Get Mystery Box with random crypto!

ገራዶ ሚዲያ

Logo of telegram channel geradomedia — ገራዶ ሚዲያ
Logo of telegram channel geradomedia — ገራዶ ሚዲያ
Channel address: @geradomedia
Categories: News
Language: English
Subscribers: 679
Description from channel

🔸ሁሉን አቀፍ የመረጃ ምንጭ!🔸
✍ ፃፉልን @geradomediabot
fb.com/geradomedia
twitter.com/geradomedia

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages 3

2021-05-04 23:01:09
አፍጥረናል!

አገራችን ደሴ፣ ግሸን ነው ደብራችን፣
በረመዳን ሰሞን፣
እናፍጥር ብለውን፣ ጠርተውን ሼሃችን፣
የመፍቀሬ ልጆች፣
አረብ ገንዳ በታች፣
አብረን አፍጥረናል፣ ከነ መስቀላችን።

ይኸው ነው።


ጃኖ መንግስቱ ዘገየ ዘ-ወሎ

t.me/geradomedia
1.1K viewsGashu, 20:01
Open / Comment
2021-05-04 21:39:50
ልጆቻችሁን ስታሳድጉ ዶክተር ወይም ፕሮፌሰር እንዲሆኑ አትምከሯቸው፥ መጀመርያ ሰው እንዲሆኑ ምከሯቸው፤ ምክንያቱም መጀመርያ ሰው ሳይሆኑ ዶክተርና ፕሮፌሰር የሆኑ ብዙ አሉና። - ፕ/ር ምህረቱ ሻንቆ

እስኪ መጀመርያ ሰው እንሁን!

t.me/geradomedia
163 viewsKedir Ahmed, 18:39
Open / Comment
2021-05-04 21:39:41
አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ

ከኦሮሚያ ክልል (ወለጋ) ተፈናቅለው ወደ ወሎ ተፈናቅለው ለመጡ ወገኖች ለመርዳት ገቢ ማሰባሰቢያ የቴሌግራም ግሩፕ የተከፈተ ሲሆን፤ ሁላችንም ከዚህ በታች ባለው የባንክ አካውንትም የተቻለንን እንርዳቸው።

የቴሌግራም ግሩፕ ሊንክ t.me/joinchat/-Dr7aZIKk0YwNzc8

ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር -1000394395475
የአካውንት ስም - Kassaw Tamene, Endalkachew Belayneh & Ahmed Ali

#የቻልነውን_እናድርግ
139 viewsKedir Ahmed, 18:39
Open / Comment
2021-05-04 21:39:28
የሰብዓዊ ድጋፍ ጥሪ

በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በትግራይ ክልል በርካታ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል። እስካሁን እየተደረገ ያለው ድጋፍ ከእርዳታ ፈላጊው ቁጥር አንፃር ገና የሚቀረው በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሃላፊነቱን እንድወጣ ጥሪ እየቀረበ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበርም እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች በገንዘብ መደገፍ ለሚፈልጉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000000902008 ላይ ማስገባት እንደሚችሉ ምስህበሩ ገልጿል። በአይነት መደገፍ ለሚፈልጉ ደግሞ በማህበሩ ብሄራዊ ፅህፈት ቤት እና በሁሉም የቀይ መስቀል ቅርንጫፎች በመሄድ መለገስ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ስለ ቀይ መስቀል ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ደግሞ 0946659969 / 0911411719 መደወል ይቻላል።

ሁላችንም በችግር ላይ ለሚገኙ ወገኖቻችን እንድረስላቸው!

t.me/geradomedia
141 viewsKedir Ahmed, 18:39
Open / Comment
2021-05-04 19:53:35
የጎዳና ላይ ኢፍጣር በደሴ......

ደሴ ከተማ ዛሬ በደሴ ከተማ ሙስሊም ወጣቶች ማህበር አስተባባሪነት የጎዳና/አደባባይ ላይ ኢፍጣርን ባማረ ሁኔታ አስተናግዳለች። በኢፍጣር ዝግጅቱ ላይ ከእስልምና እምነት ተከታዮች በተጨማሪ የክርስትና እምነት ተከታዮችና አቅመ ደካሞች ታድመዋል።

#ወሎ #ደሴ

t.me/geradomedia
133 viewsKedir Ahmed, edited  16:53
Open / Comment
2021-05-04 19:21:48
በትግራይ ያለዉ ቀዉስ 5ሺ ህጻናትን ከወላጆቻቸዉ እንደነጠለ ሴቭ ዘ-ችልድረን አስታወቀ!

ዓለም አቀፉ የረድኤት ተቋም ሴቭ ዘ-ችልድረን እንዳስታወቀዉ በሰሜን ኢትዮጲያ ትግራይ ክልል ያለዉ ቀዉስ 5ሺ ህጻናትን ከወላጆቻቸዉ እንደነጠለ ይፋ አድርጓል፡፡ በርካታ ህጻናት ከቤተሰቦቻቸዉ ከተነጠሉ በኃላ በስደተኞች መጠለያ ጣቢያ አልያም ይፋዊ ባልሆነ ስፍራ ተሸሽገዉ ይገኛሉ፡፡

ዓለም አቀፉ የረድኤት ተቋም ሴቭ ዘ-ችልድረን እንደሚለዉ እነዚሁ ህጻናት ለረሃብ፣ ለወሲባዊ ጥቃትና ለአካላዊ ጉዳት ሰለባ ስለመሆናቸዉ በሪፖርቱ ዉስጥ ተካቷል፡፡ የረድኤት ተቋማት ወደ ተጎጂዎች ስፍራ ለመድረስ አሁንም እንዳልተቻላቸዉ በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡

#ትኩረት

t.me/geradomedia
704 viewsGashu, edited  16:21
Open / Comment
2021-05-04 19:21:38
ይደውሉ - 0930613856

ቤትዎን በጅብሰም፣ ቀለም እና ግራናይት ባማረ ሁኔታ እናሳምራለን! አሁኑኑ ይደውሉልን!‌‌

We will beautify your home with plaster, paint and granite! Call us now!‌‌


Call - 0930613856
688 viewsGashu, 16:21
Open / Comment
2021-05-04 16:04:49
የአቶ አበረ አዳሙ ህልፈተ ህይዎት ምክንያት......?

አቶ አበረ አዳሙ ዛሬ ጠዋት የህመም ስሜት ተሰማኝ ብለው ወደ ሆስፒታል ሄደው፤ በድንገተኛ ህክምና ላይ እንዳሉ በልብ ህመም ችግር ምክንያት ነው ህይወታቸው ማለፉን የሆስፒታል ምንጮች የገለፁት። #EBC

t.me/geradomedia
840 viewsGashu, 13:04
Open / Comment
2021-05-04 15:48:31
አቶ አበረ አዳሙ ህይወታቸው አለፈ!

የቀድሞ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ በድንገተኛ ህመም ህይዎታቸው ማለፉ ተሰማ። አቶ አበረ አዳሙ ከጥቂት ቀናት በፊት ነበር ከአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ኃላፊነት የተነሱት። #Tikvah

t.me/geradomedia
218 viewsGashu, 12:48
Open / Comment