2021-07-21 10:08:12
ዙል-ሂጃ ❶❶ ⓵⓶ ➀➂
(ረቡዕ፣ሀሙስ፣ጁሙዓ)
አያመ-ተሽሪቅ
አልሀምዱሊላህ!
እነሆ ዛሬ አያመ-ተሽሪቅ ተብለው ከተሰየሙት ቀናቶች የመጀመሪያው ላይ እንገኛለን።ሰለነዚህ ቀናቶች አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ በቁርአኑ
"وَاذْكُرُوا اللَّهَ فِي أَيَّامٍ مَعْدُودَات"
(البقرة:203)
"በተቆጠሩ ቀኖችም ውስጥ አላህን አውሱ።"በማለት ገልጿቸዋል።
በእነዚህ የተባረኩ ቀናቶች ተክቢራ ማድረግ የጠበቀ ሱና በመሆኑ ከዛዛታና ከወንጀል በመራቅ ከተክቢራውም በተጨማሪ አላህን ማውሳት (ዚክር) ልናበዛ ይገባል።
"አላህንም ማውሳት ከሁሉ ነገር በላጭ ነው"
(ሱረቱል አንከቡት 45)
አላህ በሰጠን ፀጋ በመታገዝ የእሱን ትእዛዛት መፈጸም
ኢብን ረጀብ (አላህ ይዘንላቸውና) አላህ በሰጠን ፀጋ ስለማመስገን ሲያወሱ
"ረሱል صلى الله عليه وسلم በሀዲሳቸው "እነዚህ ቀናቶች የሚበላበት የሚጠጣበትና አላህ የሚወሳበት ቀናት ናቸው" ማለታቸው በኢዶች ቀናት መብላትና መጠጣት አላህን ለማውሳት እንዲሁም እሱን በመታዘዝ ላይ ለመታገዝ ብቻ ነው ብለዋል።
➣ምስጋና (ሹክር) የተሟላ የሚሆነው አላህ በዋለልን ፀጋዎች በመታገዝ የእሱን ትእዛዞች የምንፈፅም ሲሆን ብቻ ነው።
➣የላቀው አላህ በተከበረው ቁርአን ከምግብ ጥሩውን እንድንመገብና እሱንም እንድናመሰግን አዞናል።
➣አላህ በሰጠው ፀጋ በመታገዝ እሱን የሚያምፅ ሰው በእርግጥ በአላህ ፀጋ ክዷል።ይህን በማድረጉም ፀጋውን አላህ ሊነሳው (ሊያነሳበት) የተገባ ይሆናል።" ብለዋል።
አላህ ሆይ! አንተን በብዛት እንድናወሳ፣ እንድናመሰግንህና ኢባዳን እንድናሳምር አግዘን። አሚን
#የዒድ_መልእክት
http://t.me/nesiha_ouserya
440 viewsedited 07:08