Get Mystery Box with random crypto!

🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺

Logo of telegram channel nesiha_ouserya — 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺
Logo of telegram channel nesiha_ouserya — 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺
Channel address: @nesiha_ouserya
Categories: Education
Language: English
Country: Ethiopia
Subscribers: 2.48K
Description from channel

ለስኬታማ ቤተሰብ - نحو الأسرة الناجحة
ቤታችንን ኢሰላማዊ በማድረግ ትዉልድን እናድን!
ስለ ቻናላችን ያሎትን ሀሳብና አስተያየት
በ @nesiha_ouserya_Bot ይላኩልን!
እናመሰግናለን!
@nesiha_ouserya

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages 7

2021-08-26 11:27:46አላህ መልካም ለሻለት ሰው ዲኑን ያስገነዝበዋል
ታላቅ የምስራች ለኢስላማዊ እውቀት ፈላጊ ሴቶች በሙሉ

በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ዳሩል ሀዲስ የሸሪዓ ትምህርቶችና የዐረብኛ ቋንቋ መማሪያ ኢንስቲትዩት እድሜያቸው ከ15 አመት በላይ ለሆነ ሴት ተማሪዎች የዲን ትምህርት ለመጀመር ዝግጅቱን አጠናቆ ምዝገባ መጀመሩን ሲገልፅ በታላቅ ደስታ ነው

የትምህርት ቀናት እና ሰአት አማራጮች

በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ

ከሰኞ-ጁሙኣ=ቁርአንና ኪታብ

በሳምንት 3 ቀን=ቁርአንና ኪታብ

ቅዳሜ ብቻ=የኪታብ ቂረኣ

በከሰአቱ ክፍለ ጊዜ

ከሰኞ- ጁምኣ =ቁርአንና ኪታብ

ከሰኞ- ሀሙስ =የኪታብ ቂረኣ

ቅዳሜ= የኪታብ ቂረኣ

ከአስር በኃላ

ከሰኞ- ጁምኣ=ቁርአንና ኪታብ

የሚሰጡት ትምህርቶች ቁርአን ያልቀሩ እና ጀማሪ የኪታብ ተማሪዎችንም የሚያካትት ይሆናል።

መመዝገቢያ 300ብር

የምዝገባ ጊዜ፦ ከጁምኣ ነሐሴ 21/2013 እስከ ጿግሜ 3/2013

የምዝገባ ሰአት
ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከ3:00_10:00
ጁምኣ ከሰአት አይኖርም።

የምዝገባ ቦታ፦ ከጦር ሀይሎች ከፍ ብሎ የሚገኘው አባጅፋር መስጂድ ከሴቶች መግቢያ በር ፊት ለፊት
(የቀድሞው መርየም መድረሳ)

ለበለጠ መረጃ፦
በስልክ ቁጥር 0904 36 66 66
ወይም 0967 67 18 91 ይደውሉ

ማሳሰቢያ፦
ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ ቀድመው ይመዝገቡ!!

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
@darulhadis18
364 views08:27
Open / Comment
2021-08-17 20:38:55 ዐሹራእ !

የሙሐረም ወር 10ኛው ቀን እለተ ዐሹራእ በሚል ይታወቃል።

ይህ እለት አላህ ነብዩላህ ሙሣንና ተከታይ አማኞችን በመርዳት ትምክህተኛውን ፊርዓውንና ጋሻጃግሬዎቹን ድባቅ የመታበት ቀን ነው።

ታዲያ ይህን እለት መልዕክተኛው ልዩ ትኩረት ይሰጡት ነበር። ለሙሣ ካላቸው ቅርበት አኳያና አላህንም ለማመስገን ፆመውታል እንዲፆምም አመላክተዋል። ነብዩላህ ሙሣም ይፆሙት ነበር።
" فصامه موسى" زاد مسلم في روايته: «شكراً لله تعالى فنحن نصومه»
" ሙሣ አላህን ለማመስገን ፆመውታል ፤ እኛም እንፆመዋለን"
ባልደረቦቻቸውንም አበክረው አነሳስተዋል።
"أنتم أحق بموسى منهم فصوموا"
" ከአይሁዶች ይልቅ እናንተ ለሙሣ የቀረባችሁ ( የተገባችሁ ) በመሆናችሁ ይህን ቀን ፁሙት " ብለዋል።

ዐሹራን በመፆም የሚገኘውንም ታላቅ ምንዳ አውስተዋል።
وقال النبي صلى الله عليه وسلم: «صيام يوم عاشوراء، إني أحتسب على الله أن يكفر السنة التي قبله» (رواه مسلم)
" እለተ ዐሹራእን መፃም አላህ ዘንድ ያለፈውን አንድ ዓመት( ትናንሽ ) ወንጀሎች ያስምራል ብዬ አስባለሁ " በማለት ገልፀዋል።
ታዲያ ይህን እለት አይሁዶችና ነሳራዎችም ክብር ይቸሩት ስለነበር የአላህ መልዕክተኛ በቀጣይ ከ10 ኛው ቀን በተጨማሪ 9ኛውንም ቀን ለመፆም እንዳሰቡ ተናግረዋል።
فقال رسول الله صلى الله عليه وسلم: «فإذا كان العام المقبل إن شاء الله صمنا اليوم التاسع»، قال: فلم يأتِ العام المقبل حتى توفي رسول الله صلى الله عليه وسلم. (رواه مسلم )
" የአላህ ፈቃድ ከሆነ በመጪው ዓመት ዘጠነኛውንም ቀን እንፆማለን " ይሁንና የቀጣዩ ዓመት ግዜ ሳይደርስ የአላህ መልዕክተኛ ወደ ኣኼራ ሄደዋል።
432 views17:38
Open / Comment
2021-08-17 20:35:56 የሙሐረም ወር ክቡር ከሆኑ አራት ወራት መሃከል የሚካተት ነው።

በሂጅራ የዘመን ቀመርም የዓመቱ የመጀመሪያ ወር ነው።

እንዲሁም የአላህ መልዕክተኛ በሐዲሳቸው እንደገለፁት የሙሐረም ወር ቀናት ፆም ከረመዳን ለጥቆ የላቀ ደረጃ እንዳላቸው ነው።
عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: «أفضل الصّيام بعد رمضان شهرُ الله المحرم» (رواه مسلم)
" ከረመዳን ቀጥሎ በላጩ ፆም የአላህ ወር የሆነው የሙሐረም ፆም ነው "

አስተውሉ አላህ የዚህን ወር ትሩፋት ፣ ክብርና ደረጃ ሲያልቅ ወደራሱ በማስጠጋት " *የአላህ ወር* " በሚል እንዲጠቀስ አድርጓል።
405 views17:35
Open / Comment
2021-08-17 20:32:41
404 views17:32
Open / Comment
2021-08-10 20:26:08 በተከበሩት ወራቶች ነብሳችንን ከመበደል እንጠንቀቅ!! 

ምስጋና ለአለማት ጌታ ለአላህ የተገባ ነው። የአላህ ሰላምና እዝነት በተከበሩት መልእክተኛ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ ሁሉ ይሁን። በመቀጠል፤

አላህ እንዲህ ይላል፤ 

[إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِنْدَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْراً فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالأَرْضَ مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ ذَلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ فَلا تَظْلِمُوا فِيهِنَّ أَنْفُسَكُمْ] التوبة/36 

« አላህ ዘንድ የወሮች ቁጥር፤  በአላህ መጽሐፍ ዉስጥ (በጥብቁ ሰሌዳ ለውሀልማህፉዝ) ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን (የሰየመው) ዐሥራ ሁለት ወር ነው፤ ከነሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው፤ ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው፤ በነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ፤» አልተውባህ 36

عَنْ أَبِي بَكْرَةَ رضي الله عنه عَنْ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ : ( السَّنَةُ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ , ثَلاثٌ مُتَوَالِيَاتٌ : ذُو الْقَعْدَةِ وَذُو الْحِجَّةِ وَالْمُحَرَّمُ , وَرَجَبُ مُضَرَ الَّذِي بَيْنَ جُمَادَى وَشَعْبَانَ) رواه البخاري ومسلم.

ከአቢ በክራህ በተዘገበ ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፤ «አመት አስራ ሁለት ወራት ነው፤ ከነሱ ዉስጥ አራቱ የተከበሩ ናቸው። ሶስቱ ተከታታይ ሲሆኑ፤ ዙልቂእዳ ዙልሂጃና ሙሀረም ናቸው። ሌላው ደግሞ በጁማዳና በሻዕባን መካከል ያለው የሙደር (ጎሳዎች የታወቁበት)  የ”ረጀብ” ወር ነው።»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

ዙልሂጃ የታወቀው የሀጅ ወር ነው፤ ዙልቂዕዳ ደግሞ ሁጃጆች ወደ መካ የሚያቀኑበት ወር ሲሆን፤ ሙሀረምም ከሀጅ ስነስርአት በኋላ ሰዎች ወደቀያቸው የሚመለሱበት ወር ነው።  አላህ ረጀብንም ከእነዚህ  የረከበሩ ወራት  አድርጎታል። 

እነዚህ ወራት (የተከበሩ) ናቸው ስንል፤

1- እነዚህ ወረሰቶች ጦርነት የተከለከለባቸው ወራት ናቸው።  
ሙስሊሞች ላይ ጥቃት ከፈፀመባቸው እራሳቸውን ለመከላከል ብቻ ካልሆነ በስተቀር ውጊያ አይፈቀድም።

2- በነዚህ ወራት አላህ ክልክል ያደረጋቸውን ነገሮች መፈፀም በሌላ ወራት ወንጀልን እንደመፈፀም አይደለም። ስለዚህም አላህ እነዚህን ወራቶች ለይቶ ነብሳችንን እንዳንበድል አሳስቦናል፤ «በነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ» ። 

እራስን መበደል አስከፊ መሀይምነት ነው። በአንድ ሰውና በጌታው መካከል የሚፈፀም እራስን መበደል ለአላህ መፈፀም የሚገባን ሀላፊነት አለመወጣት ነው።
በራስ ላይ ከሚፈፀሙ በደሎች ሁሉ ትልቁ  በአምልኮ ፍጥረታትን ከአላህ ጋር ማጋራት “ሽርክ" ነው። ሰዎች ላይ የሚፈፀም በደልም ቢሆን የሚጎዳው ሰሪዉን ነውና እራስን መበደል ነው። ለራሱ ያወቀ በማንኛውም ጊዜ ከበደል ይርቃል። 

ኢባደላህ!
አላህ እነዚህን ወራቶች አክብሯቸዋልና እኛም ከፍተኛ ክብር መስጠት ይገባናል። 
እነዚህ ወራቶች ሲገቡ፤ አላህ ክብርን እንደለገሳቸው ልናስታውስና ከወንጀል ለመራቅ ያለንን ቁርጠኝነት ልናድስ ይገባል። ይህ ልባዊ ኢባዳ ነው። 

ወንጀልን በማንኛውም መፈፀም የተከለከለ ቢሆንም በነዚህ ወራት ግን ክልክልነቱ የበረታ ነው።

ስለዚህም ከምንም አይነት ወንጀሎች መጠንቀቅ እና ወደ አላህ መመለስ ያስፈልገናል።   ከትናንሽም ይሁን ከትላልቅ ወንጀሎች በአላህ እንጠበቅ። 

ሸይጣንን እናሸንፍ!
አላህ ከጥፋት ይጠብቀን..

አሚን!!

አኹኩም ፊላህ አቡጁነይድ ሳላህ አህመድ


http://t.me/abujunaidposts
813 viewsedited  17:26
Open / Comment
2021-07-28 15:39:00
የነሲሓ ቤተሰቦች ልዩ ኮንፈረንስ

በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ★★★★★
ነሐሴ 1/ 2013 ከቀኑ 6:30 ጀምሮ

የነሲሓ ታሪካዊ ሒደቶች
ቤተሰባዊ ምክክሮች
የእውቅና ፕሮግራሞች
ልዩ የምሳ ብፌ ዝግጅት
የዳሩተውሒድ ሪፖርትና ብስራት
ቃለ መጠይቆች እና አዝናኝ ፕሮግራሞች

የመግቢያ ዋጋ
– ለአንድ ሰው 3000 ብር
– ለባልና ሚስት 5,000 ብር

ገቢው ሙሉ በሙሉ ለነሲሓ ቲቪ ይውላል

ትኬቱን ለማግኘት
በተከታዩ ሊንክ ቀድመው ይመዝገቡ
http://nesiha.tv/confe

ወይም ይደውሉ
+251972757575

@nesihatv
435 views12:39
Open / Comment
2021-07-26 21:21:32 ልዩ የክረምት የወንዶች ኮርስ ከ12 አመት በላይ ለሆኑ ታዳጊዎችና ወጣቶች

“አላህ መልካም ለሻለት ሰው ዲኑን ያስገነዝበዋል”

በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ዳሩል ሀዲስ የዓረብኛ ቋንቋና የሸሪዓ ትምህርቶች ኢንስቲትዩት

እድሜያቸው ከ12 ዓመት በላይ ለሆኑ ወንድ ታዳጊዎችና ወጣቶች

ከሐምሌ 28 እስከ ነሐሴ 30 / 2013 የክረምት ኮርስ ለመስጠት መዘጋጀቱን ይገልፃል።

➤ትምህርቱ የሚሰጠው በተመላላሽ ፕሮግራም ከሰኞ እስከ ሀሙስ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡30

 ➤ት/ቱ የሚሰጥበት ቦታ፣ ቤቴል አርባ ሜትር በሚገኘው በአል-ዓፊያ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት

➤ኮርሱ የሚያካትታቸው የትምህርት ዓይነቶች፣

❶ ለታዳጊዎች፣ በደረጃ አንድና ሁለት

  አል ኡስሉ ሰላሳ

 ቀዋዒዱል አል አርበዓ

ነዋቂደል ኢስላም ከሼይኽ ሀይሰም ማብራሪያ ጋር በአማርኛና በዐረብኛ፣

ቁርአን ተጥቢቅ

 የተለያዩ የተርቢያ ትምህርቶች

❷ ለወጣቶች

  ሙዘኪራህ ፊል አቂደቲል ዋሲጢያ 

  አልበይቁንያ

  አል አርበዒን አነወውያ

  ከወጣቶች ጋር ተያያዥ የሆነ የተርቢያ ትምህርት

የምዝገባ ቦታ፦

ቤቴል በሚገኘው የነሲሓ ዳዕዋ ማስተባበሪያ ቢሮ በአካል በመገኘት

  የምዝገባ ጊዜ፦

ከሐምሌ 20-24/2013  ከጠዋቱ 3፡00  - 10፡30

  ክፍያ፦ ለኪታብ እና ተያያዥ ወጪዎች ለአንድ ሰው 300 ብር

ለበለጠ መረጃ ይደውሉ

0912617004 /0912023190

ዳሩል ሀዲስ የዓረብኛ ቋንቋ እና የሸሪዓዊ ትምህርቶች ኢንስቲትዩት

T.me/darulhadis18
864 viewsedited  18:21
Open / Comment
2021-07-24 11:37:00 ለሴት ታዳጊዎችና ወጣቶች
ልዩ የሴቶች በሴቶች የክረምት ኮርስ

“ዕውቀት ከተግባርም ሆነ ከንግግር ይቀድማል”
(ኢማሙል ቡኻሪ)

በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ስር የሚገኘው የዳሩል ሀዲስ የሸሪዓ ትምህርትና የአረብኛ ቋንቋ መማሪያ ተቋም እድሜያቸው ከ12 ዐመት በላይ ለሆኑ ሴቶች ለአንድ ወር የተለያዩ የዲን ትምህርቶችን በ4 ጣቢያዎች ለመስጠት ተዘጋጅቷል።

የሚሰጡ ትምህርቶች
አቂዳ፣ፍቅህ፣ተርቢያ፣ተጅዊድ

የመመዝገቢያ አድራሻዎች

አለም ባንክ ስልጤ ሰፈር

09 11 71 97 42

09 12 04 56 79

ፉሪ

09 11 47 91 51

09 26 94 84 54

ቤተል

09 11 69 23 77

09 11 37 59 52

አስራ ስምንት (ኢብኑ መስዑድ)

09 04 36 66 66

09 67 67 18 91

የምዝገባ ጊዜ ከሐምሌ 19-24

የትምህርት ጊዜ ከሐምሌ 26 እስከ ነሐሴ 30 / 2013

ዳሩል ሀዲስ የዓረብኛ ቋንቋ እና የሸሪዓዊ ትምህርቶች ኢንስቲትዩት

@darulhadis18
428 views08:37
Open / Comment