Get Mystery Box with random crypto!

🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺

Logo of telegram channel nesiha_ouserya — 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺
Logo of telegram channel nesiha_ouserya — 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺
Channel address: @nesiha_ouserya
Categories: Education
Language: English
Country: Ethiopia
Subscribers: 2.48K
Description from channel

ለስኬታማ ቤተሰብ - نحو الأسرة الناجحة
ቤታችንን ኢሰላማዊ በማድረግ ትዉልድን እናድን!
ስለ ቻናላችን ያሎትን ሀሳብና አስተያየት
በ @nesiha_ouserya_Bot ይላኩልን!
እናመሰግናለን!
@nesiha_ouserya

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages 5

2022-02-05 17:35:50
121 views14:35
Open / Comment
2022-02-04 06:45:03 ሴቶች ለሴቶች የሙሀደራ ፕሮግራም

የተለመደው ወርሃዊ የሙሀደራ ፕሮግራማችን በአላህ ፈቃድ፦

የመሰረቶች ሁሉ መሰረት የሆነውን አላህን ስለማወቅ እና

አሁን ላይ ብዙዎቻችን ዝንጉ የሆንበትና ሴት እህቶቻችን ለጉዳት የተዳረጉበት የሆነውን ጉዳይ የምንመካከርበት መድረክ ይሆናል።

ተባብረን የተሻለ ማንነት በመፍጠር ትውልዱን እንታደገው።

እሁድ ጥር 29፣2014

ከጠዋቱ 3:00-6:30

ቀጠሮአችን በዳሩል ሀዲስ ይሁን።
(የቦታ ለውጡን አስተውሉ)
አድራሻ፦
18 ማዞሪያ አካባቢ ከቀድሞ አልአፊያ ት/ቤት አጠገብ

መልእክቱን ለእህቶች በማድረስ የበኩላችንን ሀላፊነት እንወጣ!

https://t.me/darulhadis18
353 views03:45
Open / Comment
2022-02-03 22:37:46 በልጆች ላይ ያንዣበበ ከባድ አደጋ!

ያለንበት ዘመን ልጆች በእጃቸው ላይ ባሉ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሌት ተቀን በሚያዩዋቸው የቴሌቪዥን ቻናሎች፣ በግልፅና ስውር መርዛቸውን በሚያሰራጩ ካርቶን ፊልሞች ምክንያት ስነምግባራቸው፣ እምነታቸው በአደገኛ ሁኔታ ተጽእኖ ላይ እየወደቀ ያለበት ነው።

ታዲያ ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው ማነው?

በፍፁም ታማኝነትና በሐቀኝነት ወደ ራሳችን መመለስ ይገባናል! ይህን ጥያቄ ሁላችንም ራሳችንን መጠየቅ ግድ ይለናል!

ተጠያቂው እኔ! አንተ! አንቺ! እኛ ሁላችንም! ካልሆን ማን ሊሆን ነው???

ባለንበት ተጨባጭ ነገራቶች በፍጥነት እየተለዋወጡ፣ ብልሹነትና ጥፋት እንደ ሰደድ እሳት ከአፅናፍ አፅናፍ እየተስፋፋ ፤ ሸይጣንና ጋሻ ጃግሬዎቹ የአላህ አደራ የሆኑ ልጆቻችንን የጥፋት ማጥ ውስጥ ለመጨመር ባለ በሌለ ኃይላቸው እየተጋጋጡ የሚገኙበት ነው። ይህንን አደጋ ልብ ብለን ልናስተውል፤ ዓይናችንን ከፈት አድርገን ልንመለከት ይገባል።

ሁላችንም ኃላፊነታችንን ለመወጣት ጥረት ልናደርግ ይገባል። እኛ ግዴታችንን መወጣት ካልቻልን ግን ዓይናችን እያየ የሰውና የጂን ሸይጣናት ልጆቻችንን ከእጃችን ይነጥቁናል። ለሚፈልጉት የጥፋት አላማ ይመለምሉልናል።

አላህ ልጆቻችንን ይጠብቅልን!

I ሂዳያ ተርቢያ I #ተግሳፅ I

https://t.me/HidayaTerbiya
495 views19:37
Open / Comment
2022-02-03 09:50:49 ★ታላቅ የሙሐደራ መርሓ ግብር★

ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ


☞"የአምልኮ መከታ እውነታና ብዥታ"

⇨እሁድ ጥር 29/2014 ከጠዋት 3:30 ጀምሮ

⇨አብነት በሚገኘው ዑመር ኢብኑል ኸጥ'ጣብ መስጂድ (26 መስጂድ)
595 views06:50
Open / Comment
2022-01-22 08:37:16
265 views05:37
Open / Comment
2022-01-20 21:44:08 ሴቶች ለሴቶች ወርሃዊ የሙሃደራ ፕሮግራም

ኑ! ስለራሳችንና ስለልጆቻችን በጋራ በመመካከር የተሻለ ማንነት እንፍጠር!

በአላህ ፈቃድ
ሙራቀበቱላህ እና

መልካም የልጆች አስተዳደግ(ክፍል 2)

የተመለከቱ ወሳኝ ርዕሶች የሚዳሰሱበት ድንቅ ፕሮግራም አዘጋጅተን የእናንተን ውድ እህቶቻችንን መምጣት በናፍቆት እየጠበቅን ነው!


ቅዳሜ ጥር 14፣2014

ከጠዋቱ 3:00-6:30

አድራሻ

ኢማሙ አህመድ መስጂድ
(አለም ባንክ)


መልእክቱን ሼር እናድርገው።

@darulhadis18
322 views18:44
Open / Comment
2022-01-06 11:35:00 ሴቶች ለሴቶች የሙሀደራ ፕሮግራም

ሙራቀበቱላህ!

የአላህ ፍራቻ "ተቅዋ" ን ለመላበስ እና ኢማንን ለማበልፀግ ከሚያግዙ ነገሮች አንዱ ሲሆን እሱም አላህ እንደሚቆጣጠረንና የምንሰራውን ስራ ሁሉ እንደሚመለከት ማሰብ ነው።

በዚህና በሌሎች ርእሶች ዙሪያ ለመተዋወስና በአላህ ፈቃድ የተሻለ ማንነት ለመፍጠር

እሁድ ጥር 1፣2014

ከጠዋቱ 3:00-6:30

ቀጠሮአችን በዳሩል ሀዲስ ይሁን።

አድራሻ፦

አባጂፋር መስጂድ አጠገብ የቀድሞ መርየም መድረሳ።

መልእክቱን ለእህቶች በማድረስ የበኩላችንን ሀላፊነት እንወጣ!

https://t.me/darulhadis18
378 views08:35
Open / Comment
2021-12-24 10:45:36 ሳምንታዊ የቅዳሜ የዲን ትምህርት ፕሮግራም ለሴቶች

ታላቅ የምስራች በስራ እና በትምህርት ምክንያት በመደበኛ ቀን የዲን ትምህርት ለመማር ላልተመቻችሁ እህቶች

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ዳሩል ሀዲስ ቤተል ቅርንጫፍ ከታች በተገለፁት ሁለት ደረጃዎች ዘወትር ቅዳሜ ጠዋት ሳምንታዊ የዲን ኮርስ ለመጀመር ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል።

⓵ አንደኛ ደረጃ (ለጀማሪዎች)

የሚቀሩ ኪታቦች፦
☞ ዐቂዳ
ኡሱሉ ሰላሳ

☞ ሀዲስ
አርበዑነ- ነወዊያ

☞ ተርቢያ
ተውጂሃት

⓶ ሁለተኛ ደረጃ
የሚቀሩ ኪታቦች
☞ ዐቂዳ
ኪታቡ ተውሂድ
(ሸይኽ ሙሀመድ አ/ወሃብ)

ፊቅህ
መንሃጁ-ሳሊኪን

ተርቢያ
ኡምደቱል-መርኣ

የተማሪዎች የቅበላ መስፈርት

እድሜ ከ 12 አመት በላይ የሆነች
የትምህርት ሰዐት ከ3:00-6:30

የምዝገባ ጊዜ፦ከዛሬ ጀምሮ ከታች ባሉት ስልክ ቁጥሮች በመደወል መመዝገብ ትችላላችሁ።

የምዝገባ ቦታ፦ ቤተል አደባባይ ንግድ ባንክ ያለበት ህንፃ 4ኛ ፎቅ

ትምህርቱ የሚጀመረው በአላህ ፈቃድ ቀጣይ ቅዳሜ ታህሳስ 22፣2014 ይሆናል።

ለበለጠ መረጃ፦

911062499
911692377

መልእክቱን ሼር በማድረግ ከአጅሩ እንቋደስ!

#ዳሩል ሀዲስ
@darulhadis18
338 views07:45
Open / Comment
2021-12-24 10:10:10 ሴቶች ለሴቶች የሙሃደራ ፕሮግራም

ኑ! ስለራሳችንና ስለልጆቻችን በጋራ በመመካከር የተሻለ ማንነት እንፍጠር!

በአላህ ፈቃድ
ኢልም እና
መልካም የልጆች አስተዳደግን

የተመለከቱ ወሳኝ ርዕሶች የሚዳሰሱበት ድንቅ ፕሮግራም አዘጋጅተን የእናንተን ውድ እህቶቻችንን መምጣት በናፍቆት እየጠበቅን ነው!


ቅዳሜ ታህሳስ 16፣2014

ከጠዋቱ 3:00-6:30

አድራሻ

ኢማሙ አህመድ መስጂድ
(አለም ባንክ)

እንዳታቀሩ ሳይሆን እንዳታረፍዱ ነው የምንላችሁ!

ይህን የመሰለ ዜና ሰምቶ ዝም ማለት ንፉግነት ነው!
መልእክቱን ሼር እናድርገው።

@darulhadis18
359 views07:10
Open / Comment
2021-12-11 11:20:38
576 views08:20
Open / Comment