Get Mystery Box with random crypto!

🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺

Logo of telegram channel nesiha_ouserya — 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺
Logo of telegram channel nesiha_ouserya — 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺
Channel address: @nesiha_ouserya
Categories: Education
Language: English
Country: Ethiopia
Subscribers: 2.48K
Description from channel

ለስኬታማ ቤተሰብ - نحو الأسرة الناجحة
ቤታችንን ኢሰላማዊ በማድረግ ትዉልድን እናድን!
ስለ ቻናላችን ያሎትን ሀሳብና አስተያየት
በ @nesiha_ouserya_Bot ይላኩልን!
እናመሰግናለን!
@nesiha_ouserya

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages 6

2021-12-06 20:56:00 ልዩ ፕሮግራም ለሴት ተማሪዎች!

ኢስላም ለሴቶች ላቅ ያለ ስፍራ ችሯል! ለወጣቶች ደግሞ ልዪ ትኩረትን ሰጥቷል! ሁለቱ አንድ ላይ ሲጣመሩ ደግሞ ደረጃው እጅግ ከፍ ያለ ይሆናል!

ኑ! ስለ ሁለቱም በጋራ እንመካከር የተሻለ ማንነት እንፍጠር!

በአላህ ፈቃድ ሴትነትና ወጣትነትን የሚመለከቱ የተለያዩ አንገብጋቢና ወሳኝ ርዕሶች የሚዳሰሱበት ድንቅ ፕሮግራም አዘጋጅተን የእናንተን ውድ እህቶቻችንን መምጣት በናፍቆት እየጠበቅን ነው!

መቼ ነው ታዲያ?

ከረቡዕ ህዳር 29 እስከ ጁሙዓ ታህሳስ 1 2014

ከጠዋቱ 3:00-6:30

አድራሻስ፦

አባጂፋር መስጂድ አጠገብ የቀድሞ መርየም መድረሳ።

እንዳታቀሩ ሳይሆን እንዳታረፍዱ ነው የምንላችሁ!

ይህን የመሰለ ዜና ሰምቶ ዝም ማለታ ንፉግነት ነው! በሉ ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ ንገሯቸውና ይህን ምርጥ ፕሮግራም እንዲሳተፉ ጋብዟቸው!

ትልቅ ስጦታ እንደሰጣችኋቸው አትጠራጠሩ!

@darulhadis18
190 views17:56
Open / Comment
2021-11-28 12:19:15 https://t.me/darutewhidweqf
88 views09:19
Open / Comment
2021-10-23 07:02:55 ሳምንታዊ የቅዳሜ የዲን ትምህርት ፕሮግራም ለሴቶች (ዳሩል ሐዲስ)

ታላቅ የምስራች በስራ እና በትምህርት ምክንያት በመደበኛ ቀን የዲን ትምህርት ለመማር ላልተመቻችሁ እህቶች

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ዳሩል ሀዲስ የዓረብኛ ቋንቋ እና የሸሪዓዊ ትምህርቶች ኢንስቲትዩት፤ ከታች በተገለፁት ሁለት ደረጃዎች ዘወትር ቅዳሜ በሁለት ፈረቃ ጠዋት እና ከሰአት የሚሰጠውን ሳምንታዊ የዲን ኮርስ የጀመረ በመሆኑ ያልተመዘገባችሁ እህቶች በቀረን ውስን ቦታ ላይ እንድትመዘገቡ ያሳውቃል።

⓵ አንደኛ ደረጃ (ለጀማሪዎች)

የሚቀሩ ኪታቦች፦
☞ ዐቂዳ
ኡሱሉ ሰላሳ
ኹዝ ዓቂደተክ

☞ ሀዲስ
አርበዑነ- ነወዊያ

☞ ተርቢያ
ተውጂሃት

⓶ ሁለተኛ ደረጃ
የሚቀሩ ኪታቦች
☞ ዐቂዳ
ኪታቡ ተውሂድ
(ሸይኽ ሙሀመድ አ/ወሃብ)

ፊቅህ
ሚንሃጁ ሳሊኪን

ተርቢያ
ኡምደቱል መርኣ

የተማሪዎች የቅበላ መስፈርት
እድሜ ከ 15 አመት በላይ የሆነች
ትምህርቱን ለ1 አመት በሳምንት 1 ቀን ቅዳሜ
ጠዋት ከ3:00-6:30 ወይም
ከሰአት ከ 7፡30 እስከ 10፡00 ድረስ ለመከታተል ዝግጁ መሆን
የመርከዙን ደንብና ስርዓት አክብሮ ለመማር ዝግጁ መሆን

የመማሪያ ቦታ፦ ከጦር ሀይሎች ከፍ ብሎ የሚገኘው አባጅፋር መስጂድ አካባቢ
ከሴቶች መግቢያ ፊት ለፊት (የቀድሞው መርየም መድረሳ)

ለበለጠ መረጃ፦
በስልክ ቁጥር +251967671891
ወይም +251904366666ይደውሉ።

መልእክቱን ሼር በማድረግ ከአጅሩ እንቋደስ
ዳሩል ሀዲስ የዓረብኛ ቋንቋ እና የሸሪዓዊ ትምህርቶች ኢንስቲትዩት
@darulhadis18
554 views04:02
Open / Comment
2021-10-16 21:48:02
747 views18:48
Open / Comment
2021-10-06 18:08:55
"قُل لّلِْمُؤْمِنيِنَ يَغُضُّوا مِنْ أبْصَـٰرِهِمْ وَيَحْفَظُوا فُرُوجَهُمْ ذلِكَ أزْكَىٰ لهم"

معظم البُيوت لا تخلو من خلافاتٍ واختلافاتٍ بين الزَّوج وزوجته، وتكون الخلافات كالسَّحابة العابرة التي تمرُّ على عَجَل،

◄لكنْ لو تجاوَزَت الخلافاتُ الزَّوجيَّة الحدَّ، فإنها ستؤثِّر على كيان الأسرة، بل قد تهدِم البيت في نهاية المطاف، تسأل اللّٰه العافية والسلامة،

◄ومن أعظم أسباب هَدْم البُيوت سببٌ قبيح جدّاً، يمارسُه بعض الرِّجال وقِلِّةٌ قليلةٌ من النساء،

◄ولكنْ لابدَّ من تسليط الضوء عليه لخطورته وسُرعة هدمه للبُيوت،

ألا وأنَّ هذا السببَ هو
الخيانةُ الزَّوجية،


◄ والكلام في هذا الموضوع مؤلمٌ للغاية، فبعض الأزواج وللأسف الشديد يختار طريقَ الحرام ويقدِّمُه ويفضِّلُه على أسرته وأبنائه، فهو على أتمِّ استعداد للتضحية ببيته مقابلَ لذَّةٍ محرَّمةٍ، وركضٍ وراء ساقطةٍ غرَّتْه أوقعتْه في مصيدتها، بل قد ينتقل من امرأةٍ إلى أخرى، تاركاً زوجته تعاني قهرٍ وألمٍ لا يعلم به إلا اللّٓه،

◄فلو طلَبتْ منه تركَ هذا الطريق لَما استجاب، ولو عرضتْ عليه أن يعدِّدَ ليرجِع إلى رُشده وصوابه لَما استجاب أيضاً، فقد تعوَّد على الحرام وألِفه، من دون أن يلتفتَ إلى وقوعه في كبيرةٍ من كبائر الذُّنوب، وسلوكِه طريقٍ قد يُفقِدُه صحَّتَه وبيتَه وأبناءه،

◄فكم جرَّتْ هذه الخيانات الزَّوجية من أمراضٍ وعقدٍ نفسيَّةٍابتُلي بها الزٌَوج الخائن وقد ينقلُها إلى زوجته وأبنائه،

◄وهنا كارثةٌ أخرى، إنَّ مِن أعظم أسباب ترفُّع الرَّجُل عن خيانة زوجته استشعارُ مراقبة اللّٰه تعالى، فربُّنا لا تخفَى عليه خافية، فمهما تخفى الرجل وظن أن زوجته لا تعرف عن مغامراته المحرمة شيئا، فليتذكر عظمةَ الخالق، وأنه سميعٌ بصيرٌ عليمٌ لا تخفى عليه خافية،

◄ولْيتذكَّر أيضاً أنَّ عندَه زوجةً وبناتٍ وأخَوات، فهل يرضى عليهِنَّ ما يقومُ بفعله مع الأُخْريات،

وهل يرضَى إذا تزوَّجَت ابنتُه أنْ تُبتلى بزوجٍ يسيرُ على نفْس الطريق

◄إن من الأزواج من يبرِّرُ لنفسه الوقوعَ في الخطأ بحُججٍ واهيةٍ جدّاً،
فبعضهم يحتجُّ بأنَّ زوجتَه مقصِّرةٌ أو غيرُ جميلةٍ،
أو تزوَّجَها مِن غيرِ اقتناع!
فأصبحَ يبحثُ عن شريكةٍ يحبُّها! وغيرِ ذلك من الأعذار الواهية، التي يخدع بها الخائن نفسه، ليبرِّر ذنباً شنيعاً، يستحقُّ به غضب الله،

فخطأ الزوجة لا يبرِّر مطلقاً الوقوعَ في الخطأ،

وهل تَقبَلُ إذا وقعْتَ أنت في الخطأ أنْ تعالجَ زوجتُك الخطأَ بخيانةٍ زوجيَّة

◄وليست الخيانة مقصورةً على مصيبةٍ واحدةٍ يقوم بها الزَّوج، فبعضُهم لا يغُضُّ بصرَه، فعينُه تتحرَّك يميناً وشِمالاً بجرأةٍ ووقاحةٍ، وأمام زوجته أيضاً، أو يشاهدُ أفلاماً تعِجُّ بالفجور والعياذ باللّٰه،

فهلاَّ طبَّق قولَ الله تعالى:
(قُل لّلِْمُؤْمِنيِنَ يَغُضُّوا مِنْ أبْصَـٰرِهِمْ وَيَحْفَظُوا فُرُوجَهُمْ ذلِكَ أزْكَىٰ لهم).


[كلمات للأسرة المسلمة عبدالله الكمالي ص70_72]
619 views15:08
Open / Comment
2021-10-05 18:19:49
አልሐምዱሊላህ

" የመልካም ሚስት ስብዕና"
መጽሐፍ ዛሬ ገበያ ላይ ዋለ…

በሚከተሉት ኢስላማዊ መጽሐፍት መሸጫዎች ማግኘት ትችላላችሁ፦

አትተውባ
አል ቁድስ
ያሲን
ቤተል ተቅዋ መስጂድ በር ላይ (ኩበራ)
888 viewsedited  15:19
Open / Comment
2021-10-04 13:37:22 አልሀበሺ እውነታውን ሲያምን!!

#መውሊድ

መውሊድን የማክበር ሀሳብ ከክርስቲያኖች የገና በአል ተኮርጆ የመጣ መሆኑን ላለመቀበል ሀሰን ታጁ እና መሰሎቹ ቢሞግቱም አብደላህ አልሀበሺ በተቃራኒው እውነታውን አምኗል፤

☞ የ ‘ኢዝሀሩል አቂደቲሱኒያህ’ የድምፅ ማብራሪያ ካሴት ቁ.9 የመጀመሪያው ክፍል ላይ የመውሊድን አጀማመር አስመልክቶ፤ መውሊድን ለመጀመሪያ ጊዜ ያከበረው የኢርቢሉ ንጉስ ሙዘፈር እንደሆነ እና አጀማመሩም ክርስቲያኖች የመሲህን ልደት ሲያከብሩ አይቶ ሙሀመድ ﷺ በዚህ አለም ብቅ በማለታቸው አላህን ሊያመሰግን እንደሆነ ያብራራል።

እኛም እውነታዉን በማመኑ እያመሰገነው ተከታዮቹን ነጥቦች እንጠቁማለን፤

1) መውሊድን በዓል አድርጎ ማክበር መልእክተኛው ﷺ ወደዚህ አለም በመምጣታቸው ለአላህ ምስጋና የማቅረቢያና ውዴታንም የመግለጫ መንገድ ከሆነ ከሰሀቦችና ታቢዒዮች ዘመን ጀምሮ የኖሩ ምርጥ የኢስላም ልጆች ሳያውቁት በ630 ዓ.ሒ የሞተው ንጉስ ተገለጠለትን?

2) በላጭ ትውልዶች የተባሉት ቀደምቶቹ ሰለፎች ይህንን መውሊድ ያላከበሩት፤ ክርስቲያኖችና አህባሾች የደረሱበትን መውሊድ አላህን የማመስገኛ መንገድ የመሆኑን እውነታ ማወቅ ተስኗቸው ነውን? ይህንን ካላችሁ ጥመታችሁ ግልፅ ወጣ አለያ ወደነሱ መንገድ ተመለሱ!!

3) ይህ የተምታታ ግንዛቤ መነሻ ያደረገውን ሀሳብ ስንመለለት፤ ክርስቲያኖች የኢሳን ልደት በማክበራቸው አላህን በማመስገን ከምርጦቹ የሰለፎች ትውልዶች መቅደማቸውን ያመላክታል።
ይህ ደግሞ ባጢል ነው!!

4) አልሐበሺ እና ተከታዮቹ ክርስቲያኖችን በመከተል ልደት ሲያከብሩ መልእክተኛው ﷺ በብዙ ሀዲሶች፤ በኢስላማዊ እንድንኮራ ማዘዛቸውና አይሁዶችና ክርስቲያኖችን አርአያ እንዳናደርግ አበክረው መምከራቸውን ለምን ዘነጉ? ሙስሊም ከካፈር ጋር መመሳሰል እንደሌለበት አያውቁምን??

መልዕክተኛው ﷺ እንዲህ ብለዋል፤

عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيّ، قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللّهِ صلى الله عليه وسلم "لَتَتّبِعُنّ سَنَنَ الّذِينَ مِنْ قَبْلِكُمْ. شِبْراً بِشِبْرٍ، وَذِرَاعاً بِذِرَاعٍ. حَتّىَ لَوْ دَخَلُوا فِي جُحْرِ ضَبَ لاَتّبَعْتُمُوهُمْ" قُلْنَا: يَا رَسُولَ اللّهِ آلْيَهُودُ وَالنّصَارَىَ؟ قَالَ "فَمَنْ؟".
[رواه البخارى ومسلم ].

አቢ ሰዒድ አልኹድሪይ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ አሉ፤ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ፤ «ከናንተ በስተፊት የነበሩትን (ህዝቦች) ፈለግ ስንዝር በስንዝር እርምጃ በእርምጃ ትከተላላችሁ። የተሳቢ እንስሳ ጉድጓድ እንኳ ቢገቡ ትከተሏቸዋላችሁ!»

የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ሆይ ይሁዶችንና ነሳራዎችን ነው ? «ሌላ ማንን ነው!» (እነሱን ነው እንጂ) አሉ።

ይህንን ነብያዊ ትንቢት ባንሰማ ኖሮ በሙዘፈር ድርጊት ተገርመን አናበቃም ነበር።

5) አላህ ዲናችንን የተሟላ አድርጎት ሳለ፤ ክርስቲያኖች ሰሩት ብለን በዲናችን የሌለን ነገር እንፈፅማለን??

(ٱلْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِى وَرَضِيتُ لَكُمُ ٱلْإِسْلَـٰمَ دِينًۭا ۚ فَمَنِ ٱضْطُرَّ فِى مَخْمَصَةٍ غَيْرَ مُتَجَانِفٍۢ لِّإِثْمٍۢ ۙ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌۭ رَّحِيمٌۭ) المائدة 3

«ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለእናተ ሞላሁላችሁ። ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ። ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ»
አልማኢዳህ 3

በእውነትም የዛኔ ዲን ያልነበረ አሁን ዲን ሊሆን አይችልም!!

አኹኩም አቡጁነይድ
ረቢኡልአወል 9 /1436 ዓ.ሒ

https://t.me/abujunaidposts
921 views10:37
Open / Comment
2021-10-03 14:20:21
542 views11:20
Open / Comment
2021-09-20 21:44:07
አዲስ መፅሐፍ በቅርብ ቀን

የመልካም ሚስት ስብዕና

አዘጋጅ ፕሮፌሰር ሸይኽ ዐብዱረዛቅ ቢን ዐብዱልሙሕሲን አል`በድር

ትርጉም ወንድም ሐይደር ኸድር ዐብደላህ
392 views18:44
Open / Comment
2021-09-20 12:09:25 “አላህ መልካም ለሻለት ሰው ዲኑን ያስገነዝበዋል”

ታላቅ የምስራች ለኢስላማዊ እውቀት ፈላጊ ሴቶች በሙሉ

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ዳሩል ሐዲሥ የሸሪዓ ትምህርቶችና የዐረብኛ ቋንቋ መማሪያ ኢንስቲትዩት ቤተል ቅርንጫፍ ለሴቶች ልዩ የዲን ኮርስ አዘጋጅቶ ይጠብቆታል።

የምዝገባ ጊዜ፦ከሰኞ መስከረም 10— ሀሙስ መስከረም 13 /2014
የመመዝገቢያ ሰዐት ከ3:30— 6:30

የምዝገባ ቦታ፦ ቤተል አደባባይ ንግድ ባንክ ያለበት ህንፃ 4ኛ ፎቅ

ለበለጠ መረጃ፦

ስልክ ቁጥር 0911692377
0911375952

ማሳሰቢያ፦
ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ ቀድመው ይመዝገቡ!!
ምዝገባው ነባሮችንና አዲስ ጀማሪዎችንም ያጠቃልላል።

ዳሩል ሀዲስ
@darulhadis18
266 views09:09
Open / Comment