Get Mystery Box with random crypto!

ገራዶ ሚዲያ

Logo of telegram channel geradomedia — ገራዶ ሚዲያ
Logo of telegram channel geradomedia — ገራዶ ሚዲያ
Channel address: @geradomedia
Categories: News
Language: English
Subscribers: 679
Description from channel

🔸ሁሉን አቀፍ የመረጃ ምንጭ!🔸
✍ ፃፉልን @geradomediabot
fb.com/geradomedia
twitter.com/geradomedia

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages 5

2021-05-03 19:23:49
ህወሃት” እና ‘’ሸኔ’’ በሽብርተኝነት እንዲሰየሙ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ለመቃወም የሚያስችል ማስረጃ ያለው ካለ......

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “ህወሃት” እና ‘’ሸኔ’’ በሽብርተኝነት እንዲሰየሙ በሚንስትሮች ምክር ቤት የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ለመቃወም የሚያስችል ማስረጃ ያለው ማንኛውም ግለሰብ በ48 ሰአታት ውስጥ በአካል እንዲቀርብ ጥሪ አቀረበ።

ምክር ቤቱ በአዋጁ አንቀጽ 21 ንኡስ አንቀጽ 1 በተደነገገው መሠረት “ህወሃት” እና ‘’ሸኔ’’ ላይ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ለመቃወም የሚያስችል ማንኛውም ማስረጃ ካላቸው ማስታወቂያው በመገናኛ ብዙሃን ከተነገረበት ሰዓት ጀምሮ ባሉት 48 ሰዓታት ውስጥ በምክር ቤቱ ጽ/ቤት በአካል በመገኘት እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርቧል።

የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀጽ 2 ንኡስ አንቀጽ 2 መሠረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሚያዚያ 23 ቀን 2013 ዓ/ም ባካሄደው 23ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ህዝበ ወያኔ ሓርነት ትግራይ /ህወሓት/ እና ‘’ሸኔ’’ ድርጅቶች በሽብርተኝነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሃሳብ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማቅረቡንም ነው ምክር ቤቱ ያስታወቀው። #Ebc

t.me/geradomedia
767 viewsGashu, 16:23
Open / Comment
2021-05-03 14:02:51
ስጋ አንቆት ሕይወቱ ያለፈው ወጣት

በፋሲካ በአል ስጋ ገዝቶ ጥሬውን እየተመገበ የነበረው ወጣት ስጋው አንቆት ሕይወቱ አለፈ፡፡ የወጣቱ ድንገተኛ የሞት አደጋ የደረሰው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ካዲስኮ አካባቢ እንደሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል። ወጣቱ ወደ ሆስፒታል እየተወሰደ ሳለ ነው መንገድ ላይ ሂወቱ ያለፈው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዜጎች ጥሬ ስጋ በሚመገቡበት አጋጣሚ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡ #ኢትዮ_ኤፍኤም

t.me/geradomedia
752 viewsGashu, edited  11:02
Open / Comment
2021-05-03 11:33:51
በዩኒቨርስቲ ምደባ ዙሪያ ቅሬታ ላላችሁ ተማሪዎች፦

በዩኒቨርስቲ ምደባ ዙሪያ ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሀሙስ ድረስ ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ ተብሏል። ቅሬታ ያላቸው ቅሬታቸውን በአካል መምጣት ሳያስፈልግ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው ከታች ባለው ድረገፅ ላይ ወይም የኢሜል እና በስልክ አድርሻዎች ማቅረብ ይቻላል።

ዌብ ሳይት፦ https://forms.gle/Jt9L7F2EDDC62YLQ7
ስልክ ቁጥር፦ +251911763794 +251943543805
ኢሜል፦ support@ethernet.edu.et

t.me/geradomedia
82 viewsGashu, 08:33
Open / Comment
2021-05-03 11:33:02
ማስታወቂያ ማሰራት ለምትፈልጉ

- እዚህ ቻናል ላይ ምርትና አገልግሎታችሁን ማስተዋወቅ የምትፈልጉ @geradomediabot ወይም @gashaw02 ላይ አናግሩን!

ለ 24 ሰዓት (2 ልጥፍ) ..... 50 ብር
ለ 1 ሳምንት (7 ልጥፍ) ... 240 ብር
ለ 1 ወር (15 ልጥፍ ... 450 ብር
ለ 1 ወር (20 ልጥፍ) ... 550 ብር
ለ 1 ወር (30 ልጥፍ) ... 800 ብር በመክፈል ማሰራት ትችላላችሁ።
86 viewsGashu, 08:33
Open / Comment
2021-05-03 10:25:22
"የምስራቅ አፍሪካ ምርጡ ዩኒቨርሲቲ" - አድስ አበባ ዩ/ቲ

'US News Global' የተሰኘ ዓለም-አቀፍ ተቋም ባወጣዉ የ2021 የዓለም ዩኒቨርሲቲዎች የደረጃ ሰንጠረዥ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን የምስራቅ አፍሪካ 'ምርጡ ዩኒቨርሲቲ አንተ ነህ' ብሎታል።

ከምስራቅ አፍሪካ የቀዳሚነትን ክብር ያገኘዉ ዪኒቨርሲቲው ከድፍን አፍሪካ 10ኛዉ ከመላዉ ዓለም ደግም 553ኛዉ ምርጥ ዩኒቨርሲቲ ተብሏል። በሪፖርቱ ተካተዉ ደረጃ ከወጣላቸዉ 1 ሺህ 500 የዓለም ምርጥ ዩኒቨርሲቲዎች ዉስጥ የአሜሪካዉ ሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የሁሉም አዉራ ተብሏል። በ 'US News Global' ደረጃ ሰንጠረዥ ኬፕ-ታዉን ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆኗል።

አድስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባለፈዉ ዓመት በዚሁ ተመሳሳይ ተቋም በተሰጠዉ ደረጃ ከምስራቅ አፍሪካ የ2ኛነትን ከዓለም ደግሞ የ616ኛነትን ስፍራ ነበር ያገኘዉ። #BisratFM

t.me/geradomedia
749 viewsGashu, 07:25
Open / Comment
2021-05-03 08:54:50
መከላከያ ሰራዊት እዩ ጩፋን በህግ ሊጠይቅ ነው!

በቅርቡ እዩ ጩፋ የተባለ ግለሰብ በሐይማኖት ስም እየተከተሉኝ ነው ያላቸውን ግለሰቦች ክብር ባልጠበቀ መልኩ ከነዩኒፎርማቸው በቪዲዮና ፎቶ ቀርፆ በአደባባይ እንዲሰራጭ አድርጓል።

ይህ የሰራዊቱን ስምና ታማኝነት በማሳጣት ለግል ፍላጎትና ጥቅም በማን አለብኝነትና ኃላፊነት በጎደለው አኳኋን ለፈፀመው ድርጊት የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት በህግ ለመጠየቅ መዘጋጀቱን የሰራዊቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ አስታውቀዋል።

ጥቂት የሰራዊታችን አባላትም ይህን ፍላጎት ለማሟላት የሁሉም ኢትዮጵያውያን መለያ የሆነውን ወታደራዊ የደንብ ልብስ ለብሰው ተሳታፊ የሆኑ እንደነበሩ ተረጋግጧል ያሉት ኮሎኔሉ፤ ተሳታፊዎቹም በመከላከያ ወታደራዊ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን ተይዘውና ታስረው ጉዳያቸውን ወደ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ለማቅረብ የማጣራት ስራ እየተሰራ ይገኛል ተብሏል።

በዚህ አይነት ጥፋት ከዚህ ቀደምም በተለያዩ የእምነት ተቋማት የተገኙ አባላት ላይ የእርምት እርምጃ ተወስዶ እንደነበረ ዳይሬክተሩ አስታውሰዋል።

ወደፊትም፣ ማንኛውም የሰራዊት አባል የየትኛውም እምነት ተከታይ ቢሆን በእንደዚህ አይነት ተግባር ውስጥ ተሳትፎ ከተገኘ ተጠያቂ ይሆናል ብለዋል።

የእምነት ተቋማትና መላው ህዝብ የመከላከያ ሰራዊቱን ዩኒፎርሙን ለብሶ በእምነት ተቋማት፣ በህዝቡ ዘንድ ነውር በተባሉ የመጠጥ፣ የሱስ፣ የቁማር ወዘተ ቦታዎች የሰራዊት አባልም ሆነ አስመሳይ ዩኒፎርም ለባሽ ሲመለከት እንዲጠቁም ጥሪ አቅርበዋል።

ኮሎኔል ጌትነት፣ ሰራዊታችን በህግ የተቀመጡለትን ትዕዛዞች አክብሮ ግዳጁን ሲወጣ የነበረና እየተወጣ ያለ ተቋም በመሆኑ ይህንንም አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል። #EPA

t.me/geradomedia
522 viewsGashu, edited  05:54
Open / Comment
2021-05-03 08:37:20
አብደላህ ሐምዶክ የግድቡን ጨዋታ በመቀየር ላይ....

አል-አረቢያ የግብፅ ዲፕሎማቲክ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ሰፊ ዘገባ አስነብቧል። ምንጮቹ የሱዳንን አቋም “አደገኛ” ሲሉ ገልፀውታል። በሱዳንና ግብፅ መካከል የተፈጠረው የአቋም ልዩነት የሱዳን ውጭ ጉዳይ ምኒስትሯ ማርያም አል-ማህዲ ከግብፁ አቻ ሳሚህ ሹክሪ በካይሮ ሊያካሂዱት የታቀደው  ስብሰባ እንዲሰረዝ ምክንያት ሆኗል፡፡

ከግብፁ ውጭ ጉዳይ ሳሜህ ሹኩሪ ጋር ለመምከር የሱዳኗ ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ማሪያም ሳዲቅ አል-ማህዲ ወደ ካይሮ ለመጓዝ ጥቂት ሰዓታት ሲቀሩ ስብሰባው በሐምዶክና እሳቸው ባደራጁት የባለ ስልጣናት ጥምረት መሰረዙ ነው ምንጮቹ ለአል-አረቢ የጠቀሱት፡፡

ሐምዶክ የግድቡን አለመግባባት የኃይል ካርድ መፍትሄ አይደለም የሚል አቋም ነው ያላቸው ብሏል ዘገባው። የግብፅ ዲፕሎማቲክ ምንጮች እንዳሉት የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር በግብፅ መንገድ ሲጎዝ የነበረውን የሱዳን ወታደራዊ ባለስልጣናት ላይ ጫና ለማሳደር በሲቪሉ ክንፍ በኩል ተከታታይ ግፊት እያደረጉ ናቸው።

ካርቱም በተፈጠረው ቀውስ ዙሪያ በካይሮ ፍላጎት ተጠልፋ እንዳትወድቅ የራሷ አቋም እንድትጓዝ እየሰሩ መሆኑ የተነገረ ሲሆን ከግብፅ አካሄድ በተለየ ሁኔታ ኢትዮጵያ የሱዳንን ስጋቶች ከግምት እንደምታስገባና ሁለተኛው ሙሊት ከመጀመሩ በፊት ሙሉ የቴክኒክ ቅንጅትና በአተገባበሩ ላይም ከአዲስ አበባ እውነተኛ ዋስትናዎች እንዳሉ ለተለያዩ የሱዳን ባለስልጣናት እያስገነዘቡ ናቸው ተብሏል፡፡

የግድቡ ሁለተኛ ዙር ሙሊት ሁለት ወራት በቀሩት በዚህ ጊዜ አብደላህ ሐምዶክ ከሽግግር ባለ ስልጣናቱ ጫና የተላቀቀ ጠንካራ አመራር በመስጠት ላይ ነው የሚገኙት።

[Esleman Abay - የዓባይ ልጅ]

t.me/geradomedia
701 viewsGashu, 05:37
Open / Comment
2021-05-02 08:14:15
መልካም የፋሲካ በዓል

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የፋሲካ በዓል ይሁንላችሁ እያልን፤ በዓሉን ስታከብሩ ከጎናችን የተለዩ ንፁሃን ወገኖቻችንን፣ ከቤታቸው ተፈናቅለው ሜዳ የወደቁትን፣ የሚወዱትን ተነጥቀው በሀዘን ላይ የሚገኙ ቤተሰቦችን፣ በየሆስፒታሉ የታመሙትን እያሰባችሁ እና ለእናት ሀገራችን ፀሎት እያደረጋችሁ እንድታሳልፉ አደራ እንላለን።

በዚህ በተጨማሪም በዓሉን ስታከብሩ በየዕለቱ የዜጎቻችንን ህይወት እየቀጠፈ ያለውን የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በመጠንቀቅ ይሁን እንላለን።

መልካም የፋሲካ በዓል

t.me/geradomedia
265 viewsGashu, 05:14
Open / Comment
2021-05-01 19:32:20
እንዳትደናገጡ

የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ዛሬ ከለሊቱ 9 ሰዓት ላይ ዘጠኝ ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል። ከዚህ በተጨማሪ በቀጣይ ረቡዕ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይም የአርበኞች ቀንን ምክንያት በማድረግ 21 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ ሚኒስቴሩ አስታውቋል። ህብረተሰቡም ይህንን አውቆ እንዳይደናገጥ እና የጸጥታ አካላትም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

መልካም በዓል

t.me/geradomedia
508 viewsGashu, 16:32
Open / Comment
2021-05-01 14:03:37 ሰበር መረጃ

ሕወሓትን እና ሸኔን በሽብርተኝነት ለመሰየም የሚንስትሮች ምክር ቤት የውሳኔ ሐሳብ አቀረበ።

የውሳኔ ሀሳቡን የያዘው መግለጫ

ባለፉት 3 ዓመታት በኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ እና የመብት መከበር ጥያቄዎች እና ትግል አማካኝነት የመጣውን ለውጥ ለመቀልበስ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በሰላማዊ ዜጎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች ሲፈጸሙ የቆዩ መሆኑ ይታወሳል።

በዚህም ምክንያት የበርካታ ዜጎች ሕይወት ጠፍቷል፣ አካላቸው ጎድሏል፤ እንዲሁም ንብረታቸው ወድሟል፤ ከቀዬአቸውም ተፈናቅለዋል።

እነኚህ ጥቃቶች ኅብረተሰቡ ቀጣይነት ባለው ሥጋት እና ፍርሐት ውስጥ እንዲኖር በማድረግ በመንግሥት ላይ እምነት እንዲያጣ፣ ዜጎች እርስ በእርስ እንዳይተማመኑ አድርጓል።

እነዚህ ሁሉ የሀገረ መንግሥቱን ህልውና አደጋ ላይ ለመጣል ታቅደው ሲፈጸሙ የነበሩ መሆኑን ከተለያዩ ማስረጃዎች ለመረዳት ተችሏል።

እነኚህ ጥቃቶች ከጀርባቸው የፖለቲካ አስተሳሰብን መነሻ በማድረግ እና የፖለቲካ ዓላማን ወይም ግብን ለማሳካት በማሰብ በንጹሐን ዜጎች እና በሕዝብ መሠረተ ልማቶች ላይ ሲፈጸሙ የቆዩ ናቸው።

በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ሲፈጸሙ የቆዩት እነኚህ ጥቃቶች የተለያዩ ፈጻሚ አካላት ነበሯቸው። ከጥቃቶቹ ጀርባ ግን በዕቅድ፤ በገንዘብ፣ በሐሳብ እና በሰው ኃይል ሥልጠና በመደገፍ፤ የሚዲያ ሽፋን እና እገዛ በመስጠት ረገድ የመሪነት ሚናውን ሲጫወቱ የነበሩ ቡድኖች አሉ።

ኢትዮጵያን የማመሰቃቀል፤ የማዳከም እና የማፍረስ ፍላጎት ያላቸው የውጭ ኃይሎች እነዚህን ቡድኖች በቅጥረኝነት እየተጠቀሙባቸው እንድሆነም ግልጽ ነው።

እነኚህ ድርጅቶች ሲፈጸሙና ሲያስፈጽሙ የቆዩዋቸው የጥፋት ተግባራት የሽብር ወንጀል ተግባራት ናቸው። እነዚህ ተግባራት የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው ዐወጅ 1176/2012 አንቀጽ 3 ሥር ስለሽብር የወንጀል ድርጊት የተሰጠውን ትርጓሜ ሙሉ ለሙሉ የሚያሟሉ ተግባራት እንደሆኑ በቀላሉ ለመገንዘብ ይቻላል።

እነዚህን የሽብር ተግባራት የፈጽሙ ድርጅቶች አባላትና እና ደጋፊዎቻቸውን እንደ ግለሰብ በተናጠል በሽብር ወንጀል ተጠያቂ ከማድረግ ይልቅ ድርጅቶቹን የሽብርተኛ ድርጅት አድርጎ በመሰየም በሕጉ በተቀመጠው አግባብ የሽብር ወንጀል ድርጊትን በተሻለ ሁኔታ ለመቆጣጠር እና ለመከላከል ይችላል።

ስለዚህ የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው ዐዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀጽ 18 እና 19 መሠረት “ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሓት)” እና “ሸኔ” የሽብር ወንጀልን ዓላማቸው አድርገው የሚንቀሳቀሱ በመሆኑና የድርጅቶቹ የሥራ አመራር ወይም ወሳኔ ሰጭ አካላት ወንጀሉን አምነው የተቀበሉት ወይም አፈጻጸሙን እየመሩት በመሆኑ፤ የሽብር ተግባር መፈጸምም የድርጅቶቹ ጠቅላላ መገለጫ በመሆኑ፤ ድርጅቶቹ በሽብርተኛ ድርጅትነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሐሳብ ቀርቧል።

እንዲሁም የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው ዐዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀጽ 23 መሠረት በተመሳሳይ ተግባር በተሰማሩ እና በዚህ ውሳኔ ሐሳብ መሠረት ከተሰየሙት የሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ትብብር፤ ትሥሥር ወይም የሐሳብ እና የተግባር ዝምድና ያላቸው ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይም ይህ ውሳኔ ሐሳብ ተፈጻሚ ይሆናል።

የሚኒስትሮች ም/ቤት
ሚያዚያ 23/2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ

t.me/geradomedia
414 viewsKedir Ahmed, edited  11:03
Open / Comment