Get Mystery Box with random crypto!

🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺

Logo of telegram channel nesiha_ouserya — 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺
Logo of telegram channel nesiha_ouserya — 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺
Channel address: @nesiha_ouserya
Categories: Education
Language: English
Country: Ethiopia
Subscribers: 2.48K
Description from channel

ለስኬታማ ቤተሰብ - نحو الأسرة الناجحة
ቤታችንን ኢሰላማዊ በማድረግ ትዉልድን እናድን!
ስለ ቻናላችን ያሎትን ሀሳብና አስተያየት
በ @nesiha_ouserya_Bot ይላኩልን!
እናመሰግናለን!
@nesiha_ouserya

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages 16

2021-02-11 16:07:28 ሁለቱም የትዳር አጋሮች ከሚጋሩት ሀቆች ❶ የመኝታ ሀቅ (1) ትዳር ከተደነገገበት ጥበብ አንዱ ሰዎች ተፈጥሮአዊ የሆነ ስሜታቸውን ሀላል በሆነ መንገድ ያረኩበት ዘንድ ነው። ባልና ሚስት በኒካህ መጣመራቸው አንዱ ለሌላው መሰተሪያ ሊሆን ወደ ሀራም እንዳይመለከቱም ሊያደርጋቸው ነው። የመኝታ ሀቅ ባልና ሚስት ከሚጋሩበት ሀቅ ቢሆንም ሚስት ላይ ያለው ሀቅ ግን የጠነከረ ነው።ይህንንም ከሚያመለክቱ…
766 viewsedited  13:07
Open / Comment
2021-02-09 07:54:53 #ወሳኝ ቁጥር አንድ

ውድና የተከበራችሁ ወላጆች ልጆችን በኢስላማዊ ተርቢያ በማነፅ ሂደት ውስጥ ወሳኝ የሆነውን ነጥብ እንጠቁማቹ ።
•• ● ••

ሰዒድ ቢን ጁበይር (رحمه الله) የተባሉ ታብእይ
"እኔ ለልጄ ስል ሰላትን እጨምራለሁ " ይሉ ነበር።
••●••
➬ይህንን ንግግር ሸይኽ አብዱረዛቅ አልበድር ሲያብራሩት እንዲህ ይላሉ፦

በዘመናችን ለልጆች ከሚያስፈልጋቸው ነገር ዋናው የዚህ አይነት እውነተኛ የሆነ የወላጆች እዝነት ነው።ይህም ሰላትን በማርዘም ልጆችን ቀልባቸውን እንዲያበጅ፣ነፍሳቸውን እንዲያጠራ፣ከፈተና እንዲጠብቃቸው፣በዲን ላይ እንዲያፀናቸው፣አላህን በመማፀንና በዱዓ ችክ በማለት(በመዘውተር) ነው።

በተለይ ከዚህ ወጣቶችን እየጠለፈ ወደ ጥልቅ ስፍራ ከሚከት የፈተና አውሎ ነፋስና ግጭቶች አላህ በቸርነቱ ልጆቻችንን ይጠብቅልን ፣ ይምራቸው እንዲሁም ያስተካክላቸው ዘንድ አላህን ዘወትር ልንለምነው ይገባል፡፡
••●••
አላህ ያግራልን።

#ተርቢያ
@nesiha_ouserya
1.3K viewsedited  04:54
Open / Comment
2021-02-05 20:04:18
ልጆች ከአላህ የሆኑ ፀጋና ስጦታዎች ናቸው።

አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዲህ ይላል፦

{لِّلَّهِ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ يَهَبُ لِمَن يَشَاءُ إِنَاثًا وَيَهَبُ لِمَن يَشَاءُ الذُّكُورَ
أَوْ يُزَوِّجُهُمْ ذُكْرَانًا وَإِنَاثًا ۖ وَيَجْعَلُ مَن يَشَاءُ عَقِيمًا ۚ إِنَّهُ عَلِيمٌ قَدِيرٌ } [الشورى : 49-50]

የሰማያትና የምድር ንግሥና የአላህ ነው፡፡ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ ለሚሻው ሰው ሴቶችን (ልጆች) ይሰጣል፡፡ ለሚሻውም ሰው ወንዶችን ይሰጣል፡፡
ወይም ወንዶችና ሴቶች አድርጎ ያጠናዳቸዋል፡፡ የሚሻውንም ሰው መካን ያደርገዋል፡፡ እርሱ ዐዋቂ ቻይ ነውና፡፡

ሱረቱ ሹራ 49-50

አላህ በዚህ አንቀፅ ላይ ስለ ልጆች ሲገልፅ ሴቶችን ከወንዶች ያስቀደመበትን ምክንያት ኢብን ዐጢያ በተፍሲራቸው ሲያብራሩ

➬ይህ የሴቶችን ክብርና እነሱን መጠበቅና ለነሱ በጎ መዋልን የሚያሳስብ ነው ብለዋል።

ልጅ መሰጠትን በተመለከተ ሰዎች ለ4 ተከፍለዋል።

1. ሴት ልጆች ብቻ የተሰጣቸው
እንደ ነብዩላህ ሉጥ

2. ወንድ ልጆች ብቻ የተሰጣቸው
እንደ ነብዩላህ ኢብራሒም

3. ሴትና ወንድ የተሰጣቸው እንደ ነብዩ ሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም

4. ልጅን ያልተሰጡ
እንደ ነብዩላህ የህያ

ያ አላህ! ልጆቻችንን በመልካም በማነፅ ተግባራዊ ምስጋና የምናደርስ ባሮች አድርገን።

#ተርቢያ
@nesiha_ouserya
1.8K viewsedited  17:04
Open / Comment
2021-01-31 20:00:13 አስደሳች ዜና ለዕውቀት ፈላጊዎች

ከ 12 አመት በላይ ላሉ ታዳጊ ሴቶች ብቻ

የሚሰጡ ትምህርቶች

➬ዐቂዳ

➬አዳብ

➬ፊቅህ

የትምህርት ቀናት በሳምንት ሁለት ቀን

ፈረቃ 1 ፡ ሰኞ እና ረቡዕ

ፈረቃ 2 ፡ ማክሰኞ እና ሀሙስ

ከ3፡00-6፡30

ትምህርቱ የሚሰጠው ለ 2 ወር ሲሆን የትምህርቱ አሰጣጥም የተማሪዎችን የፈረቃ መቀያየር ከግምት ያስገባ ነው።

ትምህርቱን በአግባቡ ተምረው ላጠናቀቁ ተማሪዎች የምስክር ወረቀት የሚሰጥ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።

የምዝገባ ቀን ከሰኞ ጥር 24- ሀሙስ ጥር 27 2013

የመማሪያ ቦታ፦ ከጦር ሀይሎች ከፍ ብሎ የሚገኘው አባጅፋር መስጂድ አካባቢ
ከሴቶች መግቢያ ፊት ለፊት
(የቀድሞው መርየም መድረሳ)

ለበለጠ መረጃ፦
በስልክ ቁጥር +251938674144 ይደውሉ።

ዳሩል ሀዲስ የዓረብኛ ቋንቋ እና የሸሪዓዊ ትምህርቶች ኢንስቲትዩት

@darulhadis18
1.6K views17:00
Open / Comment
2021-01-31 12:12:56 በመጀመሪያው የግንኙነት ለሊት ምን ማድረግ ይገባል
۩••۩┈┈┈•⊰۩ ۩⊱•┈┈┈۩••۩
ጥያቄ፡
በጋብቻ ቀን ለሊት ለባልና ሚስት ሱናው ምንድነው? ከነብዩ የተገኙ ዱዓዎችንና ስራዎችን እንድትጠቅሱልን እንፈልጋለን፡

መልስ፡
●ባል ከሚስት ጋር በሚገናኝበት ለሊት ትኩረት ሊሰጣቸው ከሚገቡ ነገሮች ውስጥ፦

►ለሷ ክንፉን ዝቅ አድርጎ(ተረጋግቶና) ጭርታን በሚያስወግድ መልኩ ወደሷ መግባት አለበት። ምክንያቱም በዚህ ሰአት ጭንቀትና ፍርሀት እሷ ዘንድ ይኖራልና።

►ሯሷን ይዞ የሚታወቀውን ዱዓ ያድርግ
"አላህ ሆይ! ከኸይር ነገሯና በእሱ ላይ እሷን የፈጠርክበትን ኸይር እጠይቅሀለሁ፡ ከሸሯና በእሱ ላይ እሷን ከፈጠርክበት ሸር በአንተ እጠበቃለሁ"፡ ይህንን በግልጽ (ድምጹን ከፍ አርጎ) ይበል፡ ምናልባት ሰግታ "ምንድነው? በኔ ላይ ሸር አለ?" ትላለች ብሎ ካልፈራ በስተቀር፡ ይህን ከፈራ እጁን ራሷ ላይ አስቀምጦና ድምጹን ዝቅ አርጎ መቅራት በቂ ነው።

►ሁለተኛው የአላህ መልእክተኛ -ﷺ- አንድ ሰው ከባለቤቱ ጋር ግንኙነት ሲያደርግ እንዲል ያነሳሱበትን ዚክር ይበል

▹<<አንዳቹህ ወደሚስቱ ሲመጣ "በአላህ ስም! አላህ ሆይ እኛን ከሸይጧን ጠብቀን፡ የምትሰጠንንም ከሸይጧን ጠብቅ" ካለ በመካከላቸውም ልጅ ከተቀደረ ሸይጧን መቼም አይጎዳውም>>

▹ይሄ ልጆችን ከማስተካከያ ሰበቦች ነው። ቀለል ያለም ሰበብ ነው።

●ልክ እንደዚሁ መገንዘብና ማወቁ ከሚያስፈልግ ነገሮች… ግንኙነት እስካረጉ ድረስ የዘር ፈሳሽ ባይፈስም በሁለቱም በኩል ገላን መታጠብ ግድ ይላል።ከፊሎች በተቃራኒው መታጠብ ግድ የሚለው የዘር ፈሳሽ ሲፈስ ነው ብለው ያስባሉ ይሄ እሳቤ ስህተት ነው።ምክንያቱም ነብዩ -ﷺ- <<በአራት ቅርንጫፎቿ መሀል ከተቀመጠና ግንኙነት ከፈፀመ የዘር ፈሳሽ ባይፈስም ትጥበት ግድ ሆኗል>>ብለዋልና።

►በዚህም ከሁለት በአንዱ ትጥበት ግድ ይላል፡ ወይ የዘር ፈሳሽ በመውጣት ወይም በግንኙነት። የዘር ፈሳሽ የወጣው በመሳሳም ቢሆን በመተቃቀፍም ቢሆን ወይ በስሜት በማየትም ሆነ በመነጋገር በየትኛውም ቢሆን መታጠብ ግድ ነው።ግንኙነት ተደርጎም የዘር ፈሳሽ ባይወጣም መታጠብ እንዲሁ ግድ ነው።

►ብዙ ሰዎች ግንኙነት ፈፅመው በወቅቱም የዘር ፈሳሽ ካልወጣ እንደማይታጠቡና በዚህም ብዙ ወራት እንዳለፉ (ምን ማድረግ እንዳለባቸው) ይጠይቁናል። የዚህ ምክንያቱ የሚያገባ ሰው በጋብቻ ወቅት ምን ማድረግ እንደሚገባና ምን ግዴታ እንደሆነ አይጠይቅም። ብዙዎቹም ሰዎች እንደዚህ አይነት ትምህርቶችን በወጣቶች መካከል አያሰራጩም።
۩••۩┈┈┈•⊰۩ ۩⊱•┈┈┈۩••۩
لِلشَّــيْخ العَلّامـَـة/ مُحَـمَّد بـنُ صَـالِح العُثَـيْمِين -رَحِــمَهُ الله-

#ትዳር
@nesiha_ouserya
1.8K viewsedited  09:12
Open / Comment
2021-01-23 22:00:33 ሁለቱም የትዳር አጋሮች ከሚጋሩት ሀቆች

❶ የመኝታ ሀቅ (1)

ትዳር ከተደነገገበት ጥበብ አንዱ ሰዎች ተፈጥሮአዊ የሆነ ስሜታቸውን ሀላል በሆነ መንገድ ያረኩበት ዘንድ ነው።

ባልና ሚስት በኒካህ መጣመራቸው አንዱ ለሌላው መሰተሪያ ሊሆን ወደ ሀራም እንዳይመለከቱም ሊያደርጋቸው ነው።

የመኝታ ሀቅ ባልና ሚስት ከሚጋሩበት ሀቅ ቢሆንም ሚስት ላይ ያለው ሀቅ ግን የጠነከረ ነው።ይህንንም ከሚያመለክቱ የአላህ መልእክተኛ ﷺ ንግግሮች፦

قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: (إذا دعا الرجل امرأته إلى فراشه فأبت فبات غضبان عليها لعنتها الملائكة حتى تصبح) [رواه البخاري].

"አንድ ወንድ ሚስቱን ወደ መኝታ ሲጠራት እምቢ ካለችና እሱም ተቆጥቶባት ካደረ እስክታነጋ መላኢካዎች ይረግሟታል።"

وفي صحيح مسلم عن أبي هريرة رضي الله عنه أن النبي صلى الله عليه وسلم قال: والذي نفسي بيده ما من رجل يدعو امرأته إلى فراشه فتأبى عليه إلا كان الذي في السماء ساخطاً عليها حتى يرضى عنها.

"ነፍሴ በእጁ በሆነችው እምላለሁ ማንም ወንድ የለም ሚስቱን ወደ መኝታ ጠርቷት እምቢ ያለችው እንደሆነ ባሏ በሷ እስኪደሰት ድረስ በሰማይ ያለው በሷ ላይ የተቆጣ ቢሆን እንጂ።"

ከላይ የተጠቀሱት ትክክለኛ ሐዲሶች እንደሚያመላክቱት ሚስት ባሏ ወደ መኝታ ሲጠራት ትእዛዙን አለመፈፀሟ ወንጀሉ ከባድ በመሆኑ የአላህ ቁጣ እንዲሁም የመላኢካዎች እርግማን በሷ ላይ እንዲሆን ያደርጋል።

ይህ ሲባል ሴቷ ሸሪዓዊ ምክንያት ካላት(የግዴታ ፆም ላይ ካለች፣ምክንያት ሊሆን የሚችል ህመም ካላት...) ትእዛዙን ባትፈፅም የማትወቀስ ሲሆን፤ ሸሪዐው ግንኙነትን የከለከለበት አንዳንድ ሁኔታዎች ላይ(ፆም ላይ፣ሀጅ ላይ፣የወር አበባ ላይ ስትሆን)ደግሞ ትእዛዙን መፈፀሟ ሀራም ይሆንባታል።

ውዷ ሚስት ሆይ! በዚህ ጉዳይ ላይ ሰብር ማድረግሽ ሰብር ለማድረግ የሚከብድሽ(አላህ ይጠብቀንና) የህይወት አጋጣሚ (በአላህ ፈቃድ),እንዳይከሰት ያደርጋልና በተቻለሽ የባልሽን ፍላጎት ለሟሟላት ልትጥሪ ይገባል።


#ትዳር #የጋራ ሀቅ
@nesiha_ouserya
2.8K viewsedited  19:00
Open / Comment