel nesiha_ouserya — 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺
Channel address: @nesiha_ouserya
Categories: Education
Language: English
Country: Ethiopia
Subscribers: 2.48K
Description from channel

ለስኬታማ ቤተሰብ - نحو الأسرة الناجحة
ቤታችንን ኢሰላማዊ በማድረግ ትዉልድን እናድን!
ስለ ቻናላችን ያሎትን ሀሳብና አስተያየት
በ @nesiha_ouserya_Bot ይላኩልን!
እናመሰግናለን!
@nesiha_ouserya

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages 18

2021-01-12 22:22:21 ሒጃብን እንዴት እንረዳው? ❷

•┈•⊰✿ ✿⊱•┈•

እህቴ_ሆይ! ሂጃብ ተግባሩም እንደ ስሙ ነው፡፡ በአላህ ፈቃድ ከተለያዩ የማህበራዊ ህይወት ፈተናዎች በተለይም ከፆታዊ ትንኮሳ የሚጠብቅ ጋሻ ነው፡፡

በእስልምና ሴት ልጅ የሰው ልጅ ሰው እንዲሆን በመልካም ኢስላማዊ ስነ-ምግባሮች የሚታነፅበት ማዕከል ነች፡፡ የዚህ የፅድቅ እና ወርቃማ እሴቶች ማዕከል አጥሩ ሂጃብ ነው፡፡

ኢስላምን ማጥቃት የሚፈልጉ አካላትም ቀድመው ሂጃብ ላይ የሚዘምቱት ለዚሁ ነው፡፡ የእንስቷ ጥንካሬ የሙስሊሞችን ጥንካሬና ስኬት ከሚወስኑት ነገሮች አንዱ ነው።

●#እህቴ_ሆይ! ሂጃብ ሙስሊም ነኝ ላሉ ሁሉ ክብርና ኩራትን የሚቸር በፍቅር እና በሀሴት እንባ የሚለበስ ትምህርት፣ ስራ፣ ገንዘብ፣ ህይወት መስዕዋት የተደረገለት እና የሚደረግለት ነው፡፡

ሂጃብ ስጋን የሚሸፍን ነገር ግን መንፈስን የሚያፋፋ፣ የመንፈስ ምግብ ነው፡፡ የልብን ወደ ጌታዋ መንጠልጠል የሚያቃና ድልድይ ነው፡፡

#እህቴ_ሆይ! ሂጃብ ለማህበራዊ ደህንነት ዋስትና የሚሰጥ የሰሃቢያት ቅን ፈለግ ነው፡፡

በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከሚገኝ የፍጡራን ባርነት ነፃ የሚያወጣ የነፃነት ቀንዲል ነው።
•┈•⊰✿ ✿⊱•┈•

#ሒጃብ
2.6K viewsedited  19:22
Open / Comment
2021-01-11 12:30:53 ልጆችን ለማነፅ ቀላል ከሆኑ መንገዶች፦
•┈┈••••○○❁ ❁○○••••┈┈•

➏ ልጃቸው ፊት የሚስማሙ፣ የሚግባቡ፣  የማይጨቃጨቁና የማይጯጯሁ አባትና እናት ልጆቻቸውን ቤታቸውን እንዲወዱ፣ እርስ በእርስ የሚግባቡ፣ የሚዋደዱና የሚቀራረቡ እንዲሆኑ ያደርጓቸዋል።

➐ አባት ዝምድና የሚቀጥል ለነሱም በጎ የሚውልላቸውና የሚወዳቸው ከሆነ ልጆቹ ዝምድናን መቀጠልንና ለነሱ በጎ መዋልን ይማራሉ።

➑  አንዳንድ ነጥቦች ላይ የልጆቹንና የባለቤቱን ሃሳብ የሚቀበል ከእነርሱ ጋር የሚወያይና ራዕያቸውን የሚያከብር አባት ልጆቹን መመካከርንና አዎንታዊ (ሀሳብ ተቀባይ)
መሆንን ያስተምራቸዋል።

➒ ከልጆቹ ጋር እውነተኛ የሆነ አባት እውነትን ያስተምራቸዋል። እንዲሁም የገባውን ቃል የሚፈፅምላቸው ከሆነ ለሰዎች የገቡትን ቃል መሙላትን ያስተምራቸዋል።

➓ንጽህናንና ስርዓትን የሚጠብቁ በፕሮግራም የሚመሩ አባትና እናት ልጆቻቸውን ስርዓት ያለው ኑሮ እንዲኖሩ ያደርጓቸዋል።

➬ማጠቃለያው በልጆች አስተዳደግ ላይ ውጤታማ ለመሆን፦

እናንተ መስራት እየቻላችሁ የማትሰሩትን ነገር ልጃችሁ እንዲሰራ አትፈልጉ።

አንድን ክልክል የሆነን ነገር እናንተ ፊታቸው የምትሰሩት ሆኖ ሳለ አትከልክሏቸው።


መልካም አርአያ በመሆን ልጅን ማሳደግ ቀላሉ የተርቢያ መንገድ ነው።
•┈┈••••○○❁ ❁○○••••┈┈•

አላህ ይወፍቀን።

#ተርቢያ
@nesiha_ouserya
2.2K views09:30
Open / Comment