2021-01-19 12:45:32
ዛሬ ላይ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ በጣም የሚያስፈልገው...
መልካም አርዐያ
ልጆችን መልካም አርአያ በመሆን ማነፅ ጠቃሚ፣ ለውጤታማነት የቀረበና በህብረተሰቡ ዘንድም ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆነ የተርቢያ ዘዴ ነው።
በተርቢያ(የልጆች አስተዳደግ) ላይ መጽሐፍ መፃፍ ፣ማውራት ወይም ሥርዓተ-ትምህርትን ማዘጋጀት ቀላል ነው ፣ ነገር ግን ሰዎች በምድር ላይ ወደሚያዩት ተጨባጭ እውነታ ካልተለወጠ በስተቀር ይህ ሁሉ በወረቀት ላይ ያለ ቀለም ወይም ባዶ ቃላት ይሆናል።
በዚህ ረገድ ሰለፎች (ቀደምቶች) የነበራቸው ግንዛቤ ጥልቅ በመሆኑ ለትውልድ አስተማሪዎች እንዲህ ይሉ ነበር ፡፡
"ልጄን ከምታስተካክልበት የመጀመሪያው ነገር እራስህን ማስተካከል ይሁን።ዓይኖቻቸው ከዓይኖችህ ጋር የተሳሰሩ ናቸው ፣ በነሱ ዘንድ መልካም ማለት አንተ ያደረግከው ነገር ነው፣ ለእነሱም አስቀያሚው አንተ የተውከው ነው።"
ሰዎችን በመለወጥ (በተርቢያ) ውስጥ በጣም ዉጤታማ ከሚያደርጉ ነገሮች ከሙረቢው (ከአስተማሪው) ተግባርን ማየት እና ቃላቶች ወደ ድርጊቶች ሲለወጡ ማየት ነው።
በአብዛኛው ሰዎች የሚማሩት በሚሰሙት ሳይሆን በሚመለከቱት ነው፤ ስለሆነም በቤተሰብ ፣በመስጂድ፣ በመድረሳ፣ በትምህርት ቤት....... እና በአጠቃላይ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ውስጥ ተግባራዊ ምሳሌ ያስፈልገናል።
ይህ ማለት ግን ተምሳሌት እስክናገኝ (እስክንሆን) ድረስ የተርቢያውን ሥራ እንተወዋለን ማለት ሳይሆን እኛ ራሳችን ወደ መልካም አርአያነት መለወጥ አለብን ለማለት ነው።
ይህ አላህ ላገራላቸው ሰዎች ቀላል ቢሆንም ነገሩ ፈታኝ ነው። ሌሎችን ከመተቸታችን በፊት ሁሌም የራሳችንን እንቅስቃሴና ባህሪ ዘወር ብለን ማስተዋል አለብን።ይህ ማለት ግን ወደ ትክክለኛው ነገር ሰዎችን አናመላክት ማለት አይደለም።
ለምሳሌ አንተ ተርቢያ ከምታደርገው ሰው (ከልጆች)አንድን ነገር ትፈልጋለህ አንተ ግን በዛ ነገር ላይ አትገኝም።ይህ ተግባርህ ልጆቹ
ላይ ጫና እንዲፈጠር ውስጣቸው የተጋጨ፣ግራ የተጋቡና የሚዋልሉ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል እንጂ የምትፈልገውን መስመር እንዲይዙ አያደርጋቸውም።
ወላጆች በልጆቻችሁ ላይ ልታዩት የምትፈልጉትንና የምትወዱትን ባህሪ በመላበስ ጥሩ ተምሳሌት ሁኑ።
•┈┈••••○○❁ ❁○○••••┈┈•
አላህ ትውልድን የሚያንፁ መልካም አርአያዎችን ያብዛልን ያሉትንም ይጠብቅልን።ለኛም መልካሙን ያግራልን።
#ተርቢያ #አርዐያ
@nesiha_ouserya
2.5K viewsedited 09:45