Get Mystery Box with random crypto!

🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺

Logo of telegram channel nesiha_ouserya — 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺
Logo of telegram channel nesiha_ouserya — 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺
Channel address: @nesiha_ouserya
Categories: Education
Language: English
Country: Ethiopia
Subscribers: 2.48K
Description from channel

ለስኬታማ ቤተሰብ - نحو الأسرة الناجحة
ቤታችንን ኢሰላማዊ በማድረግ ትዉልድን እናድን!
ስለ ቻናላችን ያሎትን ሀሳብና አስተያየት
በ @nesiha_ouserya_Bot ይላኩልን!
እናመሰግናለን!
@nesiha_ouserya

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages 15

2021-03-03 08:17:30 መልእክት #ለባሎች,,,,,,,,,,

•┈┈••••○○❁ ❁○○••••┈┈•

አምር ኢብኑል አስ አላህ ስራዉን ይዉደድለትና የአላህን መልእክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም

አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ከሰዎች ሁሉ እርሶ ዘንድ ተወዳጅ ማን ነዉ? ሲል ጠየቃቸው።

እሳቸውም፡ ለምን ፈለግክ? አሉት

አምር: ማወቅን ወድጄ !

መልእክተኛዉም: አኢሻ! አሉ

•┈┈••••○○❁ ❁○○••••┈┈•

የአላህ መልእክተኛ፣ ታላቁ ነብይ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ባለቤታቸዉን አኢሻን (ረዲየላሁ አንሃ) እጅጉኑ እንደሚወዷት በግልፅ ተናገሩ።

ባል ሆይ ይህን ተግባር አንድ ቀንም ፈፅመሀው ታውቃለህ? !

ለባለቤትህስ እንደምትወዳት ነግረሃት ታውቃለህ?!

ለሷ ያለህን ፍቅርና ውዴታ ቤተሰቦቿ ዘንድ ለመግለፅስ ሞክረህ ታውቃለህ ?!

ሞክረው ትደሰታለህ ትረካለህ ዉዴታና እዝነት የሞላው ህይወትም ትኖራለህ።

#ትዳር
@nesiha_ouserya
1.6K views05:17
Open / Comment
2021-02-28 20:27:10 قال الله تعالى: ﴿ وَإِنَّ اللَّهَ لَهَادِ الَّذِينَ ءَامَنُوا إِلَى صِرَاطٍ مُسْتَقِيمٍ ﴾ [الحج:٥٤]


"አላህም እነዚያን ያመኑትን ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ መሪ ነው።"
ሱረቱል ሀጅ 54


ቴክኖሎጂው ባደገበትና በተስፋፋበት ዘመን ልጅን ለማሳደግ የተሻለው ዘዴ

በአላህና በመልዕክተኛው ያላቸው እምነት ጠንካራ እና ጥልቅ እንዲሆን ማድረግ ነው።

➬በመጀመሪያ ደረጃ ወደድንም ጠላንም አላህ ከጠበቃቸው በስተቀር ልጆች አላህና መልዕክተኛው የማይወዱትን ነገሮች ሊመለከቱ እንደሚችሉ ወላጆች ማመን አለብን።

➬ሁለተኛ በዚህ ዘመን ልጆችህን በመቆጣጠር የማትወደውን ነገር እንዳይመለከቱ ማድረግ እንደማትችል ማወቅ አለብህ።

ዛሬ ላይ ትግሉ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን ከልጅህ ላይ መቀማት ሳይሆን ልጅህ ልብ ላይ እምነትን መዝራት መሆን አለበት።

ያ አላህ! ልጆቻችንን ይጠብቅልን።እኛንም መልካም አርአያ አድርገን።

#ተርቢያ
1.9K viewsedited  17:27
Open / Comment
2021-02-22 08:19:41 ልጆችን አላህ ይከታተለኛል የሚል ስሜት እንዲያድርባቸው በማድረግ ማነፅ


ሉቅማን ለአብራኩ ክፋይ ለሆነው ለልጁ አደራ ካለውና ከመከረው ነገር አንዱ ልጁ ከአላህ ጋር የተሳሰረ መሆኑና ከሰዎች ዕይታ ቢሸሸግም ባይሸሸግም በአላህ ቁጥጥር ስር መሆኑን ማሳወቅ ነበር።

አላህ ሁሉንም ነገር ማንነቱን ምይሁን ብዛቱን እንደሚያውቅ፤ ወንጀለኛ የቻለውን ያህል ወንጀሉን ሊደብቅ ቢሞክር አላህ እንደሚያየው እንዲሁም በትንሳዔ ቀን ይቺንም ወንጀል እንደሚያቀርባትም ነግሮት ነበር።

يَٰبُنَيَّ إِنَّهَآ إِن تَكُ مِثۡقَالَ حَبَّةٖ مِّنۡ خَرۡدَلٖ فَتَكُن فِي صَخۡرَةٍ أَوۡ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ أَوۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ يَأۡتِ بِهَا ٱللَّهُۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَطِيفٌ خَبِيرٞ

(ሉቅማንም አለ) «ልጄ ሆይ! እርሷ የሰናፍጭ ቅንጣት ክብደት ያህል ብትሆንና በቋጥኝ ውስጥ ወይም በሰማያት ውስጥ ወይም በምድር ውስጥ ብትሆን አላህ ያመጣታል፡፡ አላህ ሩኅሩኅ ውስጥ ዐዋቂ ነውና፡፡
ሉቅማን 16

እዚህች አንቀጽ ላይ አባቶች ልጆቻቸውን ሲያስጠነቅቁና ሲያስፈራሩ በአላህ ሊሆን እንደሚገባ፣በአላህ ቁጥጥር ስር መሆናቸውን፥ አላህ ሁሉንም የሚሰራውን ነገር እንደሚያውቅና እንደሚመለከት ማስገንዘብ እንዳለባቸው ተጠቁሟል።

المصدر: الموقع الرسمي للشيخ #عبدالرزاق_بن_عبدالمحسن_البدر حفظه الله .

#ተርቢያ
@nesiha_ouserya
2.3K views05:19
Open / Comment
2021-02-20 22:05:37 የመኝታ ሀቅ(3)

۩••۩┈┈┈•⊰۩ ۩⊱•┈┈┈۩••۩

قال رسول ك تصوم النهار وتقوم الليل قلت بلى يا رسول الله قال فلا تفعل صم وأفطر وقم ونم فإن لجسدك عليك حقا وإن لعينك عليك حقا وإن لزوجك عليك حقا
رواه البخاري
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ፦
"አብደላህ ሆይ! አንተ ቀን እንደምትጾም ለሊት እንደምትሰግድ አልተነገረኝምን?አዎ የአላህ መልዕክተኛ አልኩ።እሳቸውም ይህን አታድርግ።ፁም አፍጥር ስገድ ተኛ።አካልህ ባንተ ላይ ሀቅ አለው፣ዐይንህም ባንተ ላይ ሀቅ አለው፣ባለቤትህም ባንተ ላይ ሀቅ አላት።"
ቡኻሪ ዘግበውታል

በሀዲሱ ሰሃባው ለሊቱን ሙሉ በዒባዳ ማሳለፉ በዚህም የሚስቱን ሀቅ አለመወጣቱ ትክክል እንዳልሆነ ተጠቁሟል።

ባል የሚስቱን ተፈጥሮአዊ የሆነውን የግንኙነት ፍላጎት የሚያሟላው ከሀራምና ከአጸያፊ ነገሮች ርቃ ጥብቅ ትሆን ዘንድ ነው።

"አንድ ወንድ ለኡዝር ቢሆን እንጂ ከባለቤቱ ጋር ግንኙነት መፈፀሙ ግዴታ ነው።"
ይህ የኢማሙ ማሊክ፣የአቢ ሀኒፋ እና የኢማሙ አህመድ አቋም ሲሆን ኢብኑ ተይሚያም ይህን መርጠውታል።

የግዴታው ልክም እሷን በሚያስፈልጋትና ጥብቅነትን ሊያስገኝ በሚችልበት ደረጃ ሊሆን ይገባዋል።

"ባል በራሱ ላይ የዚህ ነገር ድክመት ካለበትና የመኝታ ሀቋን መስጠት ካልቻለ ሚስቱን ጥብቅ ያደርጋት ዘንድ ህክምና ሊያደርግ ይገባል።"
ተፍሲር ቁርጡቢ
۩••۩┈┈┈•⊰۩ ۩⊱•┈┈┈۩••۩
#ትዳር የጋራ ሀቅ
@nesiha_ouserya
2.1K viewsedited  19:05
Open / Comment
2021-02-11 16:10:28 ኩኑዝ... የማንነት እነፃ
ልዩ የሙሀደራ መድረክ

هَـٰذَا بَیَانࣱ لِّلنَّاسِ وَهُدࣰى وَمَوۡعِظَةࣱ لِّلۡمُتَّقِینَ

ኢን ሻ አላህ እሁድ የካቲት 7/2013 ልክ ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ በካራ ስልጤ ሰፈር አዒሻ መስጂድ ልዩ የሙሀደራ መድረክ
ይካሄዳል።

የእምነት መከታ ለሸይጣን ጉትጎታ
በኡስታዝ ኢልያስ አህመድ


እና

አሻጋሪ ፅናት
ኡስታዝ ሁሴን ዒሳ



ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
@merkezuna
629 views13:10
Open / Comment