🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

Asgerami

Logo of telegram channel asgerami — Asgerami A
Logo of telegram channel asgerami — Asgerami
Channel address: @asgerami
Categories: Facts
Language: English
Country: Ethiopia
Subscribers: 158
Description from channel

💡💡💡💡💡💡💡💡💡💡💡💡💡💡💡
🔦FACTS that will make you go crazy
💡Daily Dose of Amazing and mind boggling Facts.
🔴 OUR YOUTUBE CHANNEL https://youtube.com/channel/UCCuBSfOc
OTHER CHANNEL 👉 @startlingminds
Buy ads: https://telega.io/c/asgerami

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


The latest Messages 12

2021-10-20 06:44:08
ሩስያዊው የአስር አመት ልጅ 5,713 ፑሽ አፕ በመምታት ሪከርድ አስመዝግቧል ።

ሩስያዊው የአስር ዓመቱ ኢልማን ካድዙሙራዶቭ ከፎዶርቭስኪ በየቀኑ ዘጠኝ ማይል ሩጫን ጨምሮ ከባድ የልምምድ ክፍለ-ጊዜዎች የሚያሳልፍ ሲሆን ዛሬ በሩሲያ በሱርጉት አውራጃ በሚገኘው የትምህርት ቤት የስፖርት ማእከል በሦስት ሰአት ተኩል ውስጥ 5,713 ፑሽ አፕ በመስራት የአለም የልጆች ፑሽ አፕ ሪከርደን ይዟል።

ከዚህ ቀደም ከእሱ እድሜ ክልል የሚገኘውና በቺችን ዋና ከተማ ግሮንዚ የሚኖረው የ10 አመት ልጅ 4,784 የሰራውን ፑሽ አፕ ነው ዛሬ ኢልማን ካድዙሙራዶቭ ከፎዶርቭስኪ የሰበረው። [አርቲ ሚዲያ]

@asgerami
256 views03:44
Open / Comment
2021-10-16 21:27:33 ልዩ ልዩ እውነታዎች

~አልበርት ኢንስቴይን ሊሞት ከሰአታት በፊት ስለ "Theory of every thing" ለማጣራት እየሞከር ነበር!

~አንድ ሰው በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ 1460 ህልሞችን ያያል።

~አፕል ኮምፒውተሮች አካባቢ ሲጋራ ማጨስ ካምፓኒው የሰጠህን የኮምፒውተሩን ዋስትና ያሳጣሀል፡፡

~ፀሀይ በ 1 ሰከንድ ውስጥ 6 ሚልየን ቶን የሚሆን ክበደቷን በ nuclear fusion እና በ Solar wind ምክንያት ታጣለች፡፡ አስገራሚው ነገር ግን ከተፈጠረች ጀምሮ እስከዛሬ 0.05% ብቻ የሚሆን ክብደቷ ነው የቀነሰው፡፡

~በ አለም ካሉ 25 ረዣዥም ተራራዎች 19ኙ ሂማልያ ውስጥ ይገኛሉ ።

~የሰውን ልጅ በፍፁም ከማይፈሩት አደገኛ እንስሳት መሀከል ጉማሬ አንደኛ ነው።

~በእግርኳስ ጨዋታ ከፍተኛ የተቆጠረው ጎል 149 ነው!

~ውሻን በሰንሰለት ማሰር ተናካሽነቱን በ3 እጥፍ ይጨምረዋል።

~ሜርኩሪ በክረምት ወቅት ከቅዝቃዜዋ የተነሳ ካርቦንዳይ ኦክሳይድ ሳይቀር በረዶ ይሰራል።

➟ ቼዝ መጫወት አይኪውን በአስደናቂ ሁኔታ ይጨምራል፡፡

➟ በአይናችን ውስጥ 130 ሚሊዮን የብርሀን እና የቀለም ተቀባይ ቅንጣቶች አሉ፡፡

@asgerami @asgerami
@asgerami @asgerami
229 views18:27
Open / Comment
2021-10-10 18:00:02
ድሮ ደቡብ ኮሪያ ውስጥ እጅግ በጣም ተወዳጅ ከሚባሉት የምግብ አይነቶች መካከል የውሻ ሾርባ እና የውሻ ጥብስ ነው፡፡ ከምርጥ ምግብነት አልፎም ተርፎ ለቆዳ ውበት እና ለስንፈተ ወሲብ ችግር ፍቱን መድሀኒት በመሆኑ ተወዳጅነቱን እጥፍ ድርብ አድርጎላቸዋል! ድሮ የውሻ ስጋ መብላት የኮርያውያን ባህል ቢሆንም ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ተወዳጅነቱ እየቀተሰ መቷል።

በተለይ እንደፈረንጆቹ 2000 ዓ.ም ቡኃላ የተወለዱ ልጆች ይሄ ባህል እንዲቀር እና እንደሚፀየፉት እየተናገሩ ሲሆን። ውሾች የሰው ጓደኛ እንጂ ምግብ አደሉም በሚል የተለያዩ ተቋውሞ ሰልፎች እያካሄዱ ሲሆን መንግስት የውሻ ስጋ መሸጥም ሆነ መግዛት እንዲከለክል እየገፉ ነው። ከዚህም የተነሳ በቅርብ ግዜም የቀድሞ የማንቸስተር ዩናይትድ ተጨዋች ጂሱንግ ፓርክ ለክለቡ ደጋፊዮች ዘረኝነትን ያዘሉ ቃላቶችን ለሱ ካወጡለት ዝማሬ ላይ እንዲያነሱ ጠየቀ!

በቀያይ ሴጣናቱ ደጋፊዮች ተወዳጅ የሆነዉ ደ.ኮሪያዊዉ ፓርክ ከወር በፊት በሞንሊክስ ዩናይትድ ከዎልቭስ ጋር በነበራቸዉ ጨዋታ ለሱ የወጣለትን ዝማሬ ከረጅም አመታት በኋላ በደጋፊዮች ሲዜም ነበር፤

የሚከለውንም ተናግሮ ነበር

"አዉቃለዉ እናንተ በመጥፎ አስባችሁት አይደለም ለዚህም ነዉ ላስረዳችሁ ምፈልገዉ ያ የምትጠቀሙበት ቃል[dog meat]አሁን በኮሪያ እንደዘረኝነት ነዉ ሚቆጠረዉ፤

በኮርያ አሁን ነገሮች ተቀይረዋል፤ እዉነት ነዉ በታሪካችን የዉሻ ስጋ ተመግበናል፤ አሁን ግን ልጆቻችን በጣም የሚጠሉትና የሚፀየፉት ነገር ነዉ፤ ይህ ትዉልድ ተቀይሯል፤ ስለዚህ የዩናይትድ ደጋፊዮችን የምጠይቀዉ "የዉሻ ስጋ" የምትለዉን ቃል እንድታነሱት ነዉ፤ የሀገሬ ህዝቦች ይህ ቃል ምቾት አይሰጣቸዉም ስለዚህም ይህን ቃል መጠቀም ብታቆሙ።"

@asgerami
289 views15:00
Open / Comment
2021-10-10 08:00:09
መንፈስ (Ghost)

የፓራኖርማል ኤክስፐርቶች እንደሚሉት ከሆነ ብዙ የሙት መንፈስ የሌለበት ቦታ የመቃብር ስፍራ ነው ይላሉ ፤ እነሱ እንደሚሉት ከሆነ በማታ አንድ የመቃብር ስፍራ ካሉት የሙት መንፈሶች ይልቅ በምንተኛበት ክፍል ውስጥ ብዙ መንፈሶች አሉ ። የፓራኖርማል ኢንቨስቲጌተሮች እንዳሳወቁት የሙት መንፈሶች (Ghost) ቤት ውስጥ ባዶውን የተቀመጠ ወንበር ላይ መቀመጥ ያዘወትራሉ ምተኙበት ክፍል ውስጥ ባዶ ወንበር ካለ እሱ ላይ ተቀምጠው ያፈጡባቹሃል ፣ በህልማቹ ያቃዧቹሃል ፣ ድምፃቹንም በመንጠቅ ለራሳቸው እስክትነቁ ይጠቀሙበታል ። ድንገት ሻማ ለኩሳቹ የለኮሳቹት ሻማ ሰማያዊ ሆኖ ሚበራ ከሆነ ወይም የሻማው እሳት ያለ ምንም ንፋስ በድንገት ከጠፋ አጠገባቹ መንፈስ አለ ማለት ነው ይላሉ የዘርፉ ተመራማሪዎች ።

ፓራኖርማል ሳይንስ በመላምልቶች እንጂ በእውነታ የተደገፈ አደለም

@asgerami
459 views05:00
Open / Comment
2021-10-09 18:00:00
በአለም ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የህዝብ ብዛት ከአንድ ሚሊየን በላይ የተቆጠረባት ከተማ የጣልያንዋ "ሮም" ከተማ ናት

@asgerami
562 views15:00
Open / Comment
2021-10-09 14:52:47
በዚህ ዘመን የምንመለከታቸው አብዛኛዎቹ ፊልሞች ወደ ሁለት ሰዓት ያህል ሲሆኑ ፣ ከፍተኛው ደግሞ ለሦስት ሰዓት ያህል ብቻ ነው ፣ ነገር ግን በዓለም ላይ ያለው ረጅሙ ፊልም ለ 857 ሰዓታት ያህል የሚቆይ ነው !ስሙም (ርዕሱ) " logistics " ይባላል ። ይሄ የአለማችን ረጅም ፊልም የተሰራው በስዊድን ሲሆን አንድ ሰው ፊልሙን ያለ ምንም እረፍት በቀጥታ ልየው ቢል ፊልሙን ለመጨረስ 1ወር ከአንድ ሳምንት ወይም 36 ቀናቶች ይፈጁበታል ።

@asgerami
615 views11:52
Open / Comment
2021-10-09 14:10:26
ቤቲካ ላይ ይወራረዱ! ያሸንፉ!
እጅግ ብዙ የማሸነፊያ አማራጮች ከአሪፍ የጨዋታ ኦዶች ጋር!
አሁኑኑ  ይወራረዱ! 
584 views11:10
Open / Comment
2021-10-07 19:15:10
ተሞሸሩ !!

የ35 አመቱ ግብፃዊ እና የ80 አመቷ እንግሊዛዊትዋ ተሞሸሩ ። እኝህ አሮጊት የልጅ ልጅ አይተዋል ተብሏል ። የልጅ ልጆችዋ እኩያ ከሚሆን አንድ ግብፃዊ ጋር ተጋብታ ሀገሩን ጉድ አስብላለች። ለመጀመርያ ግዜ የተዋወቁት በ ፌስቡክ ነው። ለተወሰነ ግዜ በቻት ከተጀናጀኑ ቡኃላ ወጣቱ በእንግሊዛዊቷ ፍቅር መውደቁ ተነግሯል !! ሴትዮዋም ግብፅ መታ ልጁን አግብታው ኢንግሊዝ ይዛው ሄዳለች።

በመጨረሻም ልጁ ሲጠየቅ ከ 80 ዓመት ሚስቱን ከልብ እንደሚያፈቅራት እና ከሷ ጋር እስከ ህይወቱ ፍፃሜ እንደሚኖር ተናግሯል ።

ምን ትላላቹ እንደዚህ አይነቱን ነገር


@asgerami
@asgerami
@asgerami
573 views16:15
Open / Comment
2021-10-06 12:54:49 የዶሮዎች ነፃ ትግል ፍልሚያ

በነ ሼክስፒር ዘመን የእንግሊዛውያን ነገስታት መናሃሪያ የሆነው ዌስት ሚኒስተር ቋሚ ኮፕ ኪት (የአውራ ዶሮዎች መጋጠሚያ ስታዲየም) ሁሉ ነበረው ። በየሳምንቱ ልክ ዛሬ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ እንደምንለው በሰአቱ የዶሮዎች ፕሪምየር ሊግ ይካሄድ ነበር ። በአሁኑም ጊዜ ልክ እንደ አሜሪካ ቤዝቦል እና ራግቢ በበርካታ አገራት ውስጥ ዝነኛ እና ስመጥር ስፖርት ከሚባሉት ውስጥ አንዱ ኩክ ፋይቲንግ እየሆነ መቷል ።

በአለማችን ላይ በአሁኑ ሰአት የአውራ ዶሮዎች ሊግ በየአመቱ ይካሄዳል ። የአውራ ዶሮ ሊግ ከሚያካሂዱ እና የአውራ ዶሮ ሊግ ውድድርን ለማካሄድ የአውራ ዶሮ ሊግን የሚያስተናግዱ ስቴዲየሞች ካላቸው ሃገራቶች እንግሊዝ ፣ ስፔን ፣ ቬንዙዌላ ፣ ኮሎምቢያ ፣ ኢኮዶር ፣ ሜክሲኮ ፣ ፈረንሳይ ፣ ፓኪስታን ፣ ፊሊፒንስ ፣ ፔሩ እና ፓናማ ናቸው ።

የዶሮዎቹ ፍልሚያ ልክ እንደ እግር ኳሱ ሁሉ የአለም ዋንጫ አለው በታሪክ ድርሳን መዛግብት ውስጥ የተፃፈው የመጀመሪያው ''የአውራ ዶሮዎች'' የአለም ዋንጫ የተካሄደው በ1607 ነው ። በአለም እግር ኳስ ዋንጫ ታሪክ ብራዚል አንደኛ! ጀርመን ሁለተኛ! ጣልያን ሶስተኛ ወዘተ እንደምንለው በአለም የአውራ ዶሮዎች ፍልሚያ ዋንጫ አንደኛ መሆን የቻለችው ሃገር ፓኪስታን ናት ።

ወደ ስቴዲየም ከሚመጡ ታዳሚዎች ውስጥ አብዛኛው የሚመጣው የየራሱን አውሮ ዶሮ ይዞ ነው ። ይህም ለምን ? ምክንያቱም እዛው ስታዲየም ውስጥ የሚፈጠር ክስተት አለ ። እኔ! እኔ! እኔ!እያሉ የራሳቸውን አውራ ዶሮ ወደ መድረኩ በመምጣት እጩ ተወዳዳሪ እንዲሆንላቸው ለውድድር የሚቀርቡበት አንዱ አቋራጭ ስልት ነው ።

ኮክ ፋይት ከዛሬ 6ሺ አመታቶች በፊት ጥንት ፐርሺያ ተብላ በምትጠራዋ በአሁንዋ ኢራን ውስጥ የተጀመረ ጥንታዊ የስፖርት አይነት ነው ። በበፊት ጊዜ ውድድሩ የሚዘጋጀው የንጉሳውያን ቤተሰቦችን በሳምንቱ የእረፍት ቀን ላይ ለማዝናናት ሲባል ነበር ። በዚያን ዘመን ወደ ኮምኪት ገብተው ይህንን አዝናኝ ትርኢት ለማየት የሚፈቀድላቸው የንጉሳውያን ቤተሰቦች እና ከነሱ ቅርበት ያላቸው ብቻ ነበሩ ።

ለነፃ ትግሉ የሚመረጡ አውራ ዶሮዎች የእግራቸው አጥንት እና ስጋ የፈረጠመ እና ክንፋቸውን የመወንጨፍ ሃይል የተባ መሆን አለበት ። እነዚ ተፋላሚ አውራ ዶሮዎች የገበያ ዋጋቸው እስከ 8ሺ የአሜሪካን ዶላር ወይም 320ሺ ብር ይደርሳል።

የአውራ ዶሮዎቹ ባለቤቶች ወደ መወዳደሪያ መድረክ (ኮፕ ኪት) ከመግባታቸው በፊት ይደራደራሉ ወይም የውል ሰነድ ይፈራረማሉ ። ከዚያም ገንዘብ ያሲዛሉ መሸነፍ ማሸነፍ ያለ ነውና ከውድድሩ ቡሃላ ያሸነፈው ዶሮ ለባለቤቱ ገቢ ያስገባል ። የተሸነፈው ዶሮ በሚቀጥለው በቂ ልምምድ አድርጎ ይቀርባል ።

የአውራ ዶሮዎቹ የነፃ ትግል ልክ እንደ እግር ኳስ 90 ደቂቃ ሊቆይ ይችላል ። የመጀመሪያው 45 ደቂቃ እና ሁለተኛ አጋማሽ ተብሎም በሁለት ይከፈላል ። በ90 ደቂቃው ካልተሸናነፉም ተጨማሪ ሰአት ይሰጣል ። አሁንም ካልተሸናነፉ አሸናፊው የሚለየው በእጣ ነው ።

አሸናፊ እና ተሸናፊ የሚለየው
1, ተሸናፊው የመድረክ ቀለበቱን ለቆ ከወጣ
2, ተሸናፊው ፈርጥጦ ከጠፋ
3, አሸናፊው ዶሮ በተሸናፊው ዶሮ ላይ ጉብ ብሎ ማንቁርቱንለ4 ሰከንድ በመንቁሩ ነክሶ ሳይለቅ ከያዘ
4, ተሸናፊው ዶሮ በጣም ከተጎዳ ወይም ከሞተ በማለት ነው።

ለዘመድ እና ለጓደኞቻቹ ሼር አርጉ

@asgerami
722 viewsedited  09:54
Open / Comment
2021-10-06 12:54:27
679 views09:54
Open / Comment