Get Mystery Box with random crypto!

🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺

Logo of telegram channel nesiha_ouserya — 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺
Logo of telegram channel nesiha_ouserya — 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺
Channel address: @nesiha_ouserya
Categories: Education
Language: English
Country: Ethiopia
Subscribers: 2.48K
Description from channel

ለስኬታማ ቤተሰብ - نحو الأسرة الناجحة
ቤታችንን ኢሰላማዊ በማድረግ ትዉልድን እናድን!
ስለ ቻናላችን ያሎትን ሀሳብና አስተያየት
በ @nesiha_ouserya_Bot ይላኩልን!
እናመሰግናለን!
@nesiha_ouserya

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages 4

2022-03-02 20:48:01 የሸዕባን ወር ፆም
~ ~ ~
እናታችን ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ ብላለች፡-
“ነብዩ ﷺ ከረመዳን በስተቀር ሙሉ የፆሙት ወር የለም። እንደ ሸዕባን ፆም ያበዙበት አላየሁም።” [ቡኻሪና ሙስሊም]

በሌላ የሙስሊም ዘገባ ደግሞ “ሸዕባንን ጥቂት ሲቀር እንዳለ ይፆሙት ነበር” ብላለች።
215 views17:48
Open / Comment
2022-02-23 23:03:39 "የሒጃብ ቀን" ወይስ "የፈሳድ ቀን"?!

ኢስላም ራሱን የቻሉ ህልውናዎች ያሉት መሰረቱ የፀና በየግዜያቱ ልማድና ዘዬ በተከታዮቹ ከፍታና ዝቅታ ሙቀትና ቅሬታ የሚቀያየር እምነት አይደለም። መሰረታዊ ነጥቦቹን በየግዜው ብቅ ከሚሉ የከሀዲያን በቀል ተፅዕኖዎች ለመሸሽ በሚል ፈሊጥና ከዘመኑ ጋር እንራመድን ባዘለ ሙግት ፅኑ እሳቤው የሚገፈፍና በሸውራራ ምልከታና በዝንባሌዎች ማዕቀፍ የሚኮላሽ አይሆንም።

እርግጥ ነው ዘመናዊነትን ከኢስላም ጋር በማይጋጩ ነገሮች አጣጥመን ልንጠቀምበት ከዘመኑ ጋር ልንራመድ ህይወታችንን ልናቀልበትና ልናቀናበት ይገባል። ነገር ግን ኢስላምን ዘመናዊ እናድርገው ብለን ወደ ገደል የምንጎትተው እምነት ሊሆን በፍፁም አይችልም። አምላካችን አሏህ ይህን እምነት የደነገገውና የሰዎች መመሪያ ያደረገው እስከ ምፅዐት ቀን እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል። ዘመናቶች በተሻገሩ ቁጥር ኢስላምን በታወረ ልቦናችን የምንዘምትበት በአጠረ እውቀታችን የምንጠራራበት እምነት አይደለም። ፋይሉ ከ1400 አመታት በፊት ተዘግቷል።

የምዕራባዊያን ተፅዕኖ ያስበረገጋቸው በኢስላም ቀና ማለት ያቃታቸው በስሜት አለንጋ የተገረፉ ስብዕናዎች ኢስላምን እናዘምነው በሚል ወይም ቅቡልነቱን እናግነነው በሚል ሸውራራ እይታ ማህበረሰቡን ከትክክለኛው የኢስላም እሳቤ ወደ ወረደው አዘቅት እያወረዱት የቆመበትን ምንጣፍ እየጎተቱን ይገኛሉ። እውነት ነው አላህ እንዲህ ማለቱ ፦

"አይሁዶችና ክርስቲያኖችም ሀይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ካንተ ፈፅሞ አይወዱም " አል-በቀራ 120

ከዛሬ ነገ እየከነፈ ሙስሊሟ ሴት እየተንሸራተተች የት ነው ያለችው? አንዱን ሲያስጥሏት እየወረደች አንዱን እያነሳች በመጨረሻም የእነሱን መንገድ በምልአተ ልቦናዋ ኮቴ በኮቴ እየተከተለች ትጓዝ ይዛለች። መታገል የመጀመሪያው ፈተና ላይ መሆኑን አላወቀችም። ድንበርህን አሳልፈህ ከሰጠህ ቡኃላ በሜዳህ ለሚጫወቱ አካላት መጫወቻ ትሆናለህ። አመቱን ሙሉ የሒጃብ ቀን ብለን ብናከብር የሒጃብን ልቅና በዚህ መንገድ ልናስጠብቀው በፍፁም አንችልም። ይባስ ብሎም ይህ አካሄድ ሴቶችን ከትክክለኛው የሒጃብ መፍሁምና ጭብጥ እያራቃቸው መጥቷል። ለዚህም ነው በየቦታው የቻይና ሱሪና ጠባብ ቀሚስ የታጠቁ ሙልጭልጭ ያለ ሂጃብ የለበሱ በጥቅሉ ማንነታቸው ግራ የገባቸው ሴቶች እንደ አሸን የፈሉት። ሀይ ባይ አጥተው ነውራችን የሆኑት። ግዜው በገፋ ቁጥር ነገሩም እየከፋ አበረታችና አጨብጫቢው እየፋፋ ሴቶችንም ለሐራም ማደኑም እየገፋ መጥቷል።

ፀጉራቸውን እንኳን በተገቢው መልኩ ያልሸፈኑ ብጥስጣሽ ጨርቆችን ከአናታቸው ላይ ጣል ያደረጉ በሰፋፊ ልብሶች መሸፈን ያለበት አካላቸው በጠባብና ባለ ወገብ ማሰሪያ ቀሚሶች ያሰሩና አካላቸውን የማይሰትሩ ቀሚሶች ያጠለቁ ከዚህ ሲከፋም ጠባብ ሱሪዎች ታጥቀው ብቅ የሚሉ እህቶችን ሰብስቦ "የሒጃብ ቀን" እያሉ ማጃጃል ትልቅ ውርደት ነው። የንፁህ ሴት ልጅ ክብርና መገለጫ የሆነውን ጌታዋን የምታመልክበትን ዒባዳ የሒጃብ fashion show በሚል ቀልድና ሞኝነት በወንዶች መንጋ መሀል ሲያመላልሷት እንዲሁም ቧልትና ዛዛታ በበዛበት መድረክ ላይ ወንድና ሴት ፍጥረቶች ያለ ግርዶሽ አፋጠው በሜክአፕ፣ በሊፒስቲክና .....የተበከለ ፊት በቅጡ ያልተሰተረ ማንነት የተከማቸበት ፕሮግራም እንዴት የሒጃብ ቀን ተብሎ ይሰየማል? በነሺዳ ስም የሚቅለሰለሱ ፓንክ ቁርጥ ሙነሺዶች የሚጣዱበት አብዛኞዎቹ ታዳሚያን ትክክለኛውን የሒጃብ መስፈርት ያላሟላ ሒጃብ ለብሰው የሚታደሙበት ፕሮግራም እንዴት የሒጃብ ቀን መሰናዶ ሊሆን ይችላል? በዚህ የፈተና ነፋስ በከፍተኛ ፍጥነት በሚነፍስበት ዘመን እሳትና ጭድን አቀራርቦ ደህና ምክር እንኳን መስጠት ከባድ መፍሰዳ ያስከትላል በሚባልበት እውነታ ከዛዛታው መሀል ምን ሊፈጠር እንደሚችል አስቡት? ምን አልባት ፕሮግራሙን ኢስላማዊ ለማስመሰል አንዲት ሙሐደራ ቢጤ ነገር ጣል ሊያደርጉባት ይቻል ይሆናል ይህም መሰረቱ በወደቀ ቤት ላይ ሚስማር እንደመምታት ነው።

እውነታውን ስንመለከት "ዓለም አቀፍ የሂጃብ ቀን" ተብሎ በፌብራሪ 1 የሚከበረውን በዓል አንዲት በአሜሪካ የምትኖር ትውልዷ ባንግላዲሽ ዜግነቷ አሜሪካዊ የሆነች በ 11 አመቷ ወደ ሀገረ አሜሪካ ከቤተሰቦቿ ጋር ተሰዳ የምትኖር እንስት በሂጃቧ ምክንያት በሚደርስባት ጫና ያስጀመረችው የሚዲያ ዘመቻ መሆኑ ነው። ማንም ቢሆን መልካም አላማን አንግቦ አንዳች ነገርን ይዞ በዲን ስም ከመነሳቱ በፊት በሸሪዓ ሚዛን ተለክቶና ተገምግሞ የኢስላም ሊቃውንቶችን ትክክለኛ ይሁኝታ ቁርኣንና ሐዲሥን አስደግፎ መስለሓና መፍሰዳው ታይቶ መሆን አለበት። የቢድዓ ጉዳይ ከሆነ ግን ምንም አይነት የቅቡልነት መንገድ አይኖረውም።

ሒጃብ አላህ ለሴቶች የደነገገው ጥበባዊና ፍትሓዊ የሆነ ሸሪዓዊ ልባስ ነው። አንዲት ሴት የጥብቅነትና የጨዋነት ምልክት ነው። በዚህ ርዕስ ላይ ሁሉም ሙስሊም ማህበረሰብ በተለይ የኢስላም ልሂቃንና ሰባኪያን ሴቶችን ስለ ትክክለኛው ሒጃብ ሊያስተምሩ የመዳኛ መንገድ መሆኑን ሊጠቁሙ የክብሯ፣ የሀሴቷና የልቅናዋ ሰበብ መሆኑን ሊያስገነዝቧት ይገባል።

ነገር ግን አመት ጠብቆ የሒጃብ ቀን ብሎ ማክበርና ከዚህም የባሰው ደግሞ የዛን እለት ብቻ ሒጃብ የሚለበስበትና የተለያዩ እምነት ተከታዮችም እንደ ተራ ፌስቲቫል ሒጃብ ያሉትን ጨርቅ ጣል አድርገው ሲቀልዱ በተነሱት ፎቶ ሶሻል ሚዲያዎችን ሲያጨናንቁ ማየት ከባድ የሆነ ቢድዓና በውስጡም ተዘርዝረው የማያልቁ መፍሰዳዎችን ያካተተ ነው። ይህን ተግባር በፅኑ የሚኮኑንበት ሌላው ምክንያት በተለያዩ ቀናት እንዳሻቸው ክብረ በዓል ከሚያሰናዱ ከሀዲያን ጋር መመሳሰል መንገዳቸውንም መከተል ስላለበት ነው። ኢስላምም ከተደነገጉለት በዓላት ውጪ የተለየ ክብር በዓላትን በየትኛውም መልኩ አያስተናግድም።

ይህን መሰል ነገሮችን የሚያከብሩ ሰዎች በብዛት መስለሓ አለው በሚል ሙግት መሆኑ እርግጥ ነው። ይህን ሲሉ መሰለሓና መፍሰዳን ሚዛን ላይ አስቀምጦ ለመገምገም የሚያስችል የሸሪዓ እውቀትና የቀደመ ኢስላማዊ ልቀትና ምጥቀት ላይ ያሉ ሰዎች አለመሆናቸው ደግሞ ያስተዛዝባል። መፍሰዳና መስለሓን በሸሪዓ ምልከታ፣ በረቀቀ ግምገማና እይታ አላህን ፈሪ በሆነ ልቦና ተመልክተው ብይን መስጠት ያለባቸው በዘርፉ የተካኑ የኢስላም ልሂቃን ብቻ ናቸው። ከዚህ ውጪ በዲን ስም ቢዝነሱን እያጧጧፈ መስለሓ አለው ለሚልሽ ባተሌ ጆሮ አትስጪ ማመዛዘን የሚችለውን ዐቅልሽ አታከራይው ይልቁንም ለዲንሽና ለክብርሽ ዋጋ ስጪ። የመፍሰዳው ብዛት አለች የሚሏትን ጭላንጭል መስለሓ ላይ ቢቆለል አፍነው ይገሏት ነበር። ይህ የነሺዳና ዳንኪራ ጭብጨባ፣ በወንዶች መሀል በፋሺን ሾው ስም ያለ ዕፍረት የሒጃብን መስፈርት በማያሟላ በተጋጌጠና በተቆራረጠ የጨርቅ ቅጥልጣይ ልብስ መመላለስና መሰባበር፣ ኢኽቲላጥና ዛዛታ ሌሎችም ሙንከራቶች እውነት ወደ አላህ የሚያቃርበን ዒባዳ ነውን? በፍፁም!!!

#yes_to_hijab_no_to_hijab_day

ዐብዱረዛቅ አል-ሐበሺይ
https://t.me/abdurezaq27
131 views20:03
Open / Comment
2022-02-22 20:52:44 ልጆችዎን የሚያስደስቱበትና ውስጣቸውን የሚገነቡበት ድንቅ ቃላት!

እወድሃለሁ I እውድሻለሁ
አምንሃለሁ I አምንሻለሁ
አንተ/ቺ በጣም ውድ የአላህ ስጦታ ነህ/ሽ
አስተያየትህን/ሽን አከብራለሁ
አንተ/ቺ ድንቅ ልጅ ነህ/ሽ
አንተን/ቺን ማዳመጥ ደስ ይለኛል
ና/ነይ ላቅፍህ/ሽ
ምን ማድረግ ትወዳለህ/ጃለሽ?
በውጤትህ/ሽ ረክቻለሁ
ድካምህ/ሽ እረዳለሁ
ስላየሁህ/ሽ ደስ ብሎኛል

ምርጥ ወላጅ I #ለወላጆች I

I #ሂዳያ #Hidaya #ተርቢያ #Terbiya I

https://t.me/HidayaTerbiya
195 views17:52
Open / Comment
2022-02-19 10:55:22 የፕሮግራም ለውጥ

አንዳንድ የግል እንዲሁም የመንግስት ትምህርት ቤቶች የሴሚስተር እረፍት ጊዜ ቀድሞ ከያዝነው ፕርግራም ጋ ባለመገጣጠሙ የታዳጊዎች ኮርስ መስጫ ጊዜው (የሁሉም ጣቢያ)ወደ ቀጣዩ ሳምንት ማለትም የካቲት 21 መሸጋገሩን ከአክብሮት ጋ እናሳውቃለን።

መልእክቱን አስተላልፉት

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
@darulhadis18
438 views07:55
Open / Comment
2022-02-17 19:28:44 ቤተልና አካባቢዋ ለሚገኙ ሴት ታዳጊዎች አማራጭ የኮርስ ጣቢያ

ቤተል 30 ሜትር ላይ የሚገኘው አልአፊያ ት/ቤት

ለበለጠ መረጃ
+251911062499 ይደውሉ

@darulhadis18
307 views16:28
Open / Comment
2022-02-17 19:15:56 ሴቶች ለሴቶች ወርሃዊ የሙሃደራ ፕሮግራም

ኑ! ስለራሳችንና ሰለዲናችን በጋራ በመመካከር የተሻለ ማንነት እንፍጠር!

በአላህ ፈቃድ ስራዎቻችን አላህ ዘንድ ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ ማሟላት ያለብን 2 መስፈርቶች

ኢኽላስ (ኒያን ማጥራት)እና

ሙታበአቱ ረሱል
(መልእክተኛውን አለይሂ ሶላቱ ወሰላም መከተል)

የሚሉ ርእሶች የሚዳሰሱበት ድንቅ ፕሮግራም አዘጋጅተን የእናንተን ውድ እህቶቻችንን መምጣት በናፍቆት እየጠበቅን ነው!

ቅዳሜ የካቲት 12፣2014

ከጠዋቱ 3:00-6:30

አድራሻ

አለም ባንክ የሚገኘው ኢማሙ አህመድ (አንፎ ሜዳ) መስጂድ


መልእክቱን ሼር እናድርገው።

@darulhadis18
209 views16:15
Open / Comment
2022-02-14 20:11:38
ታዳጊዎች የመጪው ጊዜ የኢስላም ተረካቢዎች!

ውድ ለሆኑት ትውልዶች! ለታዳጊ ተማሪዎች የተዘጋጀ ለ 5 ቀናት የሚቆይ ድንቅ ኮርስ!

በአላህ ፈቃድ፦
ከዕውቀቶች ሁሉ ታላቅ ስለሆነው ዕውቀት የሚማሩበት!
መልካም ስነ ምግባር የሚላበሱበትን ቁልፍ የሚያገኙበት!
የኢስላምን ውበት ተረድተው በእምነታቸው የሚኮሩበት!
አላህን በማውሳት ልዕልና ከፍ የሚሉበት!

ኮርሱ የሚሰጠው ለሁለቱም ጾታዎች በሁለት ደረጃዎች ተከፍሎ ሲሆን፦

ደረጃ 1፡ ዕድሜያቸው ከ12-14
ደረጃ 2፡ ዕድሜያቸው ከ15-18

ቀን ከየካቲት 14 - 18፣2014

ጠዋት ከ3:00-6:30
አድራሻ
ለሴቶች፦18 ማዞሪያ አካባቢ ከቀድሞ አልአፊያ ት/ቤት አጠገብ
ለወንዶች፦ቤተል 40ሜትር የሚገኘው አልአፊያ ት/ቤት

ለመመዝገብ፦
ለሴቶች
0967671891
ወይም 0904366666
ለወንዶች
093 048 4284 ይደውሉ

ወላጆች ልጆቻችሁን በመላክ ኃላፊነታችሁን ተወጡ!

እኛም መልዕክቱን በማስተላለፍ ሀላፊነታችንን እንወጣ!

https://t.me/darulhadis18
197 views17:11
Open / Comment
2022-02-13 20:41:02 ተግባራዊ ትምህርት…

ውድ አባት ሆይ! ለልጅህ ምርጥ አባትና መልካም አርዓያ መሆን ከፈለግክ፤ ለልጅህ ይህን አድርግ ይህንን አታድርግ የሚሉ ትዕዛዛትን ብቻ ከማስተላለፍ ይልቅ በተግባራዊ ምሳሌ ለማስረዳት ሞክር።

ለምሳሌ የመተባበርን ጥቅም ልታስተምረው ከፈለግክ በቤት ውስጥ አንዳንድ ስራዎችን አንተ መስራት ጀምርና ልጅህ እንዲረዳህ ጠይቀው። ባለቤትህ እገዛህን ፈልጋ ትብብር ስትጠይቅህ ቀና ምላሽ በመስጠት እድሜ ልኩን የማይረሳውን ትምህርት ስጠው።

ምርጥ አባት I #ለአባቶች I

I #ሂዳያ #Hidaya #ተርቢያ #Terbiya I

https://t.me/HidayaTerbiya
376 views17:41
Open / Comment
2022-02-10 20:47:00 ከነብዩላህ ኑህ (የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ታሪክ ውስጥ ከምንወስዳቸው እጅግ ብዙ ከሆኑ ጠቃሚ ቁም ነገሮች መካከል አንዱ ተርቢያዊ ትምህርት ነው።

እርሱም

ልጆቻችንን በተርቢያ በማሳደግ ረገድ የቱንም ያህል ጉጉ ብንሆንና ጥረት ብናደርግም ስለ ውጤቱ ግን ዋስትና ሊኖረን እንደማንችል ማወቅ ነው።

ሂዳያ (ለመልካም ነገር መምራትና እንዲቀበሉ ማድረግ) በአላህ እጅ ብቻ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል።

ስለዚህ ልጆችን በኢስላማዊ ተርቢያ ለማሳደግ ጥረት እንደምናደርገው ሁሉ አላህ ልጆቻችንን ለበጎ ነገር እንዲመራልን ከመወለዳቸው በፊትም ሆነ ከተወለዱ በኋላ ደጋግመን አላህን መለመን ዱዓ ማድረግ ይገባናል።

ምርጥ ወላጅ I #ወላጆች I

I #ሂዳያ #Hidaya #ተርቢያ #Terbiya I

https://t.me/HidayaTerbiya
421 views17:47
Open / Comment
2022-02-08 21:37:18 ለሰላት ብላ የጀመረችውን ስራ የምታቆም እናት ያላቸው ልጆቿ የሰላትን ዋጋ በደንብ ይገነዘባሉ።

ምርጥ እናት I #ለእናቶች I

I #ሂዳያ #Hidaya #ተርቢያ #Terbiya I

https://t.me/HidayaTerbiya
351 views18:37
Open / Comment