Get Mystery Box with random crypto!

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 128.91K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
Buy ads: https://telega.io/c/bewketuseyoum19
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 196

2021-11-13 15:11:01 እናቴ
ጀግናዬ ነሽ
መከታ አለኝታዬም ነሽ
ክብርሽን የጠበቅሽ
እራስሽን ያላስደፈርሽ
የሴቶች ተምሳሌት
ምሳሌ የአንድነት
የፍቅር አብነት
የሠላም ማብሰሪያ
የፍቅር መጀመሪያ
የደግነት ጥግ አንቺ ነሽ
ደከመኝ ሰለቸኝ
ተራብኩ ተጠማሁኝ
ጫማ ልብስ አጣሁኝ
ሳቲዪ ተሸነፍኩኝ
እያልሽ አሸነፍኩኝ
አልፋለው እሄም ቀን ያልፋል
መከራ ችግርም ይሄዳል
ድህነትም ይሰደዳል
ፍቅርም ይመጣል
ሰላምም ይሰፍናል
ብለሽ እዚህ ደረስሽ
ሁሉንም ችግር አልፈሽ
መከራንም ተሻግረሽ
ችግርን አሸንፈሽ
ድህነትን ተቋቁመሽ
ጥላቻን አስወግደሽ
በፍቅር ከሁሉም በልጠሽ
በትዳርሽ የተሳካልሽ
በብልሃት በዘዴ ከሁሉም በላጭ ነሽ
የኔ እናት ፍቅር ነሽ
ስምሽ ይጣፍጣል ሲሉት ወላንሳ
ግርማ ሞገስ አለው እንደ አንበሳ
አልፈሽ ያን ሁሉ አበሳ
እዚ ላይ መድረስሽ ይገርመኛል ወላንሳ
በደግነትሽ ያልተገኘልሽ አቻ
ለችግር ሁሉ ያለሽ መፍቻ
ለተዘጋ በር የማታጪ መክፈቻ
እንዳንቺ ላሉ ሴቶች የምትሰጪ ማበረታቻ
እናቴ መሠረቴ
እምዬ ሀብቴ
ላኑርሽ ከቤቴ
ነሽና በረከቴ
ልጡርሽ ዘላለም
እንዳንቺ ለኔ የሆነ የለም
ኑሪልኝ ለዘላለም
እድሜ ይስጥሽ ጤና
ለዘላለም በቤቴ ላኑርሽ ይሳካልኝና
ውለታሽ ብዙ ነው
የማያልቅ ብከፍለው
አነጋገርሽ የሆነ ረቂቅ
ቅኔሽ ልብ የሚሰርቅ
ፈገግታ ሳቅሽ የሚናፈቅ
የሰጠሽኝ ፍቅር የማይሰረቅ
ምን ልበልሽ ቃል አጠው
ምን ላርግልሽ አቅም አገኘው
ውለታሽን በምን ልክፈለው መክፈያ አጣው
የማታ ማታ
አረፍ ስል ከመኝታ
ሁሌም በሄድኩበት ቦታ
ትመጫለሽ በትዝታ
ብትለዪኝ ላፍታ
ይጠፋል ከኔ ደስታ
ሌላ ምን እላለው እንዲ ልበል እንጂ
እናቴ ይስጥሽ ጤና
እድሜም ይጨምርና
ፍቅር አይንፈግሽ
ሰላምም ይስጥሽ
ለዘላለም ኑሪልኝ ስለምወድሽ
እፈልጋለው እናትነትሽን
እናፍቃለሁ ደግነትሽን
እናቴ እምዬ ለዘላለም ኑሪልኝ
እወድሻለሁ ሁሌ ካጠገቤ ሁኚልኝ
አምላክ እድሜ ይስጥሽ ቆዪልኝ
ገጣሚ
ሜሮን ሲሳይ
2.4K viewsAbela, 12:11
Open / Comment
2021-11-13 07:33:51 ውበት አገነፋሽ ሰቶሽ ማጣቀሻ
ለኔ ለኔ ሲሆን ከለከልሽኝ ቅምሻ
መዐዛሽስ ይብስ ቀርቦ ለሚምገው
አፋንጫ ላይ ፍንጭት ወስዶ ነው ሚልገው
ፀጉርሽ ከሀሩሩ አይኔን እየገፋ
በሳቅ ያለቀሽው ልቤ ውስጥ አካፋ

ብቻ ግን

ጠብቅልኝ ብዬ የፀለይኩኝ ጊዜ
ሚጠብቃት መልአክ አጋባኝ ትካዜ
የለት ጥበቃውን ሲከውን በዋርካው
ፈላጊዋ እንዳይሆን ከኔ በላይ ማርካው!?


ናታን_ኤርሚያስ
@UniqueDy
350 viewsAbela, 04:33
Open / Comment
2021-11-12 17:54:31 የገጠሯ ብርሃን

የገጠሯ ብርሃን እኔ ነኝ
እኔ ነኝ ለእነሱ ያለሁኝ
እኔ ሴቷ ጠንክሬ በገጠር
ሰርቼ በርትቼ ለሀገር
የገጠርን ጭቃ ላደርገው እስፓልት
የገጠርን ኩራዝ
ላደርገውየአምፖልመብራት
የገጠርን ጎጆ ልሰራው አድርጌ ቆርቆሮቤት
ኩሬና ወንዙን ልቀይረው ወደ ንፁህ ውሃነት
ባህልና ወጌን ሳልዘነጋ ሳልረሳው
እቅድ ተስፋ አለኝ እኔው
እቅዴ እንዳይቀር ወድቆ እንዳይሆን መና
ተስፋዬም እንዳይጨልም እሠራለው ገና
እማማ እና አባባ እንዳይቆጡኝ
ሳልል ጫማ ልብስ ሳልል ተራብኩ ተጠማሁኝ
ቢከብድም የገጠሩ ኑሮና ሰራ
የገጠሩ ኑሮና ስራ ከላይ ለሚያየው
ቀላል ነው የሚመስለው
ውስጥ ገብቶ ላየው ግን በጣም ነው
የሚከብደው
ጥዋት ትነሳና ትሰራለች ቁርሱን
እሷ ሳትበላ ታበላለች ቤተሰቧን
ቧንቧ ስለሌለ ወንዝ ነው የምትሄደው
ወንዝም ሄዳ አያልቅ ፈተናው
ሲያስቸግራት ጎረምሳው
ሲያስቸግራት ኮረብታው
ዳገት ቁልቁለቱን
ተራራ አቀበቱን
ስትወጣ በብርታቷ
ስትሄድ በደግነቷ
ውሃውን አግኝታው
ስትመለስ ቀድታው
ሲሰበር ማሰሮው
በጎረምሣው ዱላ
ያ ሁሉ ድካም ይቀራል መና
ቤተሰቦቿም ይቆጧታል ገና
ወዳ አላመጣችው በውበቷ ስትለከፍ
እሷ ጎን ለወንዶች ውበት አትክለፈለፍ
ወንዶቹ በሙሉ ይፈልጓታል እንጂ
ያን ሁሉ ጫና ችላ ተቋቁማው
ሳትል ወዲህ ወዲያ ስትል ወደስራው
እንጀራውን ጋግራው ስትሰራ ወጡን
ከስራዋ እኩል እያስኬደች ትምህርቷን
መብራት የለምና በኩራዝ አጥንታ
ጠዋት ተነስታ ስትሄድ ወደ ት/ቤት
ስራዋን ሠርታ ነው አግዛ እናት አባት
ወንድም የላት እህት እንዳይረዷት
ህልሟን ሳታሳካ እየፈራች እንዳይድሯት
አቋርጣ ብዙ ኪ.ሜ ስትሄድ ት/ቤት
ሰቃይ ነች በትምህርቷም
በስራዋም አታውቅ ወለም ዘለም
ወላጆቿ ልፋትና ድካሟን አይተው
ላኳት ዘመድ ጋ እንድትማር በከተማው
ከተማ ስትሄድ ቢገባትም ግራ ባትለምደው
ስትቆይ ትንሽ ከተማውን ለመደችው
ህልሟንም አሳክታ የአባት የእናቷን ምርቃት አግኝታ
ብርታትም አግኝታ
እንድታየው ነገን ዛሬን በርትታ
ትሠራለች ደክማ ለፍታ
ያቺ የገጠሯ ልጅ ህልሟን ታሳካለች
ነገንም ታየዋለች
ዛሬን ጠንክራ ከሰራች
ለነገ እንጀራዋን ትጋግራለች
ነገን እንድታዩ ዛሬን ጠንክራችሁ ስሩ
የገጠሯ ብርሃን ትላለች እንዳትበሉ ሳትሰሩ
ህልም ካለሽ አላማ ካሰብሽበት እንድትደርሺ
ሁሉንም እያልሽ እሺ
ሲመክሩሽ ጥሩውን እተቀበልሽ
ሲቆጡሽ መጥፎውን እየጣልሽ
ስትወስኚ እያሰብሽ እያሰላሰልሽ
ስታቅጂ የሚጠቅም ለሀገርሽ
ህልምሽን አሳኪ ጠንክረሽ
የገጠሯ ብርሃን አንቺ ስለሆንሽ
ገጣሚ
ሜሮን ሲሳይ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.7K viewsAbela, edited  14:54
Open / Comment
2021-11-12 11:49:32 አባቴ

ልንገርህ አባቴ የሆዴን አውጥቼ
ሳርቅ ካጠገብህ መቼም የሁን መቼ

ሁሌም በልቤ ዉስጥ ዙፋንህን ይዘህ
ትኖራለህ በልቤ ዉስጥ ለኔ ነግሰህ።

የባትነት ፍቅርክ መቼም ሳይለየኝ
አለ በልቤ ውስጥ ሁሌም ትህ እንዳለኝ

ልጄ ብለህ ስትጠርኝ በጣፋጭ አንደበትህ
ማረገውን ሳጣ ከደስታ ብዛትህ

አያልቅም ተነግሮ አባ የንተ ውለታ
ቢዘከር ቢዘከር ሁሌ ጠዋት ማታ

ብትጨነቅ ለኔ ብትቆጣ ለኔ
ምን ማርግ ....
ችላለው አያሳያኝ የንተን ክፉ ለኔ

የእናት ምትኬ ነህ የአምላኬ ስጦታ
ከሰማይ በታች የለህኝ መከታ

ለኔ ህይወት ስኖር የንተን እረስተህ
በፍቅር ብርሃን ብርሃኔን አብርተህ

በል እረፍ እንግዲ ልርዳህ በተራዬ
ለሁሉም ቀን አለ አሁን ነው ፋንታዬ

ለውለታህ ምላሽ የንሰኝል ቃል
ድንገት ዞር ስትል እንካን ሳቅህ ቁጣህ ይናፍቃል

ክፉ አይንካብኝ እስከ ዘላለሜ
ካንተ በፊት ያርገው ያንተን ክፉ ለኔ

ያላንተ ባዶነው ሳስበው ህይወቴ
ክፉም ሆንክ ጥሩ ኑርልኝ አባትቴ


Lamrot

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
136 viewsAbela, 08:49
Open / Comment
2021-11-12 07:57:56 ሁሉ ላንቺ !

ለናፍቆቴ :ቋንቋ:ፊደል:አጣምሬ:
ቅኔ:ልፅፍልሽ:ቃላትን:ደርድሬ:
እንደለመደብኝ: በተመስጦ:ስንር:
የብዕሬን:ቀለም:ወረቀት:ላይ:ስጭር:
የረቀቀ:ኀሳብ:ሳወርድ:ሳወጣ:
አንድ:አጭር:መፍትሔ:ከአይምሮዬ:መጣ!
......................................
ለምግባርሽ:ፀዳል:ለህሊናሽ:ቀመር:
ምንም :አዲስ:ስንኝ:ባላቆም:መደርደር:
እስከዛሬ:ድረስ:ያሰናዳኋቸው:
እያንዳንዱን:ግጥሞች:ላንቺ:አደረኳቸው!!

By Dawit tumay

17/2/2014E.C

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.3K viewsAbela, 04:57
Open / Comment
2021-11-11 07:27:25 አንቺ ባለሽበት ፣ሚባለውን እንጃ
እኔ ባለሁበት ፣ ወሬ እንደጠብ መንጃ
የታጠቀ ሞልቷል ፣ ቢደላም ቢከፋም
ጆሮ አይሰማው የለም
የሚበላ እንጂ ፣ የሚባል አይጠፋም !
#ይባላል !
።።
ለምሳሌ ያህል
ትጥቃችን ባያልፍም
ከዱላ ከድንጋይ ፣ ግፋ ቢል ከክላሽ
ወዮለት ለጠላት ፣ ኋላ እንዳይበላሽ
ኒውክለር ሲመካ
አደቧን ትያዝ ግብፅ ፣ ትረፍ አሜሪካ
አላርፍም ካሉ ግን ፣ ወየው ለሁለቱም
ባለም ፊት ፈስ በፈስ
እንዳናደርጋቸው
በእጃችን ነው ያለው ፣ ደብተራም መተቱም
ይባላል
፣፣፣፣
ለምሳሌ ያህል
ሰማንያ ሺህ ዳቦ ፣ ሊያውም በአንድ ቀን
ሊጋገር ነው ሲሉን ፣
በምን መብራት ብለን ፣ አናውቅም ጠይቀን
እንዲሁ በማመን ፣ ሆዳችን ይሞላል
በመሪ አንደበት
ደም ያፀናው ሰንደቅ ፣ ጨርቅ ነው ይባላል።
።።።
እኔ ባለሁበት ፣ በመኖሬያዬ ሀገር
ከፀሐይዋ በታች ፣ የማይባል ነገር
አንዳች አይገኝም ፣ ሁሉ አፉን ያክላል
የሚለው ያጣ ሰው
የተባለን ነገር ፣ "አይባልም "ይላል
።።
የሆነው ሆነና ፣ ባለሁበት ሀገር
የማይባል ነገር
አጋጥሞኝ አያውቅም
ለምሳሌ ያህል
አባይ በአምስ አመት
ተገድቦ ያልቃል
በኢትዮጵያ ምድር ፣ ፀሀይ አትጠልቅም
አስራ አንድ ፐርሰንት
ሀገሪቱ አድጋለች ፣ በኑሮ ብንደቅም
ስልጣን የህዝብ ነው ፣ ግን ለህዝቡ አንለቅም
ይባላል

ለምሳሌ ያህል
ባይቆጥራቸው እንጂ፣ ዘንግቶ ምናልባት
ጠቢቡ ሶሎሞን
ከጠቢቡ በላይ ፣ አይበልጥም በእቁባት
#ይባላል
በላይ በቀለ ወያ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
793 viewsAbela, edited  04:27
Open / Comment
2021-11-10 18:49:31
547 viewsAbela, 15:49
Open / Comment
2021-11-10 08:02:04 የእኔን ፍቅር መግለፅ በቃላት ሲያቅተው
በድርጊቱም ገልፆ ለሱ አልበቃ ሲለው
እስካሁን የኖርኩት የቆየው ህይወቴ
ላንቺ ነው የምኖረው እስከ እለተ ሞቴ
እወድሻለሁኝ እያለኝ አባቴ
ፍቅር ሲዘራብኝ ባልታረሰዉ ልቤ
አፍታም አልፈጀበት ሲሳሳለት ቀልቤ
ህይወትን በፍቅር በንፁህ ልቦና
ለሚወዱት መሞት ሲልቅም አለና
ታምኖ መሰዋት ነዉ ለህይወቱ ቀና
እያለኝ አባቴ
ልዩ ጥበብና ልዩ ማስተዋልን ፈጣሪ ሲቸረው
ችሎታዉን ልቤ ሁሌ እንዲዘክረዉ
አለና እንዳስበዉ
ባዶ እጁን ተጓዘ ዉስጤን እያመሠዉ

ፅጌሬዳ አስናቀዉ
171 viewsAbela, 05:02
Open / Comment
2021-11-09 20:04:47 ብቻ እንዲያ ነበረ የተውነው ፤ ጠብታ ፍቅር ሳናስቀር፥
የትም ብንደርስ ፤ የትም ልንቀር፤
ሲመናተል ስመናቀር...
ተፎካክረን ስንወጣ መንገድ ወስዶ፥
ነገር በርዶ፤
መቆም ሲያሰኘው እግር ፣
ልባችን ይሆነው ችግር




!
ይሄው ከምንም አንለምድ
ዛሬን አናፈቅር ፣አንወድ።


#በአስካለ ልቅና
369 viewsAbela, 17:04
Open / Comment
2021-11-09 14:05:28 [ ትጉህ ደቀመዝሙር ]

አንስታ ስትጥለኝ ዘራፍ ባይ ፎካሪ
ድጋሚ ስትጥለኝ ተነሽ ተወርዋሪ
ብርጭቆ ነው ብላ ስትጥለኝ ልትሰብረኝ
ከድንጋይ ጠንክሬ ብረት ሁኜ እምገኝ
እግሮቼን ብትቆርጠኝ በደረቴ እምሳብ
አርቄ እማስብ ብልህ እንደ እባብ
ጥገቴን ስትቀማኝ የተስፋ ላም እማልብ
እንጦሮጦስ ጥላኝ አድባር ላይ እምገኝ
በረዶ ነው ብላ እሳት ላይ ስትጥደኝ
ነጥሬ እምወጣ ወርቅ ሁኜ እምገኝ
በእሳት እምትፈትን ህይወት ጨካኝ መምህር
እኔ እጄን እማልሰጥ እጅ መንሳት እንጅ
እጅ መስጠት እማልወድ ብርታቴ እሚጨምር
የህይወት ተማሪ ትጉህ ደቀመዝሙር።

ጥቅምት 19/2014/ዓ/ም

ብርሃኑ ዘላለም
393 viewsAbela, 11:05
Open / Comment