Get Mystery Box with random crypto!

ገራዶ ሚዲያ

Logo of telegram channel geradomedia — ገራዶ ሚዲያ
Logo of telegram channel geradomedia — ገራዶ ሚዲያ
Channel address: @geradomedia
Categories: News
Language: English
Subscribers: 679
Description from channel

🔸ሁሉን አቀፍ የመረጃ ምንጭ!🔸
✍ ፃፉልን @geradomediabot
fb.com/geradomedia
twitter.com/geradomedia

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages 8

2021-04-28 07:45:38
የእርስ በእርስ ግጭት መጨረሻው ይሄ ነው! አሸናፊ የለውም፤ ተያይዞ መሞት ነው! ቆም ብለን እናስብ ወገን!

መልካም ቀን!

t.me/geradomedia
427 viewsGashu, 04:45
Open / Comment
2021-04-27 21:32:07
#ለጥንቃቄ

በሚቀጥሉት 5 ቀናት በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ሊኖር እንደሚችል የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ አሳሰበ!

የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አህመዲን አብዱልከሪም እንዳሉት፥ ባለፉት ሁለት ወራት የፓስፊክ ውቂያኖስ ምስራቃዊና ማዕከላዊ የውሃ አካል ከመደበኛ በታች የመቀዝቀዝ ሁኔታ መስተዋሉን ተከትሎ የዘንድሮው የበልግ ወቅት መቆራረጥ ታይቶበታል፡፡

ከተያዘው ወር ጀምሮ ግን ቀስ በቀስ ወደ መደበኛ ሁኔታ እየተመለሰ መሆኑን የአለም አቀፍ የትንበያ ማዕከላት ማሳወቃቸውን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

አክለውም በኦሮሚያ ክልል በሁሉም የወለጋ ዞኖች፣ ጅማ፣ ኢሊባቡር፣ የሸዋ ዞኖች፣ ምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ፣ አርሲ፣ ባሌ፣ ጉጂ እንዲሁም የሱማሌ ክልል፤ ከአማራ ክልል የሰሜንና የደቡብ ወሎ ዞኖች፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ደቡብ ጎንደር፤ የሲዳማ ክልልና አንዳንድ አካባቢዎች መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል አቶ አህመዲን ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪ በሚቀጥሉት 5 ቀናት ውስጥ የደቡብ ምዕራብ እና የደቡብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ሊኖራቸው እንደሚችልም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

[አሐዱ ራዲዮ]

t.me/geradomedia
1.1K viewsGashu, 18:32
Open / Comment
2021-04-27 19:50:34
በአስዋን ግድብ አቅራቢያ ያጋጠመው የመሬት መንቀጥቀጥ......

ግብፅ 37% የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ሀይል በሚሸፍንላት ሽማግሌው የአስዋን ግድብ ያረፈበት ቦታ ላይ በሬክተር ስኬል 3.1 የሆነ “የመሬት መንቀጥቀጥ” እንዳጋጠመ Egypt Independent ዘግቧል።

የመሬት መንቀጥቀጡ በአካባቢው ሰዎች ስሜቱን ያስተዋሉት ሲሆን፣ ምንም አይነት ጉዳት አላደረሰም ተብሏል። ነገር ግን ከዚህ በፊት ግብፃዊያን በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት እኤአ አቆጣጣር በ1903 - 10 ሺህ ሰዎች፣ በ1985 - 5 ሰዎች፣ በ1992 - 541 ሰዎች ሲሞቱ፤ በሀገሪቱ ዋና ከተማ ካይሮ ደግሞ
398 ፎቆችንና 8 ሺህ ቪላ ቤቶችን ማፍረሱን የግብፅ የመሬት መንቀጥቀጥ ታሪክ ይናገራል!

በተቃራኒው እነሱ "የህዳሴ ግድቡ የሚሰራበት ቦታ ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ያስከትላል! ይሄም የወደፊት የሱዳን ስጋት ነው!" እያሉ ሱዳን በኢትዮጵያ ላይ እንድታምፅ ይገፋፉ ነበር !

Via ሱሌማን አብደላ

t.me/geradomedia
550 viewsGashu, 16:50
Open / Comment
2021-04-27 17:56:51
#ኢዜማ #መግለጫ

በኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አዘጋጅቶታል የተባለውና “የሃገሪቷ ወቅታዊ የደህንነት ስጋት ትንተና” የሚል ርእስ ያለው የኢዜማ ሚስጥራዊ ሰነድ ነው ተብሎ ከትላንት ጀምሮ በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገጾች እየተዘዋወረ ነው። የነጻነትና እኩልነት ፓርቲም (ነእፓ) በዚሁ ሰነድ ላይ ስሜ አሉታዊ በሆነ መንገድ በመጠቀሱ ማብራሪያ ይሰጠኝ ሲል ለኢዜማ በደብዳቤ ጠይቆ ነበር።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ህዝብ መግለጫ አውጥቷል። በዚህም ከትላንት ጀምሮ ሲዘዋወር የነበረውን ሰነድ "ኢዜማን የማያወክል እና ኢዜማ የማያዉቀዉ" ነው ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

t.me/geradomedia
541 viewsGashu, 14:56
Open / Comment
2021-04-27 17:01:56 የመከላከያ ሠራዊትን ዩኒፎርም በመልበስ በተለያዩ የዕምነት ተቋማት ሲያመልኩ የሚታየው ፎቶ ተጣርቶ እርምጃ ይወስዳል- መከላከያ ሰራዊት

በቅርቡ የመከላከያ ሠራዊት ዩኒፎርም በመልበስ በተለያዩ የዕምነት ተቋማት ሲያመልኩ የሚያሳይ መረጃዎች በሚመለከታቸው የተቋሙ የፍትህ አካላት ተጣርቶ አስፈላጊው እርምጃ እንደሚወሰድ የመከላከያ ሠራዊት አስታወቀ፡፡ የመከላከያ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ በሰጡት መግለጫ፤ የመከላከያ ሠራዊት ገለልተኛ፣ የትኛውንም የሀይማኖት ተቋም እንደማይወክል ገልፀዋል፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ከየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ የማይወግን እና የማንኛውንም ዕምነት የማያራምድ መሆኑ በህገ- መንግስታቱም ይሁን በቅርቡ በጸደቀው የመከላከያ ስትራቴጂክ የግንባታ ሰነድና በአስተዳደራዊ ደንብ ላይ በማያሻማ ሁኔታ ተደንግጓል ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡

ከዚህ በፊት የመከላከያን የደንብ ልብስ በመልበስ በተለያየ የዕምነት ተቋም ሲያመልኩ የተገኙ በቁጥጥር ስር ውለው እና ሪሀብሊቴሽን ማዕከል ገብተው ቅጣታቸውን ፈጽመው የወጡ መኖራቸውን ኮሎኔል ጌትነት ጠቁመዋል።

መሰል ድርጊቶችም በሰራዊቱ ውስጥ ሲከሰቱ የተለያዩ አስተዳደራዊ እርምጃዎች ሲወሰዱ መቆየታቸውን አመልክተዋል ፡፡

የመከላከያ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ እንዳሉት፤ በቅርቡ በተለያዩ የዕምነት ተቋማት የጀግናውን እና የየትኛውንም እምነት የማይወክለውን ሠራዊት የደንብ ልብስ በመልበስ የታዩ ግለሰቦችን በማጣራት ክስ ይመሰረትባቸዋል ነው ያሉት።

በእንደዚህ አይነት ጥፋት የሚገኙ የሰራዊት አባላት እስከ አምስት አመት የሚደርስ የእስር ቅጣር እንደሚበየንባቸው ገልፀዋል።

መከላከያ ሰራዊት ዕምነትም ሆነ ሀይማኖት የማይወክል በመሆኑ በዚህ ድርጊት የተሳተፉ አባላት እደዚህ ቀደሙም እርምጃም ይወሰድባቸዋል ብለዋል፡፡

የሠራዊቱ አባላት የፈለጉትን ዕምነት የመከተል መብት አላቸው ያሉት ኮሌኔሉ ይሁን እንጂ የተከበረውን የኢትዮጵያ ህዝቦች መመኪያ የሆነውን የደንብ ልብስ በመልበስ ማምለክ ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የዕምነት ተቋማቱም በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት በርካታ ሙያዎች ውስጥ ሠራዊቱን መርጠው በዚህ መልኩ ማሳየት የፈለጉበት ምክንያት ምን እንደሆነ መከላከያ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚከታተለው ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያ ፤ የተቋሙን ዩኒፎርም የለበሱ እና በፓትሮል መኪና ሆነው ሰው እየደበደቡ የተላለፈው ዘገባ እውነተኛነቱ ተረጋግጦ እርምጃ ይወሰዳል ሲሉ ገልጸዋል።

ሆን ብለው የተቋሙን አልባሳት እያስመሰሉ የሚለቀቁ ምስሎች እንዳሉ እንረዳለን ያሉት ኮሌኔል ጌትነት ፤ ይህን እና መሰል የስም ማጥፋት ዘመቻ ሲኖር ህዝቡ እየተከላከለልን ውስጣችንን ደግሞ ራሳችን እያረምን እንሄዳለን ብለዋል። ህዝቡ መሰል የመከላከያ ሠራዊትን ክብር እና መልካም ስም ለማጉደፍ የሚደረጉ ጥረቶችን ሲመለከት ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።» #FBC

t.me/geradomedia
613 viewsGashu, edited  14:01
Open / Comment
2021-04-27 14:23:23
#በድጋሚ_የተፓሰተ

የዩኒቨርስቲ ተማሪ ሆናችሁ እስካሁን ለምርጫ ያልተመዘገባችሁ፤ በሚቀጥለው ማስፈንጠሪያ በመግባት መመዝገብ ትችላላችሁ። http://www.nebe.org.et/ovrs

#እመዘገባለሁ #እመርጣለሁ

t.me/geradomedia
112 viewsKedir Ahmed, 11:23
Open / Comment
2021-04-27 13:18:40
"ደም አፋሳሽ ድርጊቶችን የሚደግፍ ሰው ሰይጣናዊ መንፈስ ያለበት ነው" - ሼህ መሀመድ ሲራጅ

ደም አፋሳሽ የሆኑ ድርጊቶችን የሚደግፍ ሰው ሰይጣናዊ መንፈስ ያለበት እንደሆነ እና በአሁኑ ወቅትም በአገሪቱ የሚታዩ ነገሮች ደስ እንደማያሰ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ዑለማ ምክር ቤት አባልና የሰላም ዘርፍ ሃላፊ ሼህ መሀመድ ሲራጅ ገለፁ። በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ የሚታዩ ነገሮች ደስ እንደማያሰኙ አስታወቁ።

ሼህ መሀመድ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት፤ የፈጣሪን ሕግና መመሪያን የሚያከብር ሰው እርስ በእርስ በሚያጋጩ፣ በሚያጣሉ፣ ደም በሚያፋስሱና በሚያጨፋጭፉ ድርጊቶች ላይ አይተባበርም። ድርጊቱን የሚፈጽሙ ሰዎች ዛሬ በሚሰሩት ሥራ ነገ መፀፀታቸው አይቀርምና ከድርጊታቸው መታቀብ አለባቸው።

ሌሎችን የሚያሰቃይ፣ ሕይወታቸውን የሚቀጥፍ፣ ደማቸውን የሚያፈስ፣ ንብረታቸውን የሚያጠፋ፣ ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሎ ሜዳ ላይ ከሚበትን አቋምና አስተሳሰብ መውጣት ይገባቸዋል ያሉት ሼህ መሀመድ፣ እንዲህ አይነት ድርጊት የሚፈጽም በዚች ምድር ላይ ተረጋግቶ አይኖርም። ቆም ብሎ ማስተዋል እንዳለበት አመልክተዋል።

"ተንኮል፣ ምቀኝነትና ሰዎች ላይ ጥቃት ማድረስ አረመኔያዊነት ተግባር ነው። ድርጊቱን የሚፈጽምም በምድር ላይ በደስታ አይኖርም፣ ቀጣይ ህይወቱም ሰቆቃ፣ መከራና ችግር ይገጥመዋል" ብለዋል።

ድርጊቱን የሚፈጽመው በወንድሞቹ፣ በእህቶቹ፣ በእናቶቹ፣ በአባቶቹና በወገኖቹ ላይ ነው። ፈጣሪ የተረጋጋ መንፈስ አይሰጠውም። ማንም ሰው እንዲህ አይነት ድርጊት በእናቱ፣ በልጁ፣ በአባቱ ላይ ቢደረግበት አይወድም፤ በእራሱ ላይ ሊደረግ የማይወደውን ነገር በሌሎች ላይ ማድረግ እንደሌለበት አስታውቀዋል። #EPA

t.me/geradomedia
332 viewsGashu, 10:18
Open / Comment
2021-04-27 12:01:57
ሱዳን ከግድቡ ጋር ተያይዞ ላሉ ልዩነቶች የአፍሪካ ህብረት መፍትሄ እንደሚሰጥ እምነቷ መሆኑን ገለፀች!

ሱዳን ከህዳሴው ግድብ ጋር ተያይዞ ላሉ ልዩነቶች በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ውጤታማና ፈጣን መፍትሄ ላይ እንደሚደረስ እምነቷ መሆኑንን አስታውቃለች። ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ በሚለው መሪ ቃል የሶስትዮሽ ድርድሩ እንዲቀጥል ፍላጎት እንዳላት ነው ሱዳን የገለፀችው።

የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ወሳኙን እና አዲስ ሃሳብና አሰራር የሚመጣበትን የአፍሪካ ህብረትን እንደሚያደንቅ መግለፁን ሱና ዘግቧል። ከዚህ ጋር ተያይዞም ሱዳን አቋሟን ለማስረዳት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ የሚመራ ልዑክ ወደ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ኬንያ፣ ሩዋንዳ እና ኡጋንዳ እንደምትልክ ገልጻለች።

Via FBC

t.me/geradomedia
1.0K viewsGashu, 09:01
Open / Comment
2021-04-27 08:16:17
እንዴት አደራችሁ ውድ የሀገር ልጆች?

ጥዋት ስንነሳ መልካሙን እናስብ! ከትናንት ጥሩውን ወስደን ዛሬን አዳስ ቀን እንጀምር! ቀኑ ደስ የሚል ነገር የምንሰማበት እንዲሆን ተመኘን!

መልካም ቀን ለሁላችን!

t.me/geradomedia
84 viewsGashu, 05:16
Open / Comment
2021-04-27 08:16:16
ማስታወቂያ ማሰራት ለምትፈልጉ

- እዚህ ቻናል ላይ ምርትና አገልግሎታችሁን ማስተዋወቅ የምትፈልጉ @geradomediabot ወይም @gashaw02 ላይ አናግሩን!
88 viewsGashu, 05:16
Open / Comment