Get Mystery Box with random crypto!

ገራዶ ሚዲያ

Logo of telegram channel geradomedia — ገራዶ ሚዲያ
Logo of telegram channel geradomedia — ገራዶ ሚዲያ
Channel address: @geradomedia
Categories: News
Language: English
Subscribers: 679
Description from channel

🔸ሁሉን አቀፍ የመረጃ ምንጭ!🔸
✍ ፃፉልን @geradomediabot
fb.com/geradomedia
twitter.com/geradomedia

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages 7

2021-04-30 10:21:41
የዩኒቨርስቲ ገቢ ተማሪዎች ምደባ ተለቀቀ!

የ2013 ትምህርት ዘመን የአስራ ሁለተኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው የዩኒቨርስቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከዛሬ ሚያዝያ 21/2013 ጀምሮ ይፋ ሆኗል። ዩኒቨርሲቲዎች እስከ ሚያዝያ 30/2013 ድረስ ተገቢውን ዝግጅት አድርገው የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርሃ ግብር የሚያሳዉቁ በመሆኑ ተማሪዎች አስፈላጊዉን ዝግጅት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

ዉጤት ለማየት መግቢያ ዌብሳይት፦ http://result.neaea.gov.et/Home/Placement

t.me/geradomedia
152 viewsGashu, 07:21
Open / Comment
2021-04-30 09:35:56
#ስቅለት

የስቅለት በዓል በክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች እየተከበረ ነው፡፡

በዓሉ በክርስትና እምነቶች በስግድት እና በፀሎት ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡ በተለይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በስግደትና በየጾም የስቅለት በዓል የሚታወስ ሲሆን በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች ተከብሮ ይውላል፡፡

መልካም የስቅለት በዓል

t.me/geradomedia
121 viewsGashu, 06:35
Open / Comment
2021-04-29 15:19:55
የሦስቱ በሬዎች መጨረሻና የእኛ ኢትዮጵያዊያን ነገር.....

(በገራዶ ሚዲያ)

የተለያየ ቀለም ያላቸው ሦስት በሬዎች (ቀይ፣ ነጭ፣ ጥቁር በሬ) ለአመታት በህብረት/በአንድነት ይኖሩ ነበር። ከዕለታት በአንድ ቀን ምሽት ላይ ሊበላቸው ያሰበ አንድ ጅብ ከሚኖሩበት ቦታ ይመጣል። ነገር ግን እነሱን ለመብላት ሲያስብ ህብረታቸው አስፈራው። አንድ መላም ዘየደ፤ ቀስ አድርጎ እያንዳንዳቸውን ተራ በተራ ለመብላት። ይህ ጅብ ለጥቁሩና ለቀዩ በሬም "ይህ ነጩ በሬ ማታ ላይ ከሩቅ ይታያል፤ አደጋ ያመጣባችኋል። ከእሱ ልትርቁ ይገባል!" ሲል ነገራቸው።

ቀዩና ጥቁሩ በሬም ከነጩ ተነጥለው መኖር ጀመሩ። ጅብም ያንን ነጭ በሬ ብቻውን ስላገኘው በላው፤ ነጩን በሬ በልቶ ሲጨርስም ወደ ቀዩና ጥቁሩ በሬ በመሄድ አሁንም "ይሄ ቀይ በሬ በጨረቃ ሲያዩት ከሩቅ ያብለጨልጫል፤ አደጋ ስለሚያመጣብህ ከእሱ ልትርቅ ይገባል" ሲል ለጥቁሩ በሬ ነገረው።

ጥቁሩ በሬም ከቀዩ በሬ ተነጥሎ መኖር ጀመረ። ጅብም ያንን ቀይ በሬ ብቻውን ስላገኘው በላው፤ ቀዩን በሬ በልቶ ሲጨርስም እነሆ ተራው የጥቁሩ በሬ ነውና ጥቁሩንም በሬ በላው። በሬዎቹም ተበልተው አለቁ።

ከዚህ ታሪክ እንደምንረዳው ጅብ በሬዎቹ በህብረት እንደነበሩ ለመብላት ፈርቶ ነበር። ለመነጣጠል ሞከረ፤ ተሳክቶለት በላቸው። እኛ የተለያየ እምነት፣ ቋንቋ፣ ዘርና የመሳሰሉት ልዩነቶች ያሉን ኢትዮጵያዊያንም ለመነጣጠል የሚመጣን ጠላት አሜን ብለን ከተቀበልን ሁላችንም መጥፋታችን አይቀርም። "ጠላት እኛን ለመብላት ያመቸው ዘንድ መነጣጠልን/መለያየትን ይወዳል!" ከነልዩነቶቻችን በህብረት እንቁም! እንደበሬዎቹ አንሁን! ብሄር፣ እምነት፣ ዘር... ሳንለይ በአንድነት እንቁም። ጠላት አሰፍስፎብናል!

እንደበሬዎቹ እንዳንሆን በህብረት እንቁም!

t.me/geradomedia
323 viewsGashu, 12:19
Open / Comment
2021-04-29 12:51:02
ወቅታዊ ሁኔታ ስለ አጣዬ፣ ከሚሴ፣ ሸዋ ሮቢት.......

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ እና የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች በቅርቡ ተፈጥሮ የነበረው ችግር ተረጋግቶ አካባቢው ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሱን የአካባቢው ኮማንድ ፖስት አስታወቀ። አጥፊዎችን የመለየትና በህግ ተጠያቂ የማድረግ ሥራዎችም እየተከናወኑ ነው ብሏል።

የኮማንድ ፖስቱ አስተባባሪ ሌተናል ጄኔራል ደስታ አቢቼ ለኢዜአ በሰጡት መግለጫ ኮማንድ ፖስቱ ግዳጅ ከተሰጠው ጀምሮ አካባቢው ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲመለስ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። ግጭትና ጸብ አጫሪነትን እንዲሁም መንገድ መዝጋትን በማስቆም የተቋረጡ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና አስተዳደራዊ ሥራዎች እንዲጀመሩ የማድረግ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

የተፈናቀሉ ሰዎችን ወደ ቀዬአቸው የመመለስና አጥፊዎችን ለይቶ ለህግ እንዲቀርቡ የማድረግ ሥራም ከኮማንድ ፖስቱ ተግባራት መካከል መሆናቸውን ጠቅሰዋል። በእነዚህ ላይ አተኩሮ በመሰራቱም በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ግጭትና የወንጀል ድርጊቶች መቆማቸውን ነው የተናገሩት።

አካባቢው የተረጋጋ እንቅስቃሴ እየታየበት በመሆኑ ተቋርጠው የነበሩ የስልክ፣ የውሃና የኤሌክትሪክ አገልግሎቶች እንድሁም የትራንስፖርትና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን ገልጸዋል።

አስተባባሪው እንዳሉት አጥፊዎችን በፍጥነት የመለየትና በህግ ተጠያቂ የማድረግ ሥራዎችም እየተከናወኑ ይገኛሉ። ህዝቡ ሰላም ፈላጊ መሆኑን ገልጸው፤ ከመንግስት ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን አመልክተዋል።

በአካባቢው ተከስቶ በነበረው ችግር የተለያዩ የአገር ውስጥና የውጭ አካላት፣ የፖለቲካ ድርጅቶችና የመንግስት መዋቅር እጅ እንዳለበት መታወቁንና በቀጣይ በማስረጃ የተደገፉ መረጃዎች የማሰባሰብ ሥራ እንደሚሰራ አስተባባሪው ገልጸዋል። #ENA

t.me/geradomedia
58 viewsGashu, 09:51
Open / Comment
2021-04-28 21:20:26
ንቁ! ንቃ! ንቂ!

ጠላቶቻችን የሶሪያን የውርደት ፅዋ ሊግቱን ዝተዋል! እርስ በእርስ አዳምተው ደማችንን ሊጠጡ፤ እንደ ቀትር ጋኔን ጥፍሮቻቸውን አንጨፍርረው አሰፍስፈዋልና ንቁ! ንቃ! ንቂ!

t.me/geradomedia
548 viewsGashu, 18:20
Open / Comment
2021-04-28 19:54:24
"ወደ ህዳሴው ግድብ ሲጓዙ የነበሩ 10 አሽከርካሪዎች ተገደሉ የሚለው መረጃ ሐሰት ነው!" - ሜ/ጄ አስራት ዴኔሮ

ወደ ህዳሴው ግድብ እቃ ጭነው ሲጓዙ የነበሩ “10 አሽከርካሪዎች ተገድለዋል" ተብሎ የተሰራጨው መረጃ የሐሰት መሆንኑን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሜጀር ጀነራል አስራት ዴኔሮ ነው” ገለፁ። ጄነራሉ አክለውም “በትናንትናው ዕለት ከ70 በላይ አሽከርካሪዎች ወደ ህዳሴው ግድብ የተለያዩ እቃዎችን እና ማሽነሪዎችን ያለምንም ችግር አድርሰዋል" ሲሉ ለአል ዓይን ተናግረዋል።

t.me/geradomedia
583 viewsGashu, 16:54
Open / Comment
2021-04-28 13:57:39
አዲሱ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር...

በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርነት ሲያገለግሉ የነበሩት ተኮላ አይፎክሩ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽንን እንዲመሩ መሾማቸው ታወቀ።

አቶ ተኮላ ከትናንት ሚያዚያ 19/2013 ዓ.ም ጀምሮ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው መመደባቸው ታውቋል። የቀድሞው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ከሁለት ዓመታት በላይ በኃላፊነቱ ሲሰሩ ቆይተዋል።

በቅርቡ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶችና በተፈፀሙ ጥቃቶች የበርካታ ሰዎች ሕይወት መጥፋቱንና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ ነው አቶ ተኮላ በአቶ አበረ አዳሙ ምትክ ወደ ኃላፊነት የመጡት።

ከ3 ዓመት በፊት በፌደራል ፖሊስ ውስጥ በኃላፊነት ከመመደባቸው አስቀድሞ በአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በተለያዩ ቦታዎች አገልግለዋል። በደቡብ ወሎ ዞን የኮምቦልቻ ከተማ ፖሊስ አዛዥ፣ የአምባሰል ወረዳ፣ የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሆነው ሠርተዋል። #BBC

t.me/geradomedia
598 viewsGashu, 10:57
Open / Comment
2021-04-28 10:40:15
"ኢትዮጵያ ጠንክሪ!" - ሱዳናዊቷ ጋዜጠኛ ሱሀይር አብዱረህማን

ሰዎቹ እንኳን ችግር ላይ ሆነህ ይቅርና እንዲሁም ሰላም ሆነህ አይተውሁም። ተንኮል እና ክፋት አብሯቸው ያደገ ነው። አንተ ቤት እሳት ቢነድ እሳቱን ለማጥፋት ውሀ ስጡኝ ብትላቸው አይሰጡህም።

አሁን ግብፆች በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ያሉትን እሳቶች እንዴት አድርገን ማቀጣጠል አለብን የሚል የክፋት ቤንዚናቸውን ስለማርከፍከፍ እያወሩ ነው። የቴሌቪዥን ቻናሎቻቸውን ብትከፍቱት፤ የፌስቡክ ገፆቻቸውን ብትፈትሹ ጋዜጣቸውን ብታገልብጡት፣ ሁሉም የሚያወሩት ኢትዮጵያ አሁን ላይ በሀገር ውስጥ ችግር ስለተያዘች እንዴት እናፍርሳት/እናጥፋት እንጅ እንዴት ሰላሟን መመለስ እንዳለበት "በምን እንገዛት" የሚል፣ ሀሳብ አታገኙባቸውም። ይገርማል!

እነሱ ለኢትዮጵያ ብቻ አይደለም እንዲህ የሚከፉት፣ ሱዳንን ለሁለት ሰንጠቀዋል። ሊበያን አፍረሰዋል። ከበረሀ የፈለቀ ውሀ ወደ ፊሊስጤም መሬት እንዳሄድ በአሽዋ ደፍነዋል። በረሃብ ላይ ያሉ ፍልስጤማውያን ወደ አገራቸው እንዳይገቡ ድንበራቸውን ዘግተዋል። ኧረ ምን ተዘርዝሮ ያልቃል።

እንደለመዱት የአባይን ውሀ በብቸኝነት ለማፈስ፣ ሲሉ ኢትዮጵያ ከማፈረስ ወደኋላ አይሉም። በመካካለኛው ምስራቅና በአፍሪካ ብቸኞቹ የመድሀኒት አምራች አገር ዘመናዊ የኢንዱስትሪ አገር፣ የአትክልት አምራች አገር፣ ጠንካራ ሚሊተሪ ያላት አገር ለመሆን ሲሉ ሁሉንም ክፋቶቻቸውን፣ ካደጉበት ሴራቸው ልምድ ወስደው አይፈፅሙትም አይባልም።

ለዚህም መድሃኒቱ፣ ኢትዮጵያ ጠንካራ ሆና መታየት ብቻ ነው! የነሱን ሴራና የነሱን ማንነት ከወዲሁ ተረድቶ የነሱን ሴራና የነሱን የጥፋት አላማ ማክሸፍ የመላው ኢትዮጵያዊያን የጋራ ስራ ይሆናል።

ሰላም ለጎረቤታችን አገር ኢትዮጵያ!
ጋዜጠኛ ሱሀይር አብዱረህማን

በሱሌማን አብደላ

t.me/geradomedia
727 viewsGashu, 07:40
Open / Comment