Get Mystery Box with random crypto!

🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺

Logo of telegram channel nesiha_ouserya — 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺
Logo of telegram channel nesiha_ouserya — 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺
Channel address: @nesiha_ouserya
Categories: Education
Language: English
Country: Ethiopia
Subscribers: 2.48K
Description from channel

ለስኬታማ ቤተሰብ - نحو الأسرة الناجحة
ቤታችንን ኢሰላማዊ በማድረግ ትዉልድን እናድን!
ስለ ቻናላችን ያሎትን ሀሳብና አስተያየት
በ @nesiha_ouserya_Bot ይላኩልን!
እናመሰግናለን!
@nesiha_ouserya

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages 13

2021-03-28 15:48:12 የዛሬው የጁምዓ ኹጥባ
ኢስላማዊ የልጆች አስተዳደግ(ተርቢያ)
t.me/sultan_54

#ተርቢያ
235 viewsedited  12:48
Open / Comment
2021-03-27 09:07:37 #ልጆችን በምን እናንፅ?

#ፆም

አንድ ህፃን ልጅ በፆም የሚታዘዘው መቼ ነው? እስኪያድግ ድረስ ዝም ይባላልን? ወይስ በህፃንነቱ እንዲፆም ይገደዳል?

ወላጅ በልጆቹ ላይ ያለው ሀላፍትና ትልቅ ነው። ይህ ሀላፍትና አላሁ ተአላ በሰው ልጅ ላይ ካስቀመጠው አደራ/አማና/ አንዱ ነው።

አላሁ ተአላ በሚወደው መንገድ የተወጣው ከሆነ እድለኛ ነው አልያ ግን አደራውን ችላ ያለ ከሆነ በዱንያም በአኼራም የከሰረ ይሆናል።

"يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ قُوٓا۟ أَنفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًا وَقُودُهَا ٱلنَّاسُ وَٱلْحِجَارَةُ عَلَيْهَا مَلَٰٓئِكَةٌ غِلَاظٌ شِدَادٌ لَّا يَعْصُونَ ٱللَّهَ مَآ أَمَرَهُمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ" التحريم 6
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከኾነች እሳት ጠብቁ፡፡ በእርሷ ላይ ጨካኞች፣ ኀይለኞች የኾኑ መላእክት አልሉ፡፡ አላህን ያዘዛቸውን ነገር (በመጣስ) አያምጹም፡፡ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ፡፡"
አል ተህሪም 6

"يُوصِيكُمُ ٱللَّهُ فِىٓ أَوْلَٰدِكُمْ " النساء 11
"አላህ በልጆቻችሁ ያዛችኋል፡፡ "አል ኒሳእ 11

ስለዚህ ወላጆች የልጆቻቸው አስተዳደግ ላይ ልዩ ትኩረት ማድረግ አለባቸው። ልጆች ለአቅመ አደም ከመድረሳቸው በፊት አምልኮን/ ኢባዳን/ ሊለማመዱ ይገባል።

ፆም ትእግስት ከሚያስፈልጋቸው የአምልኮ ዘርፍ አንዱ ነው። ስለዚህ ልጆች ካደጉ በኃላ እንዳይከብዳቸው በግዜ ወላጆች ሊያለማምዷቸው ይገባል።

የአላህ መልክተኛ ባልደረባዎች ልጆቻቸውን በህፃንነታቸው ፆምን ያለማምዷቸው ነበር ። የአላህ መልክተኛም አይተው በዝምታ ያልፏቸው ነበር።

የሙአወዝ ልጅ የሆነችው ሩበይእ አላህ ስራዋን ይውደድላትና እንዲህ ትላለች"ህፃን ልጆቻችንን እናፆማቸው ነበር።ወደ መሰጂድም እንሄድ ነበር ። ከጥጥ የተሰራ መጫወቻም እንይዝላቸው ነበር። አንዳቸው ምግብ ፈልጎ ሲያለቅስ ይህን መጫወቻ እንሰጠው ነበር። በዚህ ሁኔታ ፍጡር እስኪደርስ ድረስ እናቆየው ነበር።"
የቡኻሪና የሙስሊም ዘገባ

ለአቅመ አደመ ያልደረሰ ሆኖ ነገር ግን መፆም የሚችል ከሆነ ወላጆች ልጆቻቸውን በፆም ሊያዟቸው ይገባል።ምንም እንኳን ግዴታ ባይሆንባቸውም ይታዘዛሉ። ምክንያቱም የአላህ መልክተኛ ልጁ በቻለ ግዜ በኢባዳ ላይ እንድናዘው ታዘናል።

የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል፦
"مروا أبنائكم بالصلاة لسبع سنين واضربوهم عليها لعشر سنين وفرقوا بينهم في المضاجع"
"ልጆቻችሁ ሰባት አመት የሞላቸው ጊዜ በሰላት እዘዟቸው። በአስር አመታቸው ካልሰገዱ ግረፏቸው። በመኝታ ቦታቸውም ለያዮዋቸው።" የአህመድ ዘገባ

ወላጅ ሆኖ ለልጁ መልካም ነገር የማይመኝ ማንም የለም ሆኖም ግን ልጆች በኢባዳ ላይ ሰነፍ ሆነው እንዲያድጉ ማድረግ የለብንም። ሱብሂ ሰላት ለመስገድ ብርድ ይመታሀል፣ ፆም ለመፆም ይርብሀል በሚል ምክንያት ብቻ ሰነፍ ልናረጋቸው አይገባም።ሁኔታቸውን እያየን ልናጠናክራቸው ይገባል።
T.me/dawudyassin

አላህ ይወፍቀን።

#ተርቢያ#ረመዳን
714 viewsedited  06:07
Open / Comment
2021-03-26 16:51:14 ከሚስት ጋር በመኗኗር ዙሪያ የረሡል ﷺ ፈለግ "በመልካምም ተኗኗሩዋቸው" ኒሳእ 119 •┈┈┈┈•✿ ✿•┈┈┈┈•     ❶ በሚስት ፊት ፈገግ ማለት ረሡል ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ "በወንድምህ ፊት ፈገግ ማለትህ ላንተ ሰደቃ ነው" ቲርሚዚይ ዘግበውታል። ባለቤትህ ስትሆን ደግሞ አስበሃዋል? ❷ ሚስትን በማጉረስ እሷን ማሞናደል ረሡል ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ "አንተ አንድንም ነገር…
986 viewsedited  13:51
Open / Comment
2021-03-25 11:26:03
የልጅዎ አሳዳጊ ነዎት ወይስ ሙረቢ?

ልጆችን በሚያሳድጉ እና በተርቢያ በሚያንፁ ወላጆች መካከል ሰፊ ልዩነት አለ፤

የመጀመሪያዎቹ
አላማቸው ማሳደግ ነውና ትኩረታቸው በልጆቻቸው አካላዊ እድገታቸው ላይ ብቻ ነው። ሰለዚህም በአብዛኛው ለጤናቸው፣ ለልብሶቻቸው እና ምግቦቻቸው ይጨነቃሉ።

ሁለተኛዎቹ
አላማቸው ከአካላዊው እድገት ከፍ ባለ የሞራል፣ የግብረገብ፣ የሀያዕ እነፃ ላይ ነው። ስለሆነም፤ በአላህ ውዴታ፤ በመልካም ስነምግባር፣ በጎ እሴቶችን በማለማመድ የላቀ ማንነት ኩትኮታ (ተርቢያ) ላይ አትኩረው ይሰራሉ።

አላህ ሁላችንንም ለመልካም ተርቢያ ምሳሌዎች ያድርገን!


ለመሆኑ እራስዎን ከየትኞቹ ይመድባሉ፤ አሳዳጊ ወይስ ኮትኩቶ የሚያንፅ (ሙረቢ)?


@ተንቢሀት
68 views08:26
Open / Comment
2021-03-25 09:15:45 «ዝክረ ረመዳን»
ከጎግል ፕለይ ማውረድ ላልቻላችሁ አታች አድርገነዋል... ከማስታወቂያ ነፃ የሆነ ድንቅ የፆም ህግጋት የመማሪያ አፕ ይጫኑ።

https://t.me/zkre_remedan
216 views06:15
Open / Comment