Get Mystery Box with random crypto!

ገራዶ ሚዲያ

Logo of telegram channel geradomedia — ገራዶ ሚዲያ
Logo of telegram channel geradomedia — ገራዶ ሚዲያ
Channel address: @geradomedia
Categories: News
Language: English
Subscribers: 679
Description from channel

🔸ሁሉን አቀፍ የመረጃ ምንጭ!🔸
✍ ፃፉልን @geradomediabot
fb.com/geradomedia
twitter.com/geradomedia

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages 9

2021-04-26 21:37:00
ደግ ደጉን እናስብ፤ ደግ ደጉን እንናገር፤ ደግ ደጉን እንተግብር! መልካምነት መልሶ ይከፍለናልና!
.

መልካም አዳር

t.me/geradomedia
202 viewsGashu, 18:37
Open / Comment
2021-04-26 18:42:25
186,240 ገጀራ ተያዘ!

በአስመጭ ዳዊት የማነ ስም ብዛቱ 186,240 የሆነ የእጅ ገጀራ በአራት ባለ 20 ጫማ ኮንቴይኔሮች ከቻይና ተጭኖ ሞጆ ጉምሩክ ተጓጉዞ ከደረሰ በኃላ እቃው በዲ/ዮን ቁጥር 4-1919/21 ተመዝግቦ እቃዉም ወደ ሀገር ዉስጥ እንዲገባ ከፌዴራል ፖሊስ የተፈቀደለት በማስመሰል እና ሐሰተኛ ሰነድ አዘጋጅቶ ለገቢ ዕቃ አወጣጥ የሰነድ መርማሪው አቅርቦ ሰነዱ ተመርምሮ ከ7.7ሚሊዮን ብር በላይ ቀረጥና ታክስ ከፍሎ እቃው ከተለቀቀ በኃላ በኢንተለጀስ በኩል ክትትል ተደርጎ የቀረበው ሰነድ ሲጣራ ሐሰተኛ እና እቃዉም ወደ ሀገር ዉስጥ እንዲገባ ከፌዴራል ፖሊስ ፈቃድ ያልተሰጠው መሆኑ ተረጋግጧል።

ይህን መነሻ በማድረግም በፌዴራል ፖሊስ ለሞጆ የወንጀል ምርመራ ማስተባባሪያ ፅ/ቤት መረጃዉን በመስጠት በተደረገው እልህ አስጨራሽ ክትትል የእቃው ባለቤት አዲስ አበባ ዉስጥ ተይዞ ጉዳዩ በምርመራ ላይ ይገኛል።

[ሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ]

t.me/geradomedia
1.1K viewsGashu, 15:42
Open / Comment
2021-04-26 14:21:29
ኢትዮጵያ ለሁለት አዳዲስ የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ፈቃድ ለመስጠት ያወጣችው ዓለም አቀፍ ጨረታ ተዘጋ!

የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን ለሁለት አዲስ የቴሌኮሙኒኬሽን ፈቃዶች የወጣው ጨረታ በዛሬው እለት መዘጋቱንም የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል። በዛሬው እለት በተካሄደው የጨረታ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ሰነድ ያስገቡ ኩባንያዎች ስም ዝርዝር ይፋ ተደርጓል።

በዚህም ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ በተባለ ተቋም ስም ሳፋሪኮም ከኬንያ፣ ቮዳፎን ከብሪታኒያ፣ ቮዳኮም ከከደቡብ አፍሪካ፣ ሲ.ዲ.ሲ ግሩፕ ከብሪታኒያ እና ሰሚቶሞ ኮርፖሬሽን ከጃፓን በጥምረት እንዲሁም ኤ.ቲ.ኤን ከደቡብ አፍሪካ ሰነድ አስገብተዋል።

የሚሰጡት ሁለት የቴሌኮሙዩኒኬሽን ፈቃዶች አሸናፊዎች ባለሥልጣኑ በተረከባቸው የጨረታ ሰነዶች ላይ የሚያከናውነውን የቴክኒክ እና የፋይናንስ ግምገማዎች ካጠናቀቀ በኋላ የሚገለፅ መሆኑም ታውቋል።

ባለሥልጣኑ ከኢትዮ ቴሌኮም በተጨማሪ ለሁለት ኩባንያዎች የቴሌኮም አገልግሎት ፈቃድ ለመስጠት ባሳለፍነው ዓመት ግንቦት ወር ላይ የፍላጎት መግለጫ መጠየቂያ አውጥቶ እንደነበር ይታወሳል። ይህንን ተከትሎም ህዳር 18 ቀን 2013 ዓለም አቀፍ ጨረታ ማውጣቱ አይዘነጋም። ጨረታውም ዛሬ ተዘግቷል።

ሂደቱ መንግስት የገጠመውን የውጭ መንዛሬ ዕጥረት ለመፍታት እና ውድድርን ለመፍጠር ካቀዳቸው የአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳዎች አንዱ መሆኑንም ጠቅሷል። #AlAin

t.me/geradomedia
228 viewsGashu, 11:21
Open / Comment
2021-04-26 14:21:22
አስደሳች ዜና ለሴቶች!

ለሴቶች የሚሆኑ ምርጥ ምርጥ ኢስላማዊ አልባሳቶች፣ ጫማዎች፣ የመዋቢያና ሌሎች እቃዎችን እጅግ ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ይዘን ቀርበናል። ቀጣዩን ማስፈንጠሪያ በመጫን ቻናላችንን ተቀላቅለው ቤተሰብ በመሆን የፈለጉትን ይግዙ!

ማስፈንጠሪያ
https://t.me/joinchat/MfQzuyBzvpUyZDU0
222 viewsGashu, 11:21
Open / Comment
2021-04-25 22:21:30
"ጥላቻ ህይወትን ሽባ ያደርጋል፤ ፍቅር ግን ይፈውሳል። ጥላቻ ህይወትን ግራ ያጋባል፤ ፍቅር ደግሞ አንድነትን ይፈጥራል። ጥላቻ ህይወትን ያጨልማል፤ ፍቅር ደግሞ በብርሃኑ ጨለማን ይገፋል። በህይወት ዘመንህ ደስተኛና ተወዳጅ ለመሆን ከፈለክ ማንንም አትጥላ!" - ማርቲን ሉተር ኪንግ

መልካም አዳር

t.me/geradomedia
622 viewsGashu, 19:21
Open / Comment
2021-04-25 21:35:31
ዜና እረፍት

አርቲስት መስፍን ጌታቸው በኮቪድ-19 ህይወቱ አለፈ!

የዙምራ ፊልም፣ የሰው ለሰው እና የዘመን ድራማ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች ደራሲና ተዋናይ የነበረው አርቲስት መስፍን ጌታቸው በኮቪድ-19 ተይዞ በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቢቆይም በዚሁ ቫይረስ ሳቢያ ምክንያት በ50 አመቱ ህይወቱ ማለፉን etv ዘግቧል።

አርቲስት መስፍን ጌታቸው ባለትዳር እና የሶስት ልጆች (የሁለት ሴት እና የወንድ ልጅ) አባት ነበር። ገራዶ ሚዲያ ለአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ እና አድናቂዎች መጽናናትን ይመኛል፡፡

t.me/geradomedia
557 viewsGashu, 18:35
Open / Comment
2021-04-25 21:35:26
አስደሳች ዜና ለሴቶች!

ለሴቶች የሚሆኑ ምርጥ ምርጥ ኢስላማዊ አልባሳቶች፣ ጫማዎች፣ የመዋቢያና ሌሎች እቃዎችን እጅግ ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ይዘን ቀርበናል። ቀጣዩን ማስፈንጠሪያ በመጫን ቻናላችንን ተቀላቅለው ቤተሰብ በመሆን የፈለጉትን ይግዙ!

ማስፈንጠሪያ
https://t.me/joinchat/MfQzuyBzvpUyZDU0
554 viewsGashu, 18:35
Open / Comment
2021-04-25 19:48:37 "ኢትዮጵያን በቀጥታ ሳይሆን በውክልና ጦርነት ነው የምንወጋት"

ሼሪፍ ኤልሳሊይ ይባላል፤ ግብፃዊ ነው። የፕሬዚዳንት አብዱል ፈታ አልሲሲ አክቲቪስት ነው። ተከታዩን መልዕክት በቪድዮ ለቋል።

"ኢትዮጵያን ፊትለፊት ጦርነት አንግጥምም። የምንዋጋት በውክልና ጦርነት ነው። በሁሉም ክልሎች የሚደረጉ የሽምቅ ጦርነቶች ላይ የግብፅ ድጋፍ የለበትም ማን አላችሁ? ኢትዮጵያ ውስጥ በሁሉም ክልሎች ያሉ የሽምቅ ተዋጊዎች የግብፅ መንግስት ድጋፍ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። መንግስታችንም ይሄንን ብሎ ተቀብሎ ወደስራ ገብቷል።

እኛም የሚያዋጣንን ጠንቅቀን እናውቃለን! አሁን ኢትዮጵያን የሚገዛው ማዕከላዊ መንግስቱ ተዳክሟል። በዚህ በተዳከመ መንግስት ራሳቸውን ነፃ ለማውጣት ከኢትዩጵያ መንግስት ጋር የሚዋጉ ሀይሎች የግብፅ ስትራቴጂካዊ ወዳጅ ናቸው!

ግድቡን ከግብፅ የሄደ ጦር ከሚያፈርሰው ይልቅ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሀይሎች ቢያፈርሱት ነው ለግብጽ አዋጩ መንገድ። እዚህ ጉዳይ ላይ መንግስታችን ተግቶ እየሰራበት ነው። የግብፅ ህዝብ ሆይ .....የግብፅ መንግስት በህዳሴው ግድብ ላይ ለምን እርምጃ አልወሰደም? ይህ ቀይ መስመር ነው ብሎ የለም እንዴ? አትበሉ! መሰራት ያለበንት እየሰራ ነው። ሁሉንም ነገር ለእናተ ማሳወቅ የለበትም!"

የለቀቀውን ቪድዮ ሙሉ ትርጉም በቀጣዩ ሊንክ ታገኛላችሁ።



ውድ ኢትዮጵያዊያን አንድ እንሁን! ጠላቶቻችን እየተሳለቁብን ነው!

Via ሱሌማን አብደላ

t.me/geradomedia
33 viewsGashu, 16:48
Open / Comment
2021-04-25 14:00:49
575 viewsGashu, 11:00
Open / Comment
2021-04-25 13:16:36
አስደሳች ዜና ለሴቶች!

ለሴቶች የሚሆኑ ምርጥ ምርጥ ኢስላማዊ አልባሳቶች፣ ጫማዎች፣ የመዋቢያና ሌሎች እቃዎችን እጅግ ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ይዘን ቀርበናል። ቀጣዩን ማስፈንጠሪያ በመጫን ቻናላችንን ተቀላቅለው ቤተሰብ በመሆን የፈለጉትን ይግዙ!

ማስፈንጠሪያ
https://t.me/joinchat/MfQzuyBzvpUyZDU0
173 viewsGashu, 10:16
Open / Comment