Get Mystery Box with random crypto!

🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺

Logo of telegram channel nesiha_ouserya — 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺
Logo of telegram channel nesiha_ouserya — 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺
Channel address: @nesiha_ouserya
Categories: Education
Language: English
Country: Ethiopia
Subscribers: 2.48K
Description from channel

ለስኬታማ ቤተሰብ - نحو الأسرة الناجحة
ቤታችንን ኢሰላማዊ በማድረግ ትዉልድን እናድን!
ስለ ቻናላችን ያሎትን ሀሳብና አስተያየት
በ @nesiha_ouserya_Bot ይላኩልን!
እናመሰግናለን!
@nesiha_ouserya

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages 2

2022-08-14 11:08:27
ነሲሓ የወጣት ወንዶች ልዩ ኮንፈረንስ


ነሲሓ ወጣቶችና ታዳጊዎችን አስመልክቶ በአይነቱ ልዩ የክረምት ኮንፈረንስ አሰናድቷል


በእለቱ የሚሰናዱ ፕሮግራሞች

☞ዐቂዳና ቁሳዊነት በኡስታዝ ሙሐመድ ሀሰን ማሜ
☞መዝናናትና መደሰት በሸሪዓ ሚዛን ዐብዱረዛቅ ፈረጃ

በሌሎች ዳዒዎችና ባለተሰጥኦ ወጣቶች ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ይቀርባሉ።

☞ አስተማሪ መጣጥፍ በዶክመንተሪ መልኩ

☞ "የነብዩ ዩሱፍ ዐለይሂ ሰላም ድንቅ ፅናት" ልዩ በሆነ አቀራረብ


ፒያሳ በሚገኘው በኸሊፋ አዳራሽ

ነሓሴ 15 2014

መግቢያ በነፃ

ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ

የፕሮግራሙ መግቢያ ላይ የተለያዩ ጠቃሚ መፅሀፍት፣ ጣፋጭ ምግቦች መጠጦች በተመጣጣኝ ዋጋ ይቀርባሉ

ነሲሓ ቲቪ...
ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም!!

@nesihatv
846 views08:08
Open / Comment
2022-08-06 10:50:07
ነሲሓ የዒልም ቅፍለት ኮርስ

ከሰኞ ነሐሴ 02/2014 ዓ.ል ጀምሮ ለተከታታይ 4 ሳምንት የሚቆይ መሰረታዊ የዒልም ኮርስ

ዘወትር ከሰኞ- ሀሙስ ከጠዋት 02፡30- 6፡30

አየር ጤና በሚገኘው ዒባዱረህማን መስጂድ
የሚሰጡ ኮርሶች፡-

መንዙመቱል ሃኢያ(ዓቂዳ ) እና ተስሪፉል ዒዝይ(ሰርፍ)
በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ

ሙተሚመቱል አል‘ ኣጅሩሚያ (ነህው)
በሸይኽ ሙሐመድ ኢድሪስ


ነሲሓ ቲቪ...
ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም!!

@nesihatv
832 views07:50
Open / Comment
2022-08-03 12:41:32 ልዩ የዳዕዋ መድረክ ለእህቶች ብቻ!

በወርሀ ዙልሒጃ አንድ ብሎ የጀመረው ልዩ የዳዕዋ መድረካችን እንዳማረበት ሊቀጥል በቀጠሯቸን መሰረት እነሆ ቁጥር ሁለት ደረሰ።

ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ተሰናድተው እናንተን እየጠበቁ ነው።

በእለቱ የሚዳሰሱ ርዕሶች

ዐሹራ
እምነታችን
ሴቶችና ኢስላም

በተጨማሪም

መነባንቦች ይቀርባሉ

እሁድ ነሀሴ 1፣ 2014
ከጠዋቱ 3:00 - 6:30

አድራሻ: ፒያሳ የሚገኘው ኸሊፋ ህንጻ አዳራሽ

በራስ ድግስ አይቀርም! አይረፈድም!

መልእክቱን ለእህቶች በማድረስ የአጅሩ ተቋዳሽ እንሁን!

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር

@darulhadis18
1.4K views09:41
Open / Comment
2022-07-25 12:12:33 የሂዳያ ስንቅ በነሲሓ

ወቅቱ ክረምትና የረፍት ጊዜ እንደመሆኑ መጠን

ወላጆች ልጆቼ ጊዜያቸውን በምን ያሳልፉ ይሆን? የዲን ትምህርት የት ላስተምራቸው? ብለው የሚጨነቁበት ነው።

ልጆችም በፊናቸው የትና በምን እንደሚያሳልፉ የሚብሰለሰሉበት ወቅት ነው!

እነሆ! ይህን ጭንቀታችሁን የምታቃልሉበት መፍትሄ ይዘን ከተፍ ብለናል!

ክረምቱን የዲን ዕውቀት ስንቅ የምትሰነቁበት ልዩ ገፀ በረከት!

የሂዳያ ስንቅ በነሲሓ!

በአካል ሄደው መማር ለማይችሉ ዕድሜያቸው ከ8 -13 ላሉ ታዳጊዎች የተዘጋጀ አዲስ መጽሐፍ አዲስ የክረምት ኮርሰ በነሲሓ ቲቪ!

ይህ ኮርስ ለታዳጊዎች እንዲሆን ታስቦ ቀለ ባለና ልዩ በሆነ መልኩ የተዘጋጀ ሲሆን፤ ለኮርሱ መስጫ አጋዥ መጽሐፍም ተሰናድቷል።

መጽሐፉ በውስጡ የዐቂዳ፣ ፊቅህ፣ ሲራ እና አደብ ትምህርቶችን ከመመዘኛ ጥያቄዎችን ጋር አካቶ ይዟል።

የመጽሐፉ ማብራሪያ ፕሮግራም በነሲሓ ቴሌቪዥን ይቀርባል።

መጽሐፉን፦

ቤተል ነሲሓ ቲቪ ቢሮ እና

በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ቅርንጫፍ ጣቢያዎች ማግኘት ትችላላችሁ!

ለበለጠ መረጃ ስልክ፦
09 30 484284

አዘጋጅ፦ ሂዳያ ተርቢያ ከነሲሓ ቲቪ ጋር በመተባበር!

ምርጥ ትውልድ I #ክረምት #ኮርስ I

I #ሂዳያ #Hidaya #ተርቢያ #Terbiya I

https://t.me/HidayaTerbiya
1.4K views09:12
Open / Comment
2022-07-18 21:42:14 የኪታብ ቂርዓት ይፈልጋሉ?!

እምነት የሁለት ዓለም አንጡራ ሀብት ነው!

ትክክለኛ ኢስላማዊ እምነትን ጠብቆ ማቆየትና ለቀጣይ ትውልድ ማሻገር ደግሞ የትውልድ አማና ነው!

ኑ! ከመጤና ሰርጎ ገብ አስተሳሰቦች ራሳችንንና ማህበረሰባችንን እናድን!

በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንዲሉ

አንድም መንገድ የሳቱ ጠርዝ የረገጡ ቡድኖችን አቋም አውቀው ይጠነቀቃሉ፤

አንድም የትክክለኛውን ጎዳና ጠንቅቀው አውቀው በአላህ ፈቃድ ፀንተው ይጓዛሉ!

የኪታቡ ስም: ዶላለቱል አሕባሽ

ትምህርቱ የሚሰጠው: ከሐምሌ 18 ጀምሮ

ቀን: ከሰኞ እስከ ሐሙስ

ሰዓት: ከ7:30 - 9:00

ትምህርቱ የሚሰጥበት ቦታ:-
አባ ጅፋር መስጂድ ጎን (የቀድሞ መርየም መድረሳ)

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
@darulhadis18
1.3K views18:42
Open / Comment
2022-07-02 12:36:29 የሁለት ዓለም ስንቅ! በአንድ አገልግል!

ልዩ የመድረክ ፕሮግራም!

ለእህቶች ብቻ!

10ሩን ቀናት እንዴት ለማሳለፍ አቅደሻል?

የትኞቹን?

ከተከበሩት ወራት መካከል አንዱ የሐጅ ወር የሆነው ዙልሒጃ አይደል?

አዎ!

እና ታዲያ! አላህ ዘንድ እጅግ የተወደዱት ደግሞ አስሩ የዙልሒጃ ቀናት አይደሉም?

እንዴታ!

ኧረ! እንደዉም ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው እነዚሁ አስር ቀናት ናቸው።

አሁን ገባኝ!

ታዲያ ከገባሽ እነዚህን አስርት ቀናት እንዴት በአግባቡ ተጠቅመሽ ማሳለፍ እንዳለብሽ ማወቅ አትፈልጊም?

ምን ጥያቄ አለው?

እንግዲያውስ መጪው እሁድ ቀጠሮሽ ከእኛ ጋ ይሁን!

በተጨማሪም

እምነትሽ መዳኛሽን ስብዕናሽን ዘውድሽን የሚዳሰሱ ርዕሶች ።

እሁድ ሰኔ 26፣ 2014
ከጠዋቱ 3:00 - 6:30

አድራሻ: ፒያሳ የሚገኘው ኸሊፋ ህንጻ አዳራሽ

ለሁለቱም ዓለም የሚጠቅምሽን ስንቅ ይዘሽ ትመለሻለሽ!

ብታረፍጂ ይገርመኛል!

መልእክቱን ለእህቶች በማድረስ የአጅሩ ተቋዳሽ እንሁን!

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር

@darulhadis18
1.8K views09:36
Open / Comment
2022-06-29 22:00:20 የዙልሒጃ ወር ነገ ሐሙስ ሰኔ 23/2014 / June 30/2022
ብሎ ይጀምራል

ጃቢር ኢብኑ ዓብዲላህ ባስተላለፉት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል «ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው፤ አስርቱ ቀናት ናቸው። ማለትም አስሩ የዙልሂጃ ቀናት» አልባኒ ሰሂሁል ጃሚዕ 1133 ላይ አስፍረውታል

ከነገ ጀምሮ ያሉትን ተከታታይ ቀናት በኢባዳ እናሳልፋቸው!
1.6K views19:00
Open / Comment
2022-06-28 21:20:31 አስደሳች ዜና ለኢስላም ተስፋዎች!

ለወንድ ታዳጊዎችና ወጣቶች የተዘጋጀ የክረምት ኮርስ!

የሚሰጡ ኮርሶች

ዐቂዳ
ፊቅህ
ተርቢያ እና
ቁርኣን

ዕድሜ ከ10 ዓመት በላይ

የት/ት ሰዐት ከ3:00-6:30

የምዝገባ ጊዜ፦ ከሰኔ 21 እስከ 28

የምዝገባ ቦታ፦18 አደባባይ ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር

ኮርሱ የሚሰጥበት ቦታ

1.ፍሊ ዶሮ አል-አፊያ ት/ቤት
2. ቤተል

ወላጆች ልጆቻችሁን በመላክና በማስመዝገብ ኀላፊነታችሁን ተወጡ!

ለበለጠ መረጃ፦
0912023190/09 65 91 95 23

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
@darulhadis18
1.4K views18:20
Open / Comment
2022-06-28 20:42:56 የነገ የኢስላም ተስፋዎች ! በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ዳሩል ሀዲስ ለሴት ታዳጊዎችና ወጣቶች የተዘጋጀ ልዩ የክረምት ኮርስ! ይህ ኮርስ በአላህ ፈቃድ ከዕውቀቶች ሁሉ ታላቅ ስለሆነው ዕውቀት የሚማሩበት! ኢስላማዊ ስነ ምግባርና አደቦችን የሚቀስሙበት! ኢስላም ለሴቶች የሰጠውን ክብር የሚያውቁበት! በየደረጃው የሚሰጡ ኮርሶች ፦ ዐቂዳ ፊቅህ ተርቢያ (ሴቶችን…
1.2K views17:42
Open / Comment
2022-06-28 17:42:34 የነገ የኢስላም ተስፋዎች !

በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ዳሩል ሀዲስ ለሴት ታዳጊዎችና ወጣቶች የተዘጋጀ ልዩ የክረምት ኮርስ!

ይህ ኮርስ በአላህ ፈቃድ

ከዕውቀቶች ሁሉ ታላቅ ስለሆነው ዕውቀት የሚማሩበት!

ኢስላማዊ ስነ ምግባርና አደቦችን የሚቀስሙበት!

ኢስላም ለሴቶች የሰጠውን ክብር የሚያውቁበት!

በየደረጃው የሚሰጡ ኮርሶች ፦

ዐቂዳ
ፊቅህ
ተርቢያ (ሴቶችን የተመለከተ)
ሀዲስ
ተጅዊድ

ለጀማሪዎች የቁርኣን ንባብ እና መሠረታዊ ኢስላማዊ ትምህርቶች ይሰጣል።

ኮርሱን መሳተፍ የሚችሉት ዕድሜያቸው ከ 12 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶች ናቸው።

ከሐምሌ 11-ነሐሴ 30
ጠዋት ከ3:00-6:30
የምዝገባ ጊዜ፦ ከሰኔ 23-30

ኮርሱ እንደተለመደው በአራቱም ጣቢያዎች ይሰጣል።

ለበለጠ መረጃ:-

1.18 ማዞሪያ (አባጅፋር)
0967671891/0904366666

2.ቤተል
0911105653/0911375952

3. ስልጤ ሰፈር
0929197819/0912045679

4. ፉሪ
091377547/0911479151

ወላጆች ልጆቻችሁን በማስመዝገብ ኀላፊነታችሁን ተወጡ!

መልዕክቱን ሼር እናድርገው።

@darulhadis18
1.2K views14:42
Open / Comment