Get Mystery Box with random crypto!

ገራዶ ሚዲያ

Logo of telegram channel geradomedia — ገራዶ ሚዲያ
Logo of telegram channel geradomedia — ገራዶ ሚዲያ
Channel address: @geradomedia
Categories: News
Language: English
Subscribers: 679
Description from channel

🔸ሁሉን አቀፍ የመረጃ ምንጭ!🔸
✍ ፃፉልን @geradomediabot
fb.com/geradomedia
twitter.com/geradomedia

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages 10

2021-04-25 13:16:36
ማስታወቂያ ማሰራት ለምትፈልጉ

- እዚህ ቻናል ላይ ምርትና አገልግሎታችሁን ማስተዋወቅ የምትፈልጉ @geradomediabot ወይም @gashaw02 ላይ አናግሩን!
162 viewsGashu, 10:16
Open / Comment
2021-04-25 11:40:33
#ሆሳዓና

የክርስትና እምነት ተከታይ ለሆናችሁ የቻናላችን ቤተሰቦች በያላችሁበት መልካም የሆሳዓና በዓል ይሁንላችሁ!

የእምነታችንን ትዕዛዝ በአግባቡ ለመፈፀም የሀገር ሰላም መሆን በእጅጉ ስለሚያስፈልግ፤ ወቅቱ ደግሞ የረመዷንና የአብይ ፆም በመሆኑ ለሀገራችን ሰላምና አንድነት በፀሎት/ዱዓ እንበርታ እንላለን!

t.me/geradomedia
45 viewsGashu, 08:40
Open / Comment
2021-04-25 11:00:41
495 viewsGashu, 08:00
Open / Comment
2021-04-25 10:35:34
የኢትዮጵያ እውነት ያሸንፋል!!!!

በኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድባችን (#GERD) ዙሪያ ይጠበቅ የነበረው ክርክር ተካሄዷል:: ሚሊዮኖች በቀጥታ ስርጭት በሚከታተሉት በአልጀዚራ "Scenario" በሚባል ታዋቂ ፕሮግራም ላይ በተካሄደው በዚህ ክርክር ላይ፣ ዛሬም የኢትዮጵያ ሃሳብ አሸናፊ ሆኖ የወጣበት መሆኑ ታውቋል!!!!

በዚህ የክርክር ፕሮግራም ላይ ግብፅም ሱዳንም አሉኝ የሚሏቸውን የፖለቲካ ተንታኞች ያሳተፉ ሲሆን ፕሮግራሙን ለየት የሚያደርገው ደግሞ በቅርቡ ከኢትዮጵያ የተባረረው የኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ ተንታኝ እና የጁንታው ወዳጅ የሆነው ዊሊያም ዴቪሰን ተካፋይ የነበረበት ክርክር መሆኑ ነው፡፡

በኛ በኩል ደግሞ የምስራቅ አፍሪካ የፖለቲካ ተንታኝ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሌክቸረር የሆነው ጀግናው ወንድማችን ዶክተር ሳሙኤል ተፈራ ኢትዮጵያችንን ወክሎ ተሰልፏል!!! ተሟግቷል!!! በብርቱ ተጋድሏል!!!! በጠላት ወገን የቆሙትን ወደረኞቹን ሃቅን ይዞ ተፋልሟል!!!! የኢትዮጵያ አምላክም ረድቶታል!!!! የኢትዮጵያ ሃሳብ አሸናፊ ሆኖ ወጥቷል!!!!

እውነት ያሸንፋል!!!!
ኢትዮጵያ ታሸንፋለች!!!!
የህዳሴው ግድብ ዲጂታል ሰራዊት ክብሩልን!!!!
ጀግኖቻችን እንወዳችኃለን!!!! እናከብራችኃለን

የክርክሩን #አማርኛ ትርጉም ቆየት ብለን እናቀርባለን!

Via Dejene Assefa

t.me/geradomedia
728 viewsGashu, edited  07:35
Open / Comment
2021-04-24 21:24:11
#ኮቪድ_በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ250 ሺህ አለፈ!

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 8,869 የላብራቶሪ ምርመራ 1,663 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። በዚህም በኢትዮጵያ ውስጥ በኮቪድ-19 የተያዙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር 250,955 ደርሷል።

በተመሳሳይ በ24 ሰዓት 20 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል በዚህም አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 3,531 ደርሷል። 1,933 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን፤ በዚህም በአጠቃላይ በሀገራችን ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች 190,013 ደርሰዋል። 987 ሰዎች ደግሞ በበሽታው በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ

t.me/geradomedia
773 viewsGashu, 18:24
Open / Comment
2021-04-24 21:23:54 ይህችን ምርጥ ቻናል ተቀላቀሏት! የፈለጋችሁትን ታገኙባታላችሁ!

ለመቀላቀል t.me/joinchat/RAn9b5UCOVFhyJKe
715 viewsGashu, edited  18:23
Open / Comment
2021-04-24 12:52:44 #ከመግለጫው_የተወሰደ

- ሀገራችን ያሉባት ችግሮች ምንም ያህል እንደ ምድር አሸዋ ቢበዙ ፈጽሞ ከዜጎቿ አቅም በላይ እንደማይሆኑ ጽኑ እምነት አለን። የሚፈቱትም ተነጣጥለን ሳይሆን በአንድነትና በትብብር እንደሆነ ገና ከጅምሩ አሳውቀናል።

- የጠላቶቻችን ፍላጎት በጉዞአችን መሐል ወድቀን ግባችንን ሳናሳካ እንድንቀር ነው። በጋራ ቆመን ያጸናነው ቤታችን ፈራርሶ ወደ ትቢያነት ሲቀየር ማየት እንደሚሹ በመግለጽ እኛ ደግሞ ለዚያ የተመቸን ሆነንላቸዋል።

- የትኛውንም ዓይነት ጫና ተቋቁመን፤ የውስጥና የውጭ ፈተናዎቻችንን አልፈን የህዳሴውን ግድብ እንሞላዋለን።

- የወገኖቻችን አሲቃቂ ግድያ፣ ማፈናቀል፣ ቤትና ንብረት ማውደም፣ ነውጥና ሸፍጥ ሁሉ በሀገር ውስጥ ብቻ የተመረተ አይደለም።

- የገጠሙን ችግሮች እንኳን እርስ በእርስ እየተጓተትን ቀርቶ አንድ ሆነንም በጥቂት ዓመታት ውስጥ ድምጥማጣቸው የሚጠፋ አይደለም።

- መጀመሪያ በውስጣችን ያሉትን ባለ ሁለት ቢላዋዎች እናጸዳለን። ቀን ቀን ለኢትዮጵያ የሚሠሩ የሚመስሉ፤ ሌሊት ሌሊት በኢትዮጵያ ላይ የሚዶልቱ አሉ። እነርሱ ከውጭ ጠላቶቻችን በላይ ዋነኞቹ ጠላቶቻችን ናቸው፡፡

- የሚደረጉ ማናቸውም የፖለቲካና የመብት እንቅስቃሴዎች ይደገፋሉ። የትግላችን ውጤቶች ናቸውና፡፡ እነዚህ የመብትና የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ግን ኢትዮጵያን እንዲያናውጡ አንፈቅድም።

- ፖለቲካዊ ጨዋታውን ከጨዋታ ሜዳ ውጭ ለማድረግ ለሚፈልጉት ኃይሎች፣ ትእግሥታችን ማለቁን በዚሁ አጋጣሚ ልንነግራቸው አንፈልጋለን።

- አጥር ላይ ተቀምጠው፣ አሸናፊውን አይተው፣ ከተመቻቸው ሊገቡ፣ ካልተቻቸው ሊሸሹ የሚያስቡ መኖራቸውን አውቀናል። ወቅቱ የምርጫ ነውና መምረጥ አለብን። ወይ እነርሱን እናጸዳለን ወይ ኢትዮጵያን አሳልፈን እንሰጣለን። የኛ ምርጫ ኢትዮጵያን ለእነርሱ ስንል መሠዋት ሳይሆን፤ እነርሱን ለኢትዮጵያ ስንል መሠዋት ነው።

- ኢትዮጵያ ማሸነፏ ላይቀር እንዳታሸንፍ ሲታገሉ የኖሩትን ትታዘባቸዋለች፤ በታሪክ ሂደትም ትቀጣቸዋለች። እርሷ ግን ወጥመዱን በጣጥሳ፣ ሰንኮፉን ነቃቅላ፣ አዚሙን አስወግዳ ያሰበችበት ትደርሳለች።

- ቆም ብለን እናስብ፤ ከሁሉም በፊት ኢትዮጵያን እናስቀድም።

t.me/geradomedia
294 viewsGashu, 09:52
Open / Comment
2021-04-24 11:47:06
1 viewGashu, 08:47
Open / Comment
2021-04-24 11:46:52 ይህችን ምርጥ ቻናል ተቀላቀሏት! የፈለጋችሁትን ታገኙባታላችሁ!

ለመቀላቀል t.me/joinchat/RAn9b5UCOVFhyJKe
2 viewsGashu, edited  08:46
Open / Comment
2021-04-24 09:43:14
ምግብማ ሞልቷል፤ ያነሰን ፍቅር ነው!
.
t.me/geradomedia
80 viewsGashu, 06:43
Open / Comment